ማርጋሪት ታቸር አረፉ

መጋቢት ፴  (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚ/ር በመሆን እኤአ ከ1979 እስከ 1990 የቆዩት ታቸር በ87 ዓመታቸው በድንገት አርፈዋል።

ታቸር በእንግሊዝ ታሪክ የመጀመሪያዋ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሴት ጠ/ሚኒስትር ነበሩ።

በእንግሊዝኛ ( ዘ አይረን ሌዲ) እየተባሉ የሚጠሩት ታቸር በዘመናቸው በተከተሉት የኢኮኖሚ ፍልስፍና አወዛጋቢ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል።

በመላው አለም የሚገኙ መሪዎች ታቸር በጊዜያቸው ላሳዩት ጽናት አድናቆታቸውን እየገለጡላቸው ነው።