ከቅማንት ብሄረሰብ ጋር በተያያዘ የታሰሩት አሁንም አልተፈቱም

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ከቅማንት ብሄረሰብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩት 47 ሰዎች በፍትህ እጦት በእስር እየተንገላቱ መሆናቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል ፡፡ ባለፈው ወር የቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ከ13 ያላነሱ ሰዎች በግፍ ሲገደሉ  47 ሰዎች ደግሞ ታስረዋል።

ሰሞኑን በጎንደር ከተማ የብሄረሰብ ተወካዮችን ጠርተው  በጎንደር ሲኒማ አዳራሺ ያወያዩት የክልሉ ርዕሰ መሰተዳደድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በቅማንት ብሄረሰብ ላይ መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጀ አሳፋሪ ነው ያሉት ተወካዮች  የክልሉ ምክር ቤት እና የፌደሬሺን ምክር ቤት ለህብረተሰቡ ጥያቄ እውቅና መንፈጋቸውን ተወካዮች ተችተዋል።

መንግስት የንፁሃንን ደም በከንቱ በማፍሰስ እና በእስር በማንገላታት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲያቆም ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀራርበን ጥያቄ እንዳናሰማ የከተለከለበት ደብዳቤ ይነሳልን ሲሉም ተወካዮች ጠይቀዋል