ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚጓዙ የአማራ ተወላጆች ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቁጥራቸው ከ5 ሺ በላይ የሚጠጉ ከፍኖተሰላም ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በሚመለሱበት ቦታ የደህንነት ዋስትና እንደሌላቸው ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ገለጹ። የክልሉ  መንግስት በበኩሉ ስህተት መፈጠሩን በማመን ችግሩን የፈጠሩት ታች ያሉ አመራሮች ናቸው ብሎአል። ትናንት ማክሰኞ  21 መኪኖች፣ በዛሬው እለት ደግሞ 14 መኪኖች ተፈናቃዮችን ከአቅማቸው በላይ በመጫን ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ አቅንተዋል። የክልሉ ...

Read More »

የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ደጋፊ ሴቶች ቃለ ማህላ ፈጸሙ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሴቶች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት ኢህአዴግን እንደሚመርጡ አስታውቀዋል ኢህአዴግ ያለጠንካራ ተቃዋሚ በሚሮጥበት የአዲስ አበባ እና የክልል ምርጫ በአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ እና ማስፈራሪያ ሲደረግ ቆይቷል። ሴቶቹ በነፍስ ወከፍ ኮፍያ እና ቲሸርት የታደላቸው ሲሆን አንዳንዶቸች አበል እንደተከፈላቸውም ለዘጋቢያችን ተናግረዋል። በተለያዩ መኪኖች ላይ ቅስቀሳ ያደርጉ የነበሩ ሴቶች ...

Read More »

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመብራት እና ውሀ እጥረት አማረረን ይላሉ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ መብራት ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማግኘት ትልቅ ዜና እየሆነ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ የመብራት መቋረጥን ተከትሎ በሚፈጠረው ችግር ባንኮች፣ አየር መንገዶችና ሌሎች ድርጅቶች ስራቸውን በተገቢው መንገድ ለመስራት እንዳልቻሉ ገልጿል። ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ መጀመሩዋን የተናገረው መንግስት፣ መብራትን በፈረቃ ለማቅረብ መዘጋጀቱንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመብራት እጦት ብቻ ሳይሆን በውሀ ችግርም ...

Read More »

የአቶ መለስ ዜናዊን ስም፣ ምስልና ሥራዎቻቸውን መጠቀምን የሚከለክልና የሚፈቅድ የመመርያ ረቂቅ ቀረበ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የአቶ መለስ ዜናዊን  ማንኛውም ከመንግሥትና ከፓርቲ ሥራዎች ጋር ያልተያያዙ ምስሎች ወይም ፎቶግራፎች ባለቤትነት የቤተሰቦቻቸው ብቻ ነው። ረቂቅ መመርያው፣ ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማሰባሰብ፣ ለሽያጭ፣ ለባዛር፣ ለጨረታ ወይም ለማንኛውም ዓይነት ጥቅም ማስገኛነት ሊሰቅል፣ ሊለጥፍ፣ ሊቀርጽ ወይም ሊያስቀምጥ እንደማይችል ይከለክላል፡፡ የአቶ መለስን ፍቅርና ክብር ለመግለጽ የሚፈልጉ ምስላቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ግድግዳ ላይ ሊሰቅሉ፣ በአልበም ውስጥ፣ ...

Read More »

በፍኖተሰላም ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ዛሬ ሊነጋጋ ሲል ከ20 በላይ መኪኖች የፍኖተ-ሰላም ከተማን ማጨናነቃቸውን የተናገሩት ተፈናቃዮች፣ ከብር-ሸለቆ የመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከዞን እና ከወረዳ ፖሊስ አባላት ጋር በመተባበር፣ ተፈናቃዮቹ ወደ መኪኖቹ እንዲገቡ አዘዋል። ጥሪው ድንገተኛ የሆነባቸው ተፈናቃዮች የሚያደርጉት ጥፍቷቸው ሲላቀሱ ፣ ወላጆቻቸውን ተከትሎም ህጻናት ሲያለቅሱ ይታዩ እንደነበር የአይን እማኞች ይናገራሉ። አንድ ሌላ ተፈናቃይ ዛሬ ስላጋጠማቸው ነገር ሲናገሩ ...

Read More »

ከሚኒት ወረዳ የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን የደቡብ ክልል የአንድነት ፓርቲ ተወካይ ገለጹ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ በትናንት ዘገባው በደቡብ ክልል በሚኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ እየተባለ  በሚጠራው አካባቢ ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪዎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ክልል ተወካይ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሽበሺ የተፈናቃዩ ቁጥር ከተጠቀሰው አሀዝ እንደሚበልጥ ተናግረዋል። አቶ ዳንኤል እንዳሉት  ካለፈው ሀሙስ ...

Read More »

የአፋር ምክር ቤት አባላት የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲወርዱ ጠየቁ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአፋር ክልል ካቢኔ  ውስጥ የተነሳው ውዝግብ አይሎ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ፣ የብአዴፓን የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊን ከሀላፊነት አንስተዋል። ሌሎች የካቢኔ አባላት በበኩላቸው ” ፕሬዚዳንቱ ” ላለፉት 18 አመታት በስልጣን ላይ ቆይተው፣ ለክልሉ ህዝብ ያመጡት ነገር ባለመኖሩ ስልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው” እያሉ ነው። አብዛኞቹ የካቢኔ አባላት ፕሬዚዳንቱ የሀወሀት ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን የአፋርን ...

Read More »

ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ለግራዚያኒ የሚሰራውን ሀውልት አለም እንዲያወግዘው ጠየቁ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያውያው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የአለማቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እና በሊቢያ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ላደረሰው ግራዚያኒ ሀውልት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት እንዲያወግዝ ጠይቀዋል። ሚ/ሩ ይህን የተናገሩት በሩዋንዳ የደረሰውን ዘር ማጥፋት 19ኛ አመት ለማስታወስ በተጠራ ዝግጅት ላይ ነው። የኢትዮጵያን እና የሊቢያን ዜጎች በግፍ የጨፈጨፈው ግራዚያኒ ሀውልት አይገባውም ብለዋል ሚስትሩ። የሚኒሰትሩ ንግግር ...

Read More »

አማርኛ ተናጋሪዎች ከደቡብ ክልል በድጋሜ እንዲለቁ ተደረገ

መጋቢት ፴  (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እንደገለጠው፣ ቀደም ሲል በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ20 ሺ ያላነሱ አርሶደሮች የገቡበት ሳይታወቅ፣ አሁን ደግሞ በዚሁ ዞን በሚኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪዎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ ከመኖሪያ አካባቢያቸው 61 ከብቶችና ግምቱ ያልታወቀ እህል ...

Read More »

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አርሶአደሮች የደረሰባቸውን ግፍ ለሚዲያዎች እያቀረቡ ነው

መጋቢት ፴  (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲስ አድማስ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ ወደ ፍኖተሰላም በማቅናት አንድ ዘገባ አቅርቧል። በዘገባውም ተፈናቃዮች የደረሰባቸውን ግፍ በዝርዝሮ አትቷል። “ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፣ ትላለች የአዲስ አድማሱዋ ናፍቆት ዮሴፍ ። ...

Read More »