180 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶች የአለም ባንክ አገራትን ከቢዝነስ አንጻር ማወዳደሩን እንዲያቆም ጠየቁ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ባወጣው ዘገባ ደሃ አገሮች “ቢዝነስ” ለመስራት ምቹ ናቸው ተብለው ደረጃ ውስጥ እንዲገቡ በማሰብ መሬታቸውን ለሃብታም አገራት ነጋዴዎች እያስረከቡ ነው።

አገሮች በአሜሪካ ባለስልጣናት አይን እየተገመገሙ ” ለቢስነዝ ስራ ምቹ ናቸው አይደሉም” እየተባሉ እንደሚመደቡ የገለጸው ኦክላንድ፣ በዚህም የተነሳ የደሃ አገር መንግስታት ሀብታሞችን ለማስደሰት ሲሉ ድሆችን እየጎዱ መሬትና ሌሎች ማእድናት እንዲዘረፉ እያደረጉ ነው።

ደሃ አገሮች በቡድን 8 አገራት መሬታቸውንና ሃብታቸውን መዘረፋቸው እንደሚቀጥል የሚገልጸው ድርጅቱ፣ አለም ባንክ ለድሆች መቆም ሲገባው ለሃብታሞች ዝርፊያ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ብሎአል።

የአለም ባንክ በቅርቡ አመታዊ ስብሰባውን ሲያደርግ ጥያቄ እንደሚቀርብ ተቋሙ አስታውቋል።