በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የወሰደውን እርምጃ እንደደገፉት ዘጋቢያችን ገለጠ

ጥር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባው ወኪላችን እንደገለጠው፣ በርካታ የኦሮሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጄነራል ከማል የሚመራው ኦነግ፣ የመገንጠል አጀንዳን ሰርዞ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት አሳዛኝ ሁኔታ አላቆ፣ አገሪቱዋን ለመምራት የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል። ለደህንነቱ ሲባል ስሙን መግለጽ ያልፈለገ አንድ የኦነግ ደጋፊ እንደገለጠው ፤ አለም ወደ አንድ እየተቀራረበች በመጣችበት ጊዜ እና በአሁኑ አለም ህልውናን ጠብቆ ለመኖር አንድነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ...

Read More »

በአፋር ክልል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኡመድ አፋሶ አሊ፤ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው በዋስ መፈታታቸው ተዘገበ

ጥር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፋር ክልል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ  ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኡመድ አፋሶ አሊ፤ ከሚኖሩበት አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ- አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው  በ5 ሺህ ብር ዋስ መፈታታቸውን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ።   ከድርጅቱ ጽ/ቤት የደረሰውን መረጃ በመጥቀስ ጋዜጣው እንደዘገበው አቶ ኡመድ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱት ባለፈው ቅዳሜ ነው።  አቶ ኡመድ፦“ ለምንድነው ያሰራችሁኝ?” በማለት ...

Read More »

በደሴ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ሙስሊሞች የአህበሻን አስተምህሮ፣ የመንግስትን ጣልቃ ገብነትና መጅሊሱን ተቃወሙ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በከተማዋ የሚኖሩ ሙስሊሞች በዋናው መስጊድ ግቢ በመገኘት መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም፣ መጅሊሱ ወይም የእስልምና ጉባኤው ሙስሊሙን የማይወክል በመሆኑ እንዲፈርስ እንዲሁም የአህባሽ አስተምህሮ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል። የመንግስት ባላስልጣናት ሙስሊሞቹ ተወካዮቻቸውን መርጠው እንዲነጋገሩ ባሳሰቡት መሰረት 50 ተወካዮች ከሰአት በሁዋላ የዜን የጸጥታ ሀላፊ፣ የዞን አስተዳዳሪ፣ የደሴ ከተማ እና ሌሎችም 9 ባለስልጣኖች ባሉበት ውይይት ተካሂዷል። የዞኑ ...

Read More »

አልሸባብ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶማሊያ ታጣቂ ሀይል የሆነው አልሸባብ እንደገለጠው ጥቃቱን የፈጸመው በለደወይን እየተባለች በምትጠራ የሶማሊያ ግዛት ነው። የኢትዮጵያ ጦር ባለፈው ወር ከተማዋን ከአልሸባብ በመንጠቅ የተቆጣጠራት ሲሆን፣ ለአፍሪካ ህብረት ሰራዊት ለማስረከብ በዝግጅት ላይ ነበር። ታጣቂ ሀይሉ ጥቃቱን የፈጸመው አንድ አጥፍቶ ጠፊ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሰፈሩበት ካምፕ በመሄድ በፈጸመው ጥቃት ነው። የአይን እማኞች እንዳሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች የሚኖሩበት ህንጻ ክፍሎች ...

Read More »

የእስራኤል ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዉያን የዘፈን ግጥም ደረሱ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያዊ  ቤተ እስራኤላዉያን ላይ የደረሰዉ የዘር መድልዎ የተሰማቸዉ የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሺሞን ፔሬዝ አንድ የዘፈን ግጥም በመድረስ እዉቁ የእስራኤል የዜማ ደራሲ እንዲያቀናብረዉ ማድረጋቸዉን አንድ የእስራኤል ጋዜጣ ገለፀ። ፕሬዝዳንቱ ግጥሙን ያዘጋጁት በቅርቡ በእየሩሳሌም በሚገኝ ትምህርት ቤት ዉስጥ ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያዊያን ሕፃናት እስራኤላዊ ከሆኑ የህብረተሰቡ ህፃናት ጋር ያላቸዉ የቅርብ ትስስርና ዉህደት በመመልከታቸዉ ነዉ። በተለይም የ8ኛ ክፍል ተማሪ ...

Read More »

ግዳጃቸዉን የፈፀሙ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደል እንደደረሰባቸዉ ገለፁ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በአዋሳ ከተማ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ግዳጃቸዉን ፈጽመዉ በክብር የተሰናበቱ ተራ ወታደሮች ወደ ትውልድ ስፍራቸዉ ተመልሰዉ የቤት መስሪያ ቦታ ወይንም የኮንዶሚኒየም ቤት ለመግዛት ቅድሚያ እንዲሰጣቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ በክልሉ ባለስልጣናት ተቀባይነት ማጣቱን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በሰፈረ ብሶት ተገለፀ።  የክልሉ መስተዳድር፤ የክልሉ ቤቶች የልማት ኤጀንሲ፤ የቤቶች ልማት ቦርድ የወታደሮቹን ጥያቄ ዉድቅ አድርገዉ በምትኩ   የኮንዶሚኒየሙ ቤት ...

Read More »

መንግሥት በነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በከሰሳቸው ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ብይን የመስጠት ሂደቱን ለሌላ ጊዜ አሻገረ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት መንግሥት በነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል በከሰሳቸው የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ብይን የመስጠት  ሂደቱን በጊዜ አሻገረ፡፡ ዛሬ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ የነ አንዷለም አራጌን የክስ መዝገብ ተመልክቶ የጥፋተኝነት ወይም ከጥፋት ነፃ የመሆን ብይን ይሰጣል ተብሎ ...

Read More »

አርዱፍ 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ( አርዱፍ) 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል። የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን በመጥቀስ ረዩተርስ እንደዘገበው፤ ቱርስቶቹ የተገዱለት በኢትዮጵያ ወታደሮች ነው በማለት ግንባሩ ለሟቾቹ የ ኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል። በአካባቢው የአርዱፍ ግብረሀይል ቅኝት በማድረግ ላይ ሳለም፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት እንደተከፈተበት -ግንባሩ ገልጧል። በተኩሱ ልውውጥ መሀል ...

Read More »

የአቶ መለስ መንግስት ኤርትራን ለመውጋት እየተዘጋጀ ነው ሲል ደብረብርሀን ብሎግ ዘገበ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ብሎጉ እንደዘገበው ፤ሰሞኑን የመከላከያ ኢንጄነሪንግ ኮሌጅ ሲቪል ሰራተኞች በግዴታ እረፍት እንዲወስዱ ታዘዋል። ብሎጉ በማያያዝም፦”ለተለያዩ የኮሌጁ ሰራተኞችም የደሞዝ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የሚከሰቱት አገሪቱ ለጦርነት ስትዘጋጅ ነው”ሲል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። በሌላ በኩል መንግስት አንዳንድ የአዲስ አበባ የቀበሌ ነዋሪዎችን ኤርትራ በወሰደችው እርምጃ ዙሪያ እያወያየ ነው። የአፋር ህዝብ ባወጣው መግለጫ ደግሞ መንግስት ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሁዋላ ...

Read More »

“የሰብኣዊ መብት ሁኔታና ኢትዮጵያ የምትጫወተዉ አፍራሽ ሚና “ በሚል ርዕስ በለንደን ኮንፈረንስ ተካሄደ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ያለዉ የምስራቅ አፍሪቃ የሰብኣዊ መብት ሁኔታና ኢትዮጵያ የምትጫወተዉ አፍራሽ ሚና “ በሚል ርዕስ በለንደን ኮንፈረንስ ተካሄደ በምስራቅ አፍሪቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ ይበልጥ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ባለዉ የሰብኣዊ መብት ሁኔታና በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የጠ/ሚር መለስ ዜናዊ መንግሰት የሚከተለዉ የተሳሳተ አቅጣጫ በአፍሪቃ ቀንድ ያለዉን ችግር እንዳወሳሰበው በስብሰባው ተገልጧል። በለንደን የአምነስቲ ...

Read More »