ማርጋሪት ታቸር አረፉ

መጋቢት ፴  (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚ/ር በመሆን እኤአ ከ1979 እስከ 1990 የቆዩት ታቸር በ87 ዓመታቸው በድንገት አርፈዋል። ታቸር በእንግሊዝ ታሪክ የመጀመሪያዋ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሴት ጠ/ሚኒስትር ነበሩ። በእንግሊዝኛ ( ዘ አይረን ሌዲ) እየተባሉ የሚጠሩት ታቸር በዘመናቸው በተከተሉት የኢኮኖሚ ፍልስፍና አወዛጋቢ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል። በመላው አለም የሚገኙ መሪዎች ታቸር በጊዜያቸው ላሳዩት ጽናት አድናቆታቸውን እየገለጡላቸው ነው።

Read More »

ተፈናቃይ አርሶአደሮች የደረሰባቸውን ጉዳት በመዘርዝር ለመንግስት ባለስልጣናት አቀረቡ

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፍኖተሰላም ከተማ ላይ ሰፍረው የሚገኙትን ተፈናቃዮች ያነጋገሩ ሲሆን፣ ተፈናቃዮችም ልዩ ሀይል እየተባለc በሚጠራው ታታቂ ቡድን የደረሰባቸውን ግፍ ያለምንም ፍርሀት ማቅረባቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አንድ ተፈናቃይ ገልጠዋል። በስብሰባው ላይ ከአማራ ክልል መገናኛ ብዙሀን የተውጣ  ጡ ጋዜጠኞች ቢገኙም፣ ስብሰባውን እንዳይቀርጹ መደረጉን አንድ በስፍራው አለው ...

Read More »

ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለን” አለ

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ” የንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤት መካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ  ” እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል። ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛው አዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ ...

Read More »

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የደረሰውን መፈናቀል በመቃወም ፊርማ እያሳበሰቡ ነው

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በጀመሩት የፊርማ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ በርካታ የጀርመን ዜጎች ፊርማቸውን አኑረዋል፡ ዝግጅቱን እያስተባበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ የሲቪክና ፖለቲካ ድርጅቶች ጥምረት የተባለው ገለልተኛ ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በላይ ወንድአፍራሽ ለኢሳት እንደገለጡት፣ ዝግጅቱ ለሚቀጥለው አንድ ወር ይቀጥላል። የተሰባሰበውን ፊርማም ለጀርመን ፓርላማ፣ ለጀርመን የተለያዩ መሰሪያ ቤቶች፣ ለአውሮፓ ህብረትና፣ ለተለያዩ የአውሮፓ አገራት፣ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ለሂውማን ...

Read More »

በፌስ ቡክ “ስም አጉድፈሀል” የተባለው ተማሪ በ5 ሺ ብር ዋስ ተፈታ

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነው  ማንያዘዋል እሸቱ ለኢሳት እንደገለጠው ከአንድ ሳምንት እስር በሁዋላ፣ የአርባ ምንጭ ፍርድ ቤት “ስትፈለግ ትመጣለህ” በማለት በ5 ሺ ብር ዋስ ለቆታል። ወደ ፈተና ለመግባት ሲዘጋጅ ሶስት ፖሊሶች መጥተው የፍርድ ቤት ማዘዣ በማሳየት እንደወሰዱትና በአርባ ምንጭ እስር ቤት አንድ ሳምንት ማሳለፉን ተማሪ ማንያዘዋል ገልጿል። ተማሪ ማንያዘዋል፣ ...

Read More »

ሙስና እና ፖለቲካ ብአዴንን እየፈተኑት ነው

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“ማንኛውም ሰው” ይላሉ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ” ስለ እነ አቶ በረከት ክፉ ቢያወራ በደቂቃዎች ውስጥ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያገኘዋል፣ ባበህርዳር።” በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ በተለመደው ቋንቋ ሙስና ወይም ጉቦኝነት የድርጅቱ ዋነኛው የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ነበር። የብአዴን ነባር ታጋይ አቶ ህላዊ ዮሴፍ፣ እውን ከፍተኛውን አመራር የምንጠይቅበት ስርአት አለን?” ሲሉ ያቀረቡት ...

Read More »

ረገብ ብሎ የሰነበተው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ተካሄደ

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጁመአን ስግደት ተከትሎ ዘወትር አርብ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሰሞኑን ረገብ ብሎ ቢቆይም  ፣ በዛሬው እለት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ቤኒን መስጊድ ተካሂዷል። ሙስሊሞቹ እጅግ ለእጅ በመያያዝ አንድ መሆናቸውን አሳይተዋል። የአለፉትን 1 አመት ከ3 ወራት በከፍተኛ ጫና እና እንግልት ያሳለፉት ሙስሊሞች ” የታሰሩ መሪዎች ሳይፈቱና ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ” ትግላችንን አናቆምም ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳድር ለ40 በ60 ቤቶች በድጋሜ ምዝገባ ሊጀምር ነው፤ የምርጫ ቅስቀሳው አካል ነው ተብሎአል

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በሚያዝያ ወር ለሚያካሂደው የአዲስአበባና የአካባቢ ምርጫ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚረዳውን የ40 በ60 ቤቶችና የኮንዶምኒየም ቤቶች ዳግም ምዝገባ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ በተወሳሰበ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር በሕዝብ ዘንድ ክፉኛ የሚወገዘው የኩማ አስተዳደር በተለይ የአዲስአበባ ከተማ ሕዝብን ቁጣና ኩርፊያ ለማለዘብ ይረዳኛል በሚል ያሰበውን ከቤቶች ልማት ጋር የተገናኘ ቅስቀሳና ...

Read More »

የአቶ መለስ ፋውንዴሽን ነገ ይፋ ይሆናል

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነገው ዕለት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሚካሄደው የመለስ ፋውንዴሽን መስራች ጉባዔ ላይ 13 አባላት ያሉት የቦርድ አባላት እንደሚመረጡና ፋውንዴሽኑ የመለስ ሁለት ልቦለድ መጽሐፍትን ጨምሮ ሌሎችንም ፖለቲካዊ ጹሑፎች እንደሚያሳትም ተጠቆመ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በሞት ከተለዩ ከሰባት ወራት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ተተኪው አመራር የእሳቸውን ሌጋሲ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለማስቀጠል በገባው ቃል ...

Read More »

የመንግስት ባለስልጣናት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አርሶአደሮችን እያነጋገሩ ነው

መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአማራ ክልል የተውጣጡ ባለስልጣናት በፍኖተ ሰላም ከተማ ሰፍረው የሚገኙትን የቤንሻንጉል ጉሙዝ አማርኛ ተናጋሪ ተፈናቃዮችን በማነጋገር ላይ መሆናቸውን በሰፍራው የሚገኙ ተፈናቃዮች ገለጡ። ባለስልጣናቱ ተፈናቃዮቹ የምርጫ ካርዶችን፣ ግብር የከፈሉባቸውን ደረሰኞች፣ የክልሉን መታወቂያ እንዲሁም ሌሎች አባሪ ሰነዶችን አቅርበው እንዲያስመዘግቡ አድርገዋል። ይሁን እንጅ ተፈናቃዮች ወደ መጡበት አካባቢ ስለመመለስ እና አለመመለሳቸው ወይም ሀብትና ንብረታቸው ተመልሶላቸው ወይም ካሳ ...

Read More »