ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ባወጣው ዘገባ ደሃ አገሮች “ቢዝነስ” ለመስራት ምቹ ናቸው ተብለው ደረጃ ውስጥ እንዲገቡ በማሰብ መሬታቸውን ለሃብታም አገራት ነጋዴዎች እያስረከቡ ነው። አገሮች በአሜሪካ ባለስልጣናት አይን እየተገመገሙ ” ለቢስነዝ ስራ ምቹ ናቸው አይደሉም” እየተባሉ እንደሚመደቡ የገለጸው ኦክላንድ፣ በዚህም የተነሳ የደሃ አገር መንግስታት ሀብታሞችን ለማስደሰት ሲሉ ድሆችን እየጎዱ መሬትና ሌሎች ማእድናት እንዲዘረፉ እያደረጉ ነው። ...
Read More »የሱዳኑ መሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ፈቀዱ
ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንቱ ትናንት ባካሄዱት ፕሬዚዳንታዊ አዋጅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስራቸውን በነጻነት እንዲሰሩና እንዲሰበሰቡ እንዲሁም የመንግስትን ሚዲያ እኩል እንዲጠቀሙ ፈቅደዋል። ውሳኔው በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ውይይት ለማድረግ አዲስ ጅማሮ ነው ተብሎለታል። ፕሬዚዳንት በሽር 83 ከሚሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ድርጅትቶች ጋር በመጪው እሁድ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ የፕሬስ ነጻነት ያለምንም ገደብ እንዲከበር እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ መንግስትን በሃይል ለማውረድ ...
Read More »በየረር ባሬ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ መምህራን ታሰሩ
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል ነዋሪ የሆኑ የየረር ጎሳ አባላት ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ ያነሱዋቸውን ጥያቄዎች ተከትሎ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 16 የጎሳው አባላት መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከወራት በፊት በክልሉ መስተዳድር ትእዛዝ ልዩ ሚሊሺያ እየተባለ የሚጠራው ሃይል በጎሳው አባላት ላይ በከፈቱት ጥቃት ከ50 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ቀደም ብሎ በኢሳት የተዘገበ ሲሆን፣ ድርጊቱ ተጣርቶ እርምጃ ...
Read More »መንግስት የመንግስት ተሽከርካሪዎች በኮድ 4 ሰሌዳ ቁጥር ብቻ እንዲጠቀሙ መመሪያ አወጣ።
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት መመሪያውን ያወጣው በግለሰብ ታርጋዎች በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎች መበራከታቸውን በተመለከተ ዘገባው በኢሳት ከቀረበ በሁዋላ ሲሆን፣ ታዛቢዎች ግን አዲሱ መመሪያ ይስሙላ ነው ይላሉ። ኢሳት የምንጮቹን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል የመመሪያውን ቅጅ ይፋ ባያደርግም ከአፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር መ/401/653/2 የተላለፈው ሠርኩላር የመንግስት መስሪያ ቤት ተሽከርካሪዎች ከኮድ ቁጥር 4 ...
Read More »በሶማሊ ክልል የኮካ ኮላ ምርት እንዳይገባ ታገደ
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የኢሳት ምንጭ እንደገለጸው ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ የኮካ ኮላ ምርት ወደ ክልሉ እንዳይገባ በመታገዱ ነዋሪው ህዝብ ከሶማሊላንድ እየታሸገ በኮንትሮባንድ የሚገባውን ኮካ ኮላ ለመጠቀም ተገዷል። ኢትዮጵያ በሚገኘው በኮካ ኮላ ድርጅትና በክልሉ መንግስት መካከል ልዩነት መፈጠሩም ታውቋል። ቀደም ብሎ በክልሉ የኮካ ምርትን የሚያከፋፍለው የታዋቂዋ ባለሃብት የወ/ሮ ሱራ ድርጅት ሲሆን፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለመሪዎቻቸው አጋርነታቸውን በተቃውሞ ሊገልጹ ነው
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀረባባቸውን ክስ በፍርድ ቤት እየተከራከሩ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በፍርድ ሂደቱ ላይ ያቀረቡት መከራከሪያና ያሳዩት ጥንካሬ የመላውን ሙስሊም ማህበረሰብ ቀልብ በሳበበት በዚህ ወቅት፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመሪዎቹ ያለውን ድጋፍ ለመግለጽና የመንግስት ህገወጥ እርምጃ ለመቃወም የፊታችን አርብ የተቃውሞ ድምጹን እንደሚያሰማ ታውቋል። የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በእስር ቤት ውስጥ እጅግ አሰቃቂ ሆነ ...
Read More »ዩክሬን መንግስት ለሩሲያ ደጋፊዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶስቱ የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች የተነሳው አመጽ እንደቀጠ ሲሆን የዩክሬን መንግስት አመጹ ካልቆመ በ48 ሰአታት ውስጥ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል፡ ሉሃንስ፣ ዶኔትስክ እና ካርኪቭ በተባሉት የዩክሬን ግዛቶች የሚኖሩ አብዛኞቹ ሩሲያውያን ፣ ከሩሲያ ጋር መቀላቀልን ወይም ነጻ የሆነ ግዛት የመመስረት ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፣ ይህንንም ለማሳካት ቁልፍ የሚባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ይዘዋል። ሩሲያ በክርሚያ እንዳደረገችው ሁሉ ...
Read More »የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አወዛጋቢ አዋጅ ሥራ ላይ ዋለ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት መጨረሻ በአዲስ መልክ በአዋጅ የተቋቋመውና ዜጎች መረጃ እንዲሰጡ የሚያስገደድደው ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት አዲሱን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በ1987 ዓ.ም የደህንነት የኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን በሚል ስያሜ ተቋቁሞ በስራ ላይ የነበረው ይህው ተቋም የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት እንዲችል በሚል ባለፈው ዓመት አዲስ የማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማው ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል፡፡ ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ወ/ሮ አስቴር ማሞን ሾሙ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ዛሬ ፓርላማ በድንገት ተገኝተው የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩትን ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር እንዲሆኑ ያቀረቡትን ሹመት ፓርላማው ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ የኦህዴድ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚደንት ከነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሞት በኃላ ኦህዴድ ባደረገው የሥልጣን ሽግሽግ አቶ ሙክታር ከድር ከምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ተነስተው ...
Read More »የምእራብ ጎጃም ነዋሪዎች በመብራት እጦት መማረራቸውን ገለጹ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በፍኖተ ሰላም እና አጎራባች ወረዳዎች ማለትም በቡሬ ፤ በጃቢ ጠናን ፤ ፈረስ ቤት ፤ ይልማና ዴንሳ፣ ፤ሜጫ ፣ አቸፈር እና ቋሪት የሚኖሩ ነዋሪዎች በፍኖተ ሰላም ከተማ በጃቢ አዳራሽ ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ ከክልሉ መስተዳደር ጋር በተደረገ ውይይት በመብራት እጦት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን በምሬት ተናግረዋል። የመብራት ሃይል ሹሞች በሙስና ተዘፍቀዋል ያሉ ...
Read More »