ከሚኒት ወረዳ የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን የደቡብ ክልል የአንድነት ፓርቲ ተወካይ ገለጹ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ በትናንት ዘገባው በደቡብ ክልል በሚኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ እየተባለ  በሚጠራው አካባቢ ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪዎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ክልል ተወካይ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሽበሺ የተፈናቃዩ ቁጥር ከተጠቀሰው አሀዝ እንደሚበልጥ ተናግረዋል።

አቶ ዳንኤል እንዳሉት  ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ 3 ሰዎች እንደተገደሉ በአንድ ወር ውስጥ 7 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል

አቶ ዳንኤል ሽበሺ መንግስት በአማራው ህዝብ ላይ የሚከተለው ፖሊስ ከግንቦት20፣ 1983 ዓም በፊት የነበረውን ፖሊሲ እየተገበረ መሆኑን እርሳቸው የኢህአዴግ አባል በመሆን በሰሩበት ወቅት በተግባር ለማረጋገጥ እንደቻሉ ገልጸዋል።