አብዛኞቹ የተፈናቀሉ የጉራፈርዳ ነዋሪዎች የደረሰቡት እንደማይታወቅ መኢአድ ገለጠ

ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ” በጭቆናና በአፈና ስልጣንን ለማራዘም የሚካሄደው ዘመቻ ቀጥሏል” በሚል ርእስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ በጉራፈርዳ ወረዳ የሚፈናቀለው አርሶአደር ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑንና የተወሰኑትም በሚዛን ተፈሪ፣ በጅማ፣ በአንቦ እና በአዲስ አበባ ያለመጠለያ ለልመና መዳረጋቸውን ገልጿል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አርሶአደሮች መሬታቸውን ተነጥቀው የአካባቢው ታጣቂዎች በጨረታ ስም እየተቀራመቱት መሆኑን የገለጠው መግለጫው፣ ወ/ሮ ...

Read More »

ለአባይ ግድብ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ የተሰበሰበው ከ35 በመቶ በታች ነው

ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ይፋ ከተደረገበት ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች እና ግለሰቦች ቃል ከተገባው 600 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 11 ቢሊዮን ብር ውስጥ እስካሁን ለመሰብሰብ የተቻለው ከ200 ሚሊዮን ዶላር ወይም 4 ቢሊዮን ብር ሊበልጥ አልቻለም። መንግስት  ሰራተኞችን እንዲሁም የንግድ ድርጅቶችን በማስገደድ እስካሁን ያሰባሰበው ገንዘብ ፕሮጀክቱን ለማሰራት ከሚፈጀው ገንዘብ ጋር ሲተያይ ...

Read More »

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ ራሱዋን መጸዳጃ ውስጥ በመግባት አጠፋች

ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ገነቴ ጌታቸው የተባለችው ተማሪ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ራሱዋን በመወርወር ያጠፋቸው ባለፈው ሳምንት ነው። በትምህርቷ ከፍተኛ ውጤት የነበራት ተማሪ ገነቴ ራሱን  ለማጥፋት ለምን እንደወሰነች በትክክል ለማወቅ ባይቻልም ተማሪዎች እንደሚሉት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው ተማሪዎች የውሀ፣ የመጸዳጃ እና ሌሎች አገልግሎቶች አልተሟሉልንም በሚል ተቃውሞ ከማስነሳታቸው ጋር ሊያያዝ  ይችላል። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸውን በማስቸገር በሚላክላቸው ገንዘብ የፕላስቲክ ውሀ  ...

Read More »

ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል

ጥር ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ብይን ለመስጠት የተሰየመ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ብይኑ አልደረሰልኝም በማለት ቀጠሮ ሰጥቷል። የችሎቱ ዳኛ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እና አሳታሚው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ማስተዋል ብርሀኑ መኖራቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ ብይኑን ለመስጠት ለየካቲት አንድ ቀጠሮ ሰጥተዋል። ...

Read More »

የሙስሊም መሪዎች የችሎት ውሎ አስቂኝ ነው ተባለ

ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በዝግ ችሎት በሚካሄደው የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ 190 ምስክሮች እንደሚቀርቡ አቃቢ ህግ ቢያስታውቅም እስካሁን የቀረቡት  ምስክሮች  11 ናቸው። ምስክሮችን የመስማት ሂደቱ በ10 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ በአሁኑ አካሄድ  አቃቢ ህግ የምስክሮችን ቁጥር ካልቀነሰ በስተቀር በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ላይጠናቀቅ ይችላል። የውስጥ ምንጮች እንደገለጡት አቃቢ ህግ ምስክሮችን  ሲያቀርብ የአባታቸውን ...

Read More »

በጉርዳፈርዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረጋጣ ቀጥሏል

ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ዞን በጉርዳፈርዳ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረገጣ መቀጠሉ ተገለጸ። በወረዳው ባለፈው ታህሳስ አንዲት የ8 ልጆች እናት በጥይት ሲገደሉ፣ ሁለት ህጻናት በመስተዳድሩ መኪና ተገጭተው መሞታቸውን የመኢአድ ም/ሊ/መንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ለኢሳት ገልጸዋል። ታህሳስ 28/ 2005 ከምሽቱ 4 ሰአት ሲሆን 5 መሳሪያ የታጠቁ ወተዳሮች የ8 ልጆች እናት ...

Read More »

ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት የህትመት ዋጋ ጭማሪ አደረገ

ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማሽኖች እርጅናና በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ውስጥ የሚዋልለው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጦች የሕትመት ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፡፡ ማተሚያ ቤቱ በተለይ ባለቀለም ጋዜጦችን ተቀብሎ የማተም አቅሙ ከጊዜ ወደግዜ እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ብዙ ጋዜጦችን በወቅቱ ማተም ባለመቻሉ በተለይ ቅዳሜ እና እሁድ የሚወጡ ጋዜጦች _ማለትም ሪፖርተር፣ፎርቹን፣ካፒታል ጋዜጦች ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ መዳረጕቸው ...

Read More »

የአቶ ጁነዲን ያለመከሰሰ መብት ያለመነሳት ጉዳይ ማነጋገሩን ቀጥሏል

ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት በአጀንዳ መልክ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረውና ባልታወቀ ምክንያት ፓርላማው እንዳይወያይበት በተደረገው የቀድሞ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ _ሕግ አስፈጻሚው አካል አሁንም ዝምታን መምረጡ አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል፡፡ ፓርላማው ከሁለት ሳምንት በፊት ባቀረበው አጀንዳ የአንድ የም/ቤት አባል ያለመከሰሰ መብት ስለማንሳት በሚል ለውይይት አጀንዳ መያዙን ...

Read More »

አቶ ዱባለ ገበየሁና ሁለቱ ዐቃብያነ ህጎች ክስ ተመሰረተባቸው

ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን ተነስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ አቶ ዱባለ ገበየሁ ፣   አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ     ትናንት  ከሰዓት በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ግለሰቦቹ  ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳትና በማሳመጽ ፣ ሕገመንግስ  ቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር  እንዲሁም የመንግሥትን ንብረት በአመጽ በማስወደም ወንጀል ተከሰዋል። ኢሳት ያለውን የመረጃ ሰንሰለት ተጠቅሞ አቶ ዱባለን በእስር ቤት ውስጥ ...

Read More »

ከግብርና የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ከግማሽ በታች ቀነሰ

ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በግብርና ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት የሆልቲካልቸር፣ሥጋና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ገቢ በአስደንጋጭ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን አቶ ተፈራ ደርበው የግብርና ሚኒስትር ዛሬ ለፓርላማው ያቀረቡት ሪፖርት ጠቆመ፡፡ በ2005 የኢትዮጵያ የበጀት ቀመር የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከሥጋና ከቁም እንስሳት ከወጪ ንግድ(ኤክስፖርት) 299 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው ከግማሽ በታች ማለትም 130 ሚሊየን ወይም የዕቅዱን 44 ...

Read More »