የኢትዮጵያ እና የኬንያ መንግስታት እንዲሁም የአለማቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ቀንድ ለረገፈው ከ50 እስከ 70 ሺ ለሚጠጋ ህዝብ ሞት ተጠያቂ ናቸው ተባለ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-ኦክስፋምና ሴቭ ዘችልድረን በጋራ ባወጡት መግለጫ አምና በተከሰተው ረሀብ እስከ 70 ሺ የሚጠጋ ህዝብ ረግፏል።

የአለማቀፉ ማህበረሰብ ጥያቄ ሲቀርብለት ፈጥኖ መለስ ቢሰጥ ኖሮ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያና የኬንያ መንግስታት  ረሀብ የለም በማለት ችግሩን ለመሸፋፋን መሞከራቸው  ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።

አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የለም አንድም የሞተ ሰው የለም ብለው መናገራቸው ይታወሳል።

ከቢቢሲ ዘገባ  ለመረዳት እንደሚቻለው የኬንያ መንግስት እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳይደገም ትምህርት መውሰዱንና ከኖርዌይና ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራርሞአል።

የአቶ መለስ መንግስት 11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አምጥቻለሁ ቢልም አሁንም በሺ ዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በርሀብ መርገፋቸውን አላቆሙም።

የሁለቱ ድርጀቶች ዘገባ አብዛኛው ህዝብ በረሀብ ያለቀው በኢትዮጵያ ፣ ሶማሊያና ኬንያ መሆኑን አመልክቷል።

ኤርትራ ኢኮኖሚዋ የደቀቀ፣ ልትፈርስ የተቃረበች አገር ናት የሚል መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ የሚቀርብ ቢሆንም፣ ኤርትራ ረሀብ ያልገባባትና ሰዎም ያልረገፈባት መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።