በሰሞኑ ምርጫ ከፍተኛ ዘለፋዎችን ያስተናገዱት ወ/ሮ አዜብና ባለራእዩ ባለቤታቸው ናቸው

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በጨርቆስ ክፍለከተማ በተካሄደው ምርጫ ከፍተኛውን ዘለፋና ትችት ያስተናገዱት ወ/ሮ አዜብ መስፍን እና ባለራእዩ ባለቤታቸው እንደነበሩ በቆጠራው የተሳተፉ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት በ8 የአዲስ አበባ የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የተሳተፉ ታዛቢዎችን በመጠየቅ ባሰባሰበው መረጃ ከ30 በመቶ ያላነሰ መራጭ ድምጹን የሰጠ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ባዶ ወረቀት ሲያስገቡ፣ አብዛኞቹ ደግሞ ...

Read More »

እርዳታ ሰጪ መንግስታት የኢትዮጵያ የገንዘብ አስተዳደር እንዲሻሻል ጠየቁ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ከፌደራል ጀምሮ እስከ ክልሎችና ወረዳዎች ድረስ በርካታ ችግሮች የሚስተዋልበት የገንዘብ አስተዳደር  እንዲያሻሽል ጥሪ ያቀረቡት ዋነኞቹ የኢትዮጵያ ለጋሽ አገራት፣  ችግሮቹንና አሳሳቢነታቸውን የለዩ የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን ሁሉንም የፌደራል፣ የክልልና የወረዳዎች የፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊዎች አዲስ አበባ ላይ በመሰብሰብ፣ በችግሮቹና መፍትሔዎች ዙርያ ባለፉት ሁለት ቀናት ውይይት አድርገዋል፡፡ የቡድኑ አስተባባሪና በዓለም ባንክ የአፍሪካ የፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያ ...

Read More »

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በኑሮ ውድነቱ መማረሩን ቀጥሎአል

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኑሮ ውድነቱ ቅናሽ ያሳይ ይሆን በማለት ኢትዮጵያውያን ከአመት አመት ተስፋ ቢያደርጉም ተስፋቸው ግን ከተስፋነት እንዳልዘለለ በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በአምስት ክልሎች የሚኖሩ ዘጋቢዎቻችን አጠናቅረው የላኩት ዘገባ እንደሚያመለክተው በሁሉም ክልሎች የኑሮ ውድነቱ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በመላ እየጠበሰ ነው። በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል  የኑሮ ውድነቱ ተባብሶ በመቀጠሉ ህዝቡ ኑሮውን በአግባቡ መምራት እየተሳነው ...

Read More »

ከመተከል ዞን የተፈናቀሉ አብዛኞቹ የአማራ ተወላጆች ተመለሱ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከከማሺ ዞን በሀይል ተፈናቅለው በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ የአማራ ተወላጆች የተለያዩ ወገኖች በመንግስት ላይ ባሳደሩት ጫና ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንደሚለሱ ቢደርግም፣ ከመተከል ዞን በተመሳሳይ መንገድ ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ሰፍረው የነበሩት ከ2 ሺ በላይ ዜጎች አፋጣኝ መልስ አጥተው መቆየታቸውን በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆይተናል። ዛሬ ከዞኑ ባገኘነው መረጃ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደሚለሱ ተደርገዋል። ...

Read More »

ጋዜጠኛ እና መመህርት ርዮት አለሙ የዩኒስኮ ጉሌርሞ ካኖ የፕሬስ ነጻነት አሸናፊ ሆነች

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓም የሚከበረውን የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ምክንያት በማድረግ ዩኒስኮ በእያመቱ የሚያዘጋቸውን የዘንድሮውን ሽልማት ፣ ኢትዮጵያዊቱ የፕሬስ ጀግና ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ አሸንፋለች። ርእዮት ከዚህ ቀደም የኢንተርናሽናል ውሜንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን ሽልማትን አሸንፋለች።  በእስር ቤት በምታሳየው ጽናት የመላው ኢትዮጵያውያንን ቀልብ የሳበቸው ርእዮት አለሙ በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ እንግልት ቢደርስባትም እስካሁን ፈተናውን ...

Read More »

የቀድሞዋ የህወሀት ታጋይ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ተቹ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወ/ሮ አዜብ መስፍን የባለቤታቸው ወርሃዊ ደመወዝ አነስተኛ እንደነበር በመጥቀስ በኢህአዴግ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን ስሜታዊ ንግግር የሕዝብን የማመዛዘን ችሎታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ሲሉ የቀድሞ የህወሃት ታጋይ ወ/ት አረጋሽ አዳነ ተቹ፡፡ ወ/ት አረጋሽ በዛሬው ዕለት በአዲስአበባ ለንባብ በበቃው “ኢትዮ ምህዳር” ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ ቃለምልልስ ላይ የወ/ሮ አዜብን ንግግር አስመልክቶ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል፡፡አቶ መለስ ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ ያልጠበቀውን የምርጫ ውጤት አገኘ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ያለምንም ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ባደረገው ምርጫ ያልጠበቀውን ውጤት ማግኘቱን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሰባሰብናቸው መረጃዎች አመለከቱ። ምንም እንኳ ኢህአዴግ ምርጫውን ከ99 እስከ 100 ፐርሰንት እንደሚያሸንፍ ቢጠበቅም ህዝቡ በምርጫ ካርዶች ላይ ያሰፈረው መልእክት ግን ገዢው ፓርቲ ያልጠበቀውና ያለሰበው ነበር እንደ ታዛቢዎች አገላለጽ። በአንዳንድ አካባቢዎች የቀበሌ እና የወረዳ ሹሞች የምርጫ ታዛቢዎች እና ...

Read More »

መንግስታዊ ተቋማት በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት አስተዳደራዊ በደሎች ከዓመት ዓመት እያደገ ነው

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ከሕዝብ ከሚቀርቡለት አስተዳደራዊ በደሎች መካከል በመንግስት ላይ በተለይ በፍትህ ተቋማት ላይ የሚቀርበው የአስተዳደራዊ ቅሬታ ብዛት ከፍተኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት ወደተቋሙ የመጡ ቅሬታዎች መካከል አንድ ሶስተኛ ወይም 31 በመቶ ያህል ከፍተኛ ድርሻ የያዙት የመንግስት ተቋማት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ማለትም ከቀበሌ መዋቅር አንስቶ አስከ ፌዴራል ባሉ ...

Read More »

የእርዳታ ድርጅቶች በዝቅተኛው የኦሞ ሸለቆ የደረሰውን የህዝብ መፈናቀል ከቁም ነገር አለመቁጠራቸውን አንድ ድርጅት አስታወቀ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ለኢሳት በላከው ዘገባ በኦሞ ሸለቆ ላይ የሚገነባው ግልገል ጊቤ 3 እና ለስኳር እርሻ በሚል የሚካሄደው የመሬት ወረራ በአካባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ቢያስከትልም፣ መንግስትን በገንዘብ የሚደጉሙት ለጋሽ አገራት ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት አልሰጡትም። በቦዲ. ክዌጎ እና ሙርሲ ህዝቦች ኩራዝ እየተባለ ለሚጠራው የስኳር ፕሮጀክት መሬቱ ይፈለጋል በሚል ከቦታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። ነዋሪዎቹ አብዛኛውን ከብቶቻቸውን ...

Read More »

ከሰሀራ በታች ያሉ አገሮች በመጪዎቹ 3 አመታት ፈጣን እድገት ያስመዘግባሉ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ የአለም ባንክን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች በመጪዎቹ ሶስት አመታት ከሌላው አለም አማካኝ የእድገት መጠን ጋር ሲተያይ የተሻለ እድገት ያሳያሉ። የአብዛኞቹ አገራት እድገት ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ አገራት በመላክ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው፣ የስራ አጥ ቁጥር መጨመር እና ከጥሬ እቃዎች ባሻገር ገቢን ለመጨመር የሚያስቸሉ ሌሎች የስራ መስኮች ባለመፈጠራቸው ...

Read More »