በጋምቤላ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ተሰማ

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ተባባሪ ዘጋቢ እንደገለጸው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በክልሉ ያለው ውጥረት ጨምሮአል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እየሰራ ባለው የዋንኬ መንገድ አካባቢ ከደቡብ ሱዳን የተፈናቀሉ ስደተኞች በሰፈሩ አካባቢ አንድ ሾፌር እና አንድ የልዩ ፖሊስ አባል መገደላቸውን ተከትሎ አካባቢው በፌደራል ፖሊስ መወረሩ ታውቋል፡፡ የግድያው መንስኤ በውል ባይታወቅም የክልሉ ፖሊስ ከኤርትራ ሰርገው የገቡ አሸባሪዎች የፈጸሙት ...

Read More »

በአፋር በተነሳ የጎሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሃዊያ እየተባሉ በሚጠሩ የሶማሌ ጎሳዎችና በአፋሮች መካከል በተነሳ የእርስ በርስ ግጭት 6 ሰዎች መሞታቸውን በርካቶች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የጠቡ መነሻ ከግጦሽ መሬት ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ከትናንት ጀምሮ የቆመ ቢሆን ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለትንዳሆ የሸንኮራ ምርት ማስፋፊያ በሚል ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተነስተው ...

Read More »

በጉጅና በቦረናዎች መካከል ግጭት ማገርሸቱ ተሰማ

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግርማየ ፣ ቦቢላ ፣ መደር እና ቦኪዳዋ ቀበሌዎች ሚያዚያ 4 ቀን 2006 ዓም በተነሳ ግጭት  ከ5 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ከአካካቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። በጉጂ የወረዳ ሹማምንት እርስ በርስ ግምገማ ላይ መቀመጣቸውም ተሰምቷል። የኦሮምያ ክልል የጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዳ ሮቤ ከስልጣን መነሳታቸው ችግሩን ያበርደዋል ተብሎ ቢጠበቅም ...

Read More »

በናይጀሪያ-አቡጃ በሚገኝ አንድ አውቶቡስ ማረፊያ በደረሱ ሁለት የቦንብ ፍንዳታዎች ከ 40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ሰገበ።

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቢቢሲዋ ወኪል  ሀሩና ታንጋሳ ከአቡጃ እንዳጠናቀረችው ሪፖርት ፤ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት የትራፊክ መጨናነቅ በነበረበት  ሰዓት ሲሆን፣ አብሳኞቹ ሟቾች እና ተጎጂዎች ወደ ሥራ ለመግባት አውቶቡስ እና ታክሲ ለመሳፈር ከቤታቸው ማልደው የሚገሰግሱ ነበሩ። የዓይን ምስክሮች የበርካታ ሟቾች አስከሬን ጎዳናውን ሞልቶት ማየታቸውን ገልጸዋል።  ጥቃቱን የፈፀመው “ቦኮ ሀራም” የተሰኘው  የእስላሚስት ሚሊሺያ ቡድን ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ባዳምሲ ኒያንያ  የተባሉ የ ...

Read More »

የአገውና የጃን አሞራ አካባቢ አርሶ አደሮች በረሃብ ምክንያት ወደ ትግራይ ከተሞች እየተሰደዱ መሆኑን አንድ ታዋቂ ፖለቲከኛ ተናገሩ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የህወሃት አመራርና ነባር ታጋይ በአሁኑ ጊዜ በአረና ፓርቲ ውስጥ በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የሚገኙት ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አቶ አስገደ ገብረስላሴ ለኢሳት እንደገለጹት በሰሜን ወሎ ዞን በሰቆጣ፣ ላሌበላ፣ ዋግና ሌሎችም አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው በተነሳው ከፍተኛ ረሃብ የተነሳ  ቀያቸውን ጥለው ወደ መቀሌ፣ ሽሬ፣ አክሱምና ሁመራ መሰደዳቸውን ገልጸዋል። “አርሶደሮችን ሲያነጋግሩ ከፍተኛ ረሃብ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ ለሚገኙ መሪዎቻቸው ድግፋቸውን ገለጹ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ” ፍትህ ተነፍገንም ትግላችን አይቆምም” የሚል መፈክር በማንገብ  በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ፍትሃዊነት የማይታይበትን የፍርድ ሂደት አውግዘዋል። እጅግ በርካታ ህዝብ የተገኘበት  ተቃውሞ በሰላም ተጠናቋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በፓርላማ ቀርበው የሙስሊሙን እንቅስቃሴ መቆጣጠራቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጅ ተቃውሞው እንደገና እየተጠናከ መምጣቱን ባለፉት 2 ሳምንታት ...

Read More »

በባህርዳር ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከተማው አስተዳደር የቤት አፍራሽ ግብረሃይል በቀበሌ 13 በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል ያላቸውን ቤቶች ለማፍረስ በተንቀሳቀሰበት  ወቅት ከነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ቤት አፍራሽ ግብረሃይሎች ነዋሪዎች ዛሬውኑ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ሲጠይቋቸው፣ ነዋሪዎች  ” መጪው የአመት በአል ጊዜ ነው፣  ክረምትም እየመጣ ነው፣ ...

Read More »

ሩሲያ በዩክሬን ላይ በምትወስደው የነዳጅ ማቋረጥ እርምጃ የአውሮፓ አገሮች ችግር ላይ እንደሚወድቁ አሳሰቡ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ፑቲን ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ዩክሬን ያልከፈለችውን ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ ባለመክፈሉዋ ነው።የሩሲያ ታላቁ ነዳጅ ማከፋፈያ ድርጅት ጋዝ ፕሮም ዩክሬን በአስቸኳይ እዳዋን የማትከፍል ከሆነ የነዳጅ አቅርቦቷ ይቋረጥባታል። የዩክሬን የነዳጅ አቅርቦት መቋረጥ ከሲሶ በላይ የነዳጅ ፍጆታቸውን ከሩሲያ የሚያገኙት የአውሮፓ አገራት አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ። አሜሪካ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ የተቸች ሲሆን፣ የጀርመንና የፈረንሳይ ኩባንያዎች ደግሞ ጋዝ ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ በቦዴዎች ላይ በሰነዘረው ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አስታወቀ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በቦዴዎችና በኮንሶች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ ወደ 29 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለድርጅታቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የሟቾችን ስም ዝርዝር በማጠናቀር ላይ ሲሆኑ  ሰሞኑን ይፋ እንደሚያደርጉም ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል ሆስፒታል ...

Read More »

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ቀዳሚ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆነ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በ2005 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት ካገኘችው ገቢ ይበልጥ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በሐዋላ መልክ ያገኘችው ገቢ እንደሚበልጥ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ የጹሑፍ መረጃ አመልክቷል። መረጃው እንደሚያሳየው በ2005 በጀት ዓመት አገሪቱ ከኤክስፖርት 3.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከውጭ ከሚልኩት ገንዘብ ደግሞ 3 ቢሊዮን 9 መቶ ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ ...

Read More »