ለከፍተኛ ስልጠና ወደ እስራኤል የተላኩ ስምንት የኢትዮጵያ ወታደሮች በኤርትራ ጥገኝነት መጠየቃቸውን “ሀሬትዝ” የተሰኘው የእስራኤል ጋዜጣ ዘገበ

ታህሳስ 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል ራዲዮ ያሰራጨውን ዜና በመጥቀስ ጋዜጣው እንደዘገበው፤ ስምንቱ የ ኢትዮጵያ ወታደሮች ለስልጠና ወደ እስራኤል የመጡት ከሶስት ወራት በፊት ሲሆን፤ከሶስት ቀናት በፊት ከማሰልጠኛ ቤዛቸው ጠፍተዋል። በእስራኤል የኤርትራ አምባሳደር አቶ ተስፋማርያም ተከስተ ፤ወታደሮቹ ባለፈው ሀሙስ ወደ እርሳቸው መኖሪያ ቤት በመምጣት  በኤርትራ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ለ እስራኤል ራዲዮ ገልፀዋል። እንደ ራዲዮው ዘገባ ከስምንቱ ወታደሮች ሦስቱ ...

Read More »

በወሎ እና በአፋር ድንበር በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት- አንድ ሰው መገደሉንና 45 ቤቶች መቃጠላቸውን፤ ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ

ታህሳስ 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ጋዜጣው ዘገባ ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ልዩ ቦታው ቀበሌ 014 በሚባለው የድንበር ቀበሌ ውስጥ በወሎየዎችና በአፋሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት አንድ ሰው ሲሞት፤ 45 ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን፤በርካታ ከብቶችና ግመሎች መሞታቸውና ንብረቶች መውደማቸውም ተመልክቷል፡፡ ይሁንና የሞተው አንድ ሰው ከየት ወገን እንደሆነና የተቃጠሉት ቤቶችም የነ ማን እንደሆኑ ጋዜጣው በዝርዝር የገለጸው ነገር የለም። ስለተፈጠረው ግጭት በጋዜጠኖች ...

Read More »

መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት መንገሱን የደህንነት ምንጮች ገለጡ

ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግንባሩ መተካካት እና የብሄር ተዋጽኦን ለማመጣጠን በሚል ሰበብ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን ማባረሩን ተከትሎ የመጣ ነው። የኢሳት የደህንነት ምንጮች እንደዘገቡት ሰሞኑን 6 ጄኔራሎችና ከ120 በላይ የኮሎኔልነት ማእረግ ያላቸው መኮንኖች ተባረዋል። የተባረሩት ጄኔራሎች   ሁለቱ የትግራይ ፣ 3 የአማራ እና አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። በደራሲ ተስፋየ ገብረአብ መጽሀፍ በዳንስ ...

Read More »

በአቶ መለስ ሽብርተኞች ናቸው ተብለው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሲዊዲናዊያኑ ጋዜጠኞች የ11 ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈረደባቸው

ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ መለስ መንግሥት ሽብርተኞች ናቸው ተብለው በቁጥጥር ሥር  የዋሉት ሲዊዲናዊያኑ ጋዜጠኞች መርቲን ካርል ሽብየ እና ፎቶ ጋዜጠኛ ጁሃን ከርል ፐርሰን ዛሬ ጠዋት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት የ አሥራ አንድ (11) ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈረደባቸው፡፡ በፍርድ ውሳኔው የተበሳጩት የሲዊዲን አምባሳደር የፍርድ ሂደቱ በሚነበብበት ጊዜ ችሎቱን ረግጠው አቋርጠው ወጥተዋል፣ ወደ ችሎት አዳራሽ በግድ ሊመልሳቸው ...

Read More »

በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት በዐቃቤ- ሕግ ጥያቄ ዛሬ ሳይካሄድ ቀረ

ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባል የማጠቃለያ የክርክር ማቆሚያ በዐቃቤ- ሕግ ጥያቄ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሳይካሄድ ቀረ፡ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛና መምህርት ርዮት ዓለሙ፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚሃብሄር ...

Read More »

ኢትዮጵያ በብልጽግናና ደስታ ከአለም ከመጨረሻዎቹ ሶስት አገሮች አንዷ ሆነች

ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሲኤን ኤን ሊጋተም ፕሮስፐርቲ ኢንዴክስን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በአለም ላይ ደስታ የሚባል ነገር ከጠፋባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ዝምባብዌና ማእከላዊ አፍሪካ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል። ኖርዌይ፣ ዴንማርክና አውስትራሊያ ደግሞ በደስታ ብዛት ከአንድ እስከ ሶስት ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል። ኢትዮጵያ የመጨረሻውን ደረጃ የያዘቸው በአገሪቱ ውስጥ በተንሰራፋው ስራ አጥነት፣ የመብት አፈናና የማህበራዊ አግልግሎት ችግር ነው። ከህዝቡ ሲሶ የሚሆነው እንኳ በስልጣን ...

Read More »

በደቡብ ክልል በተጀመረው ግምገማ በርካታ ሰዎች ከስልጣናቸው እየተነሱ ነው፤ የየኔሰውን ታሪክ ለማበላሸት ከፍተኛውን ስራ የሰራው ከስልጣኑ ተነስቷል

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ በተጀመረ ግምገማ ፣ ከ5 0 ያላነሱ ሰዎች በሙስና ሰበብ ተባረዋል። የግምገማው ዋነኛ ነጥብ በዳውሮ ዞን በዋካ ከተማ ከተነሳው ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ የፌደራሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ መረጃው በአለም እንዲሰራጭ በማድረግ በኩል እጃቸው አለበት ብሎ የጠረጠራቸውን ባለስልጣናት በማባረር በአዲስ ሰዎች እየተካ ነው። የመባረር እጣው ከደረሳቸው ባለስልጣናት መካከል የደቡብ ክልል የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ የነበሩት አቶ ...

Read More »

በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚደረገው ቅነሳ ሁለት ብሄሮችን ማእከል ያደረገ ነው ሲሉ የሰራዊት አባላት ገለጡ

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አባላት ለኢሳት የአዲስ አበባ ወኪል እንደገለጡት በሰራዊቱ ውስጥ፣ የብሄር ተዋጽኦን ለመቀነስ ተብሎ እየተወሰደ ባለው እርምጃ እንዲቀነሱ የሚደረጉት በብዛት የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ናቸው። የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ የሰራዊቱን የብሄር ተዋጽኦ ለመጠበቅ መንግስት የማመጣጠን ስራ እየሰራ ነው በማለት ለፓርላማ መናገራቸው ተከትሎ፣ አባላቱ እንደገለጡት፣ የሰራዊቱን ተዋጽኦ ለማስተካካል በሚል ሽፋን አገዛዙን ...

Read More »

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ንብረት አውድመዋል የተባሉ 52 ተማሪዎች ተቀጡ

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተማሪዎች እርምጃ የተወሰደባቸው በግቢው ውስጥ ተከስቶ የነበረውን በሽታ ምክንያት በማድረግ ረብሻ አስነስተዋል ተብሎ ነው። ከ50 ተማሪዎች ውስጥ 22ቱ በአንደኛ ደረጃ ጥፋተኝነት ተፈርጀው ለአንድ ዓመት ከትምህርታቸው እንዲገለሉ ሲደረግ ፣ 18ቱ ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ተማሪዎች ላወደሙት ንብረት ተጠያቂ እንደሆኑና እንዲከፍሉ ታዘዋል። ገንዘቡን ካልከፈሉ የትምህርት ማስረጃቸው የማይሰጣቸው ሲሆን፣ ከዚህ በኋላም በማንኛውም ዓይነት ጥፋት ውስጥ ቢሳተፉ ያለምንም ...

Read More »

የግብጽ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ ልኡካን በአባይ ግድብ ዙሪያ ለመምከር በካይሮ ተሰብስበዋል

ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስብሰባው የሚካሄደው በግብጽ የውሃና መስኖ ልማት ሚኒሰትር ሂሻም ቃንዲል፣ በኢትዮጵያ የውና ሀይል ልማት ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ እና በሱዳኑ የመስኖና ውሀ ልማት ሚኒሰትር ካሚል አሊ ሙሀመድ ጋር ኔቬምበር 29 ተደርጎ በነበረው ስምምነት መሰረት ነው። በስብሰባው ላይ ከሶስቱም አገሮች የተውጣጡ ኤክሰፐርቶች ይሳተፋሉ ተብሎአል። ስብሰባው የአባይን ግድብ በማስቀጠልና ባለማስቀጠል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የመለስ መንግስት አዲስ ...

Read More »