በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት አደረጉ

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አርቲስት ታማኝ በየነ እንዲሁም ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በክብር እንግድነት በተገኙበት ጀኔቫ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ለኢሳት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ የሆነው ወጣት ጴጥሮስ አሸናፊ እንደገለጠው ዝግጅቱ ከታሰበው በላይ በስኬት መካሄዱን ገልጿል ( ) አርቲስት ታማኝ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ለኢሳት የሚያደርገውን ድጋፍ በስዊዘርላንድ ጀምሯል። ከአውሮፓ አገራት መካከል በስዊድን ...

Read More »

በገንዘብዎ ሳይሆን በጊዜዎ የሚገዙት ሎተሪ በኢሳት !

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን / ኢሳት / በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን፣ በድህረ ገጽ፣ በፌስ ቡክና በትዊተር የሚዲያ ዘርፎቹ  በወር ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ጎብኚ ያለው ነው። ይህ ከፍተኛ አድማጭና ተመልካች ያለው የሚዲያ ተቋም በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ተቀባይነት ጠብቆ ለመቆየት፤  ስራውን እያሳደገና ወደ ኢትዮጵያ የሚያድርገውንም የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ስርጭት አስተማማኝ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። በሚያስተላልፈው ፕሮግራምም የተለያየ የህብረተሰብ ክፍልን ፍላጎት ለማሟላት በየጊዜው ያልተቋረጠ ፕሮግራሞችን የማስፋፋት ስራም እያከናወነ ...

Read More »

መድረክ ለረጅም ጊዜ ሲያጓትተው የነበረውን ማንፌስቶ አጸደቀ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ ክርክር በታየበት የመድረክ ጉባኤ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት ማንፌስቶውንና መተዳደሪያ ደንቡን አጽድቀዋል። ባለ 25 ገጹ ማንፌስቶ ላለፉት ስድስት ወራት ሲዘጋጅ  የቆየ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ በፈጀ ክርክር ጸድቋል:፡፡ ላለፉት 4 አመታት ሲንከባለል የቆየውና የድርጅቶች የልዩነት ምንጭ ተደርጎ ይታይ የነበረው መተዳደሪያ ደንብም እንዲሁ ጸድቋል። “በጣም ደስ የሚል ኢትዮጵያዊ መድረክ ነበር፣ ቋንቋው፣ ...

Read More »

ኦህዴድ ለሶስት ቡድኖች መከፋፈሉ ታወቀ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት በአብዛኛው የኦሮሚያ ዞኖች በተለይም በምስራቅ ኦሮሚያና በአርሲ ዞኖች የሚገኙ የድርጅቱ አባላት ለ3 ተከፍለው እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው። የክፍፍሉ መንስኤዎች በድርጅቱ እምነት ማጣት፣ ሙስናና የግል ጥቅምን ማሳደድ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አመራሮቹ እርስ በርስ እየተባሉ ይገኛሉ ያሉት ምንጮች፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የድርጅቱ ህልውና ሊያከትም እንደሚችል ጠቁመዋል። በዞን ደረጃ የሚታየው መከፋፋል ...

Read More »

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ በትናንትናው እለት በደህንነት ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት 2ቱ ጓደኞቻቸው የት እንዳሉ ዩኒቨርስቲው እንዲያሳውቃቸው ጠይቀዋል። የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ከተማሪዎች ለቀረበው ጥያቄ ” ተማሪዎቹ በደህንነት ሀይሎች ተፈልገው የተወሰዱ በመሆኑ እኛ ምንም ማድረግ አንችልንም፣ ለወደፊቱም የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘው ከመጡ  አሳልፈን እንሰጣለን” በማለት መልስ መስጠታቸው ታውቋል። በሰላማዊ ...

Read More »

”የመለስ ወራሾች አገሪቷን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየከተቷት ነው” ሲል ጋዜጠኛተመስገን ደሳለኝ ገለጸ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ተመስገን ይህን ያለው፤  <<የመለስ ራዕይ በ አዲስ ታይምስ መጽሔት ተተገበረ>>በሚል  ርዕስ የአዲስ ታይምስን መዘጋት አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ማስታወሻ ነው። “ምንም ጥርጥር የለውም መለስ ዜናዊ ፍፁም አምባገነን ነበር፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ከአንድ ክፍለ ጦር በላይ የተለየ ሀሳብን እና ነፃ ሚዲያን  ይፈራ ነበር>> በማለት አስተያዬቱን መስጠት የጀመረው ተመስገን፤ << ወራሾቹም ...

Read More »

ሕዝቡ በምርጫ እንዳይሳተፍ ጥሪ ቀረበ

ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግ ሊያካሂደው ባሰበው የአካባቢ ምርጫ እንዳይሳተፍ 39ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ። ፓርቲዎቹ ህዝባዊ ጥሪውን ያቀረቡት ”ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ  አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ  ባወጡት መግለጫ ነው። የ ኢህአዴግ ምክር ቤት ጸሀፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ፓርቲዎቹ በምርጫ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን አስመልክቶ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ፦<<እነሱ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ከትልልቅ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ የሚፈጸሙ የካሳ ክፍያዎች እየተመዘበሩ ነው

ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከከፍተኛ የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ ወጪው እስከ 15 በመቶ ይደርሳል ተብሎ የሚገመተው የካሳ ክፍያ አፈጻጸም ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ከመንግስት ፕሮጀክቶች የካሳ ክፍያ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የፌዴራል የጸረ ሙስና ኮምሽን ያዘጋጀውና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን፣የስኳር ኮርፖሬሽን፣የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር፣የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ...

Read More »

በዳውሮ ዞን ሰዎች እየታሰሩ ነው

ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዞኑ ያለው ችግር እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ ፣ የችግሮች ምንጭ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች እየተያዙ ሲሆን፣ መምህር ጸጋየ ገብረመስቀል የተባሉት በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሎች ሶስት ተፈላጊ መምህራን ለመሸሸግ የተገደዱ ሲሆን፣ ፖሊስ እያሳደዳቸው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም አሉ። ከትናንት በስቲያ በእስር ላይ ከሚገኙት ከአቶ ዱባለ ገበየሁ እና ከሁለት ጠበቆች የእስር ቦታ ማዛወር ጋር በተያያዘ የታዘዙትን ለመፈጸም ...

Read More »

በዱባይ የሚኖሩ 5 ነጋዴዎች ለአዳነ ግርማ መኪና አበረከቱለት

ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዱባይ የሚኖሩ አምስት ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች  የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  ኮከብ ተጫዋች ለሆነው አዳነ ግርማ  ቶዮታ ኮሮላ መኪና  ገዝተው ሰጡት። ኢትዮጵያውያኑ ነጋዴዎች  ለ አዳነ ግርማ የመኪና ስጦታ ያበረከቱለት  ከሰላሳ አንድ አመት  በሁዋላ ኢትዮጵያ ለኣፍሪካ ዋንጫ አልፋ  ባደረገችው ውድድር ጎል ከማስቆጠሩና ኮከብ ተጨዋችነቱን በማስመስከሩ ነው። ለአዳነ ግርማ የመኪና ስጦታ ያበረከቱለት ፦አቶ ጌታቸው ሙሶኮሬ ፥ ...

Read More »