ከ10 አመታት በላይ ጊዚያቸው ያለፈባቸው መድሀኒቶች በመጋዘን ውስጥ ተገኙ

የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር እንዳስታወቀው ጊዜያቸው ያለፈባቸው በአማካኝ ከ8 እስከ 14 አመታት የቆዩ መድሀኒቶች በከነማ ፋርማሲዎች ተከማችተው ተገኝተዋል።

የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና እንዳስደመጠው መድሀኒቶቹ በህገወጥ መልኩ እየወጡ ለፋርማሲዎች ሳይሸጡ አልቀረም። የአዲስ አበባ የጤና ቢሮ እንዳስታወቀው መድሀኒቶቹ የተጠራቀሙት የኦዲት ምርመራ ስላልተደረገባቸው ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል።

በመንግስት ፋርማሲዎች ተከማችተው የሚገኙ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መድሀኒቶች አንዳንድ ግለሰቦች ለግል ፋርማሲዎች እያወጡ እንደሚሸጡ ኢሳት ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል።