በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት ሰዎች ሞቱ

ጥር ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በወረዳ 10 በተለምዶ ሰራተኛ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ47 አባዎራዎች መኖሪያ ቤቶችና አራት ተሽከርካሪዎች በአደጋው ምክንያት የወደሙ ሲሆን ሶስት ሰዎችም በአደጋው ምክንያት መሞታቸው ታውቋል።

እሳቱን ለማጥፋት በስፍራው በነበሩ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ 2 ሰራተኞችና 4 የግቢው ነዋሪዎች ላይ ደግሞ የቃጠሎ አደጋ ደርሷል።

የኤጀንሲው የኮሚዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳሉት በአደጋው ሳቢያ የደረሰው የንብረት ውድመት እየተጣራ ነው።

ከንቲባ ኩማ እና እና የካቢኔ አባላትም አደጋው በደረሰበት ስፍራ ጉብኝት አድርገዋል።

በአሁኑ ወቅት ለሟች ቤተሰቦች ቤት የተሰጣቸው ሲሆን ፥ በወረዳ 10 ለሚገኙት የአደጋው ተጎጂዎችም በሙሉ መጠለያ ለመስጠትም ከንቲባው ቃል ገብተዋል።