ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላዋካ አማራ የተባለዉ የ37 አመት ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊ የ32 አመት እድሜ ያላትን የሶስት ልጆቹን ወላጅ እናት በስለት ወግቶ በመግደል እራሱን ሰቅሎ እንዳጠፋ ሃሬትዝ የዜና ምንጭ ገለጿል። ከአምስት አመት በፊት ወደ እስራኤል የተጓዙት ሁለቱ የትዳር ጓደኞች በአንድ ትልቅ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ዉስጥ የሚሰሩ ሲሆን ለዚህ መጠፋፋት የደረሱበት የግጭት መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን አልተገለፀም። እድሜያቸዉ ...
Read More »ቀነኒሳ በቀለንና ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ ታዋቂ የኢትዮጵያ አትሌቶች ከውድድር ታገዱ
ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰለች መልካሙ ፣ ስለሺ ስህንና ሌሎች በአለማቀፍ ውድድሮች ከወርቅ እስከ ነሀስ ያገኙ አትሌቶች ከውድድር እንዲታገዱ የተደረገው በመጪው መጋቢት ወር በሚካሄደው አለማቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር እና ለለንደን ማራቶን ልምምድ እንዲያደርጉ ተጠይቀው በጊዜው ሪፖርት ለማድረግ ባለመቻላቸው ነው ተብሎአል። 35 አትሌቶችን በአንድ ጊዜ ሪፖርት አላደረጉም በሚል ማገድ አሳማኝ ሆኖ አልተገኘም። አትሌቶቹ ፕሮፌሽናል እንደመሆናቸው የወድድርና ...
Read More »የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ላይ የጥፋተኝተነት ብይን አስተላለፈ
ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በተከሰሱት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ላይ በዳኛ እንዳሻው አዳነ የተመራው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ ጋዘጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በ4 የሽብርተኝነት ክሶች ጥፋተኛ ተብሎአል። ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ አንድነት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ የነበረውን ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፣ መምህርትና የፍትህ ጋዜጠኛ አምደኛ የሆነችውን ርእዮት አለሙን እና ሂሩት ክፍሌን በሶስት ...
Read More »ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሽብር ፈጣሪው የኤርትራ መንግስት ላይ የማያዳግም ርምጃ ካልወሰደ የኢትዮጵያ መንግስት አስመራ ውስጥ ያለውን መንግስት የመከላከል ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል ሲል የመለስ መንግስት አስታወቀ
ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማበወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የኤርትራ መንግስት የሚያካሂዳቸውን የሽብር ድርጊቶችና ለአሸባሪዎች የሚሰጠውን እርዳታ መታገስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡፡ የኤርትራ መንግስት ያሰማራቸውአሸባሪዎች በአፋር ክልል የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በመጎበኘት ላይ በነበሩ 27 ቱሪስቶች ላይ ከትናንትበስቲያ ጥቃት ማድረሳቸውንና አምስቱ መገደላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል። የሽብር ጥቃቱ ከአንድ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ...
Read More »“የመኢአድ አባል የሆነ ሁሉ ይታሰራል እየተባለ ነው” ሲል መኢአድ ገለጸ
ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለየ መልኩ በደቡብ ክልል በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አባላት ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየከፋ በመምጣቱ ፤ የዘንድሮ ጠቅላላ ጉባኤውን እዚያው ክልል ውስጥ ለማድረግ መወሰኑን ፓርቲው አስታወቀ። መኢአድ በመግለጫው እንዳለው፤ ጠቅላላ ጉባዔውን በክልሉ ማካሄድ ያስፈለገው፤ በክልሉ በሚገኙ የድርጅቱ አባላት ላይ ኢህአዴግ የሚያደርሰው ጭቆና እየበረታ በመምጣቱ፤ ጭቆናውን በህጋዊ መንገድ እንዴት መግታት እንደሚቻል ውሳኔ ለማሳለፍ ...
Read More »የኢጋድ አባል አገራት “ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት “ መፈራረማቸውን ተከትሎ ኡጋንዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ
ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን የ ኢጋድ አባል አገራት “ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት “ መፈራረማቸውን ተከትሎ በተለይ በ ኡጋንዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ከፍ ያለ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ። በአቶ መለስ መንግስት ግንባር ቀደም ፊታውራሪነት ሁሉም የኢጋድ አገሮች እንዲፈረም ግፊት እየተደረገበት ያለውና ሥራ ላይ ለመዋል ጥቂት ሳምንታት የቀረው ይህ ስምምነት ዋነኛ ዓላማው፤ በጎረቤት አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችን ...
Read More »“ክዋክብት ኢንተርናሽናል” የተሰኘ አማካሪ ድርጅት ጋዜጣ የማሳተም ፈቃድ መከልከሉን ፍትህ ጋዜጣ ዘገበ የአቶ በረከት ግብረ-ሀይል የጋዜጣ ፈቃድ መስጠት አቁሜያለሁ አለ
ጥር 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት፤በሀገሪቱ የነፃ ጋዜጣ ህትመት ስራ ዙሪያ ረጅም ጊዜ የወሰደ ምልከታና ጥናት በማካሄድ በቅርቡ‹‹ርግብ›› በሚል ስያሜ ሳምንታዊ ጋዜጣ ለማሳተም አስፈላጊ ዝግጅቶችን አጠናቅቀው እና አስፈላጊ ነገሮችን አሟልተው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለማግኘትያቀረቡት ጥያቄ ከሁለት ወራት በላይ ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ፦” በቅድሚያ የድርጅቶቹን ባለቤቶች ማንነት ማጥናት አለብን”የሚል እንደሆነ ...
Read More »የአፋር ህዝብ ፓርቲ በአፋር ክልል በውጭ አገር ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ፣ የመንግስት እጅ ሳይኖርበት እንደመማይቀርም ገለጠ
ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ለኢሳት እንደተናገሩት በውጭ አገር ዜጎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ ፓርቲያቸው ያወግዘዋል። በኦጋዴን ክልል የኢትዮጵያ መንግስት በ9 ቻይናውያን እና ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ከ4 አመታት በፊት የተፈጸመውን ግድያ ምክንያት በማድረግ እስከዛሬ ድረስ አካባቢውን የጦር ቀጠና ማድረጉ ይታወቃል። በሰሞኑ ጥቃት 5 የጀርመን፣ የሀንጋሪና ኦስትሪያ ዜጎች ሲገደሉ፣ ሁለት የጀርመን፣ እንድ የኦስትሪያና ...
Read More »የኢትዮጵያ እና የኬንያ መንግስታት እንዲሁም የአለማቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ቀንድ ለረገፈው ከ50 እስከ 70 ሺ ለሚጠጋ ህዝብ ሞት ተጠያቂ ናቸው ተባለ
ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኦክስፋምና ሴቭ ዘችልድረን በጋራ ባወጡት መግለጫ አምና በተከሰተው ረሀብ እስከ 70 ሺ የሚጠጋ ህዝብ ረግፏል። የአለማቀፉ ማህበረሰብ ጥያቄ ሲቀርብለት ፈጥኖ መለስ ቢሰጥ ኖሮ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያና የኬንያ መንግስታት ረሀብ የለም በማለት ችግሩን ለመሸፋፋን መሞከራቸው ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የለም አንድም የሞተ ሰው የለም ብለው መናገራቸው ይታወሳል። ከቢቢሲ ዘገባ ለመረዳት እንደሚቻለው የኬንያ ...
Read More »50 ሺህ የ ኦሮሞ ተወላጆች በራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ ጥያቄ በማቅረባቸው ለ እስራትና ለተለያዩ በደሎች መጋለጣቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ገለጠ
ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ( ኢሰመጉ) የሚለውን ስያሜውን በመንግስት ጫና ወደ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ለመለወጥ የተገደደው ብቸኛው የኢትዮጵያ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሰሞኑን ባወጣቸው ሁለት ልዩ መግለጫዎች፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን አጋልጧል ። ሰመጉ በ118ኛ እና በ119ኛ ልዩ መግለጫው የተፈፀሙትን የመብት ጥሰቶች በስፋት በመዘርዘርም፤ የእርምት እርምጃ እንዲወስድባቸው ለሚመለከታቸው መንግስታዊና ...
Read More »