የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት መውረዱን ብሉም በርግ ዘገበ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ ብሄራዊ ስታትስቲክስን ጠቅሶ እንደዘገበው በሰኔ ወር ውስጥ የዋጋ ንረቱ ከ25 በመቶ ወደ 21 በመቶ ዝቅ ብሎአል። የምግብ ዋጋዎች በአንጻሩ ከአምናው ጋር ሲተያይ 21 በመቶ ከፍ ብሎአል። የአቶ መለስ መንግስት በሰኔ ወር የዋጋ ንረቱን ወደ አንድ አሀዝ እንደሚያወርደው ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጅ አቶ መለስ ይህን ማድረግ እንደማይቻል አምነው በመስከረም ወር ግሽበቱን ወደ አንድ ...

Read More »

ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ የመንግስትን አካሄድ እየተቃወመ ነው

ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመብት ጥያቄያቸውን እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማቅረብ ያለፉትን ስድስት ወራት ያሳለፉት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፣ መንግስት ጥያቄያቸውን ወደ ጎን በማለት አጠቃላይ ሂደቱን እሱ በሚፈልገው መንገድ ለማስተናገድ መሞከሩ ሙስሊሙን እያስቆጣ ነው። በትናንት የአርብ ጁምዓ ጸሎት በአንዋር መስኪድ እና ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጊድ የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መንግስት ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ ለማስተናገድ እየተጓዘበት ያለው መንገድ ችግሩን ከማወሳሰብ ...

Read More »

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከተከሰሱት ሰዎች በአራቱ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ

ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ አሰናብቷቸው የነበሩ አራት ተከሳሾች ላይ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ10 እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ ዛሬ አሳለፈ። የመንግስት አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ በነኚሁ አራት ግለሰቦች ላይ፣ ማለትም በ21ኛው ተከሳሽ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ በ12ኛ ተከሳሽ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፤ በ19ኛው ...

Read More »

አዲሱ የቴልኮም አዋጅ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን ሪፖርተር ዊዝ ዓውት ቦርደርስ ገለጠ

ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ድርጅት ትናንት ባወጣው ጽሁፍ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ሽመልስ ከማል  በኢንተርኔት የሚደረጉ የኢንተርኔት የስልክ ልውውጦችን አናግድም በማለት ቢናገሩም ተቀባይነቱ አጠራጣሪ ነው ብሎአል። ድርጅቱ እንደሚለው፣ የጸረ ሽብር ህጉ አሻሚ የሆኑ አንቀጾችን በመያዙ ጋዜጠኞችን ለማጥቂያነት መዋሉን በአስረጅነት የጠቀሰው ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ  ፣ አዲሱ የቴሌኮሙኒኬሽን አዋጅም ጋዜጠኞችን እና ሌሎች ወገኖችን ...

Read More »

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በሚካሄደው ኦሊምፒክ በ5 ሺ ሜትር ለመሳተፍ የሚያስቸለውን ሚኒማ ሳያሟላ ቀረ

ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት በፓሪስ ዲያመንድ ሊግ ላይ በ5 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፈው ቀነኒሳ በቀለ ፣ ውድድሩን በ5ኛነት በመጨረሱ በለንደን ኦሎምፒክ ላይ በዚሁ ርቀት አይሳተፍም። ቀነኒሳ ለሽንፈቱ መንስኤ ያደረገው በእግሩ ላይ የደረሰውን ጉዳት ነው። ” የእኔ ችግር ገና አሁን ከህመም አገግሜ መምጣቴ ነው። እያሻሻልኩ ነው። በለንደን በ10 ሺ ሜትር እሮጣለሁ። በ5 ሺ ሜትር ላይ ...

Read More »

በጎሳ ግጭት ከ40 በላይ ሰዎች አለቁ ግጭቱ እንደቀጠለ ነው

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን አሬሮ ወረዳ ውስጥ በገብራና በቦረና ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት እስካሁን ድረስ ከ40 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። ግጭ ቱ ዛሬ ድረስ የቀጠለ ሲሆን አድማሱን እያሰፋ መምጣቱንም የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። የአካባቢው ሰዎች እንደሚናገሩት በእስካሁኑ ግጭት የዛሬውን ሳይጨምር ከገብራ 21 ከቦረና ደግሞ 19 ሰዎች ተገድለዋል። በዛሬው እለትም የውጊያው አድማስ ሰፍቶ ሱልሉታ ወደሚባለው የያቬሎ ...

Read More »

የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት 9 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ገለጠ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው  የበሀይሌ ሊ/መንበር የሆኑት አቶ አሊ ማያቤ፣ የአካባቢው የጎሳ ተጠሪ የሆኑት አቶ ዳቶና ሙሀመድ ፣ አቶ አሊ ናስሪ ሙሀመድ፣ አቶ ኦማር ሀቴ፣ አቶ ዳውድ አሊ፣ አቶ ማያቢሄ ሞሀመድ፣ አቶ ካድር አስከሪ እና አቶ ሙሀመድ ኢጋሀሌ በፌደራል ፖሊስ ከተወሰዱ በሁዋላ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ድርጅቱ እንዳለው ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ...

Read More »

ጀርመናዊው የአዳማ ዩኒቨርስቲ ዲን ስራቸውን ለቀቁ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዳማ ዩኒቨርስቲን በጀርመን የትምህርት አደረጃጀት መሰረት ሞዴል ዩኒቨርስቲ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ተቋርጧል። ፕሮፌሰር ፒተር ላንግፊልድ የጀርመን መንግስት የውጭ ትምህርት ግንኙነት ( ዳድ) ግፊት ወደ ኢትዮጵያ ከሁለት አመት ከስድስት ወራት በፊት ቢያቀኑም፣ የሶስት አመት የኮንትራት ውላቸው እያለ ከዩኒቨርስቲው እንዲለቁ ተደርጓል። ከእርሳቸው ጋር አብረው የተጓዙ ሌሎች 5 ጀርመናዊያንም ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። መንግስት በምትካቸውም ...

Read More »

ፓርላማው በአቶ መለስ ዜናዊ ህመም ምክንያት የመዝጊያ ፕሮግራሙን አራዘመ

ሰኔ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-99 በመቶ የአንድ ፓርቲ አባላት የተሰባሰቡበትና በምሁራን ዘንድ ” እጅ አውጭ”  እየተባለ የሚጠራው ፓርላማ በሕገመንግስቱ ከተደነገገው ውጪ የስብሰባ ጊዜውን በአንድ ሳምንት ማራዘሙን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ፓርላማው በሕገመንግስቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ በተደነገገው መሰረት የዓመቱ ሥራው ተጠቃሎ የሚዘጋው ሰኔ 30 ቀን መሆኑን ደንግጓል፡፡ በየዓመቱ ለቀጣዩ ዓመት የሚቀርበው በጀት በም/ቤቱ አባላት ቀናት የወሰደ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፖርት ላይ ለመወያየት ሰሞኑን ወደ ጀኔቫ አምርተው የነበሩ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ተወቀሱ

ሰኔ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፖርት ላይ ለመወያዬት ሰሞኑን ወደ ጀኔቫ  አምርተው የነበሩ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፦“አካሄዳችሁ፤የፈራችሁትን የዓረብ ስፕሪንግ እዛው እቤታችሁ ድረስ ሰተት አድርጎ የሚያመጣ እንጂ፤መፍትሄ ሊሆናችሁ አይችልም” ተብለው ተወቀሱ። ባለስልጣናቱ ይህ ወቀሳ የተሰነዘረባቸው፤ባለፈው ሐሙስ በስዊዘርላንድ-ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ውስጥ፤ ሲቪኪዮስ -ለዜጎች ተሳትፎ ዓለማቀፋዊ ህብረት የተባለ ድርጅት-  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ...

Read More »