ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በደረሰባቸው የሀይል ጥቃት የተነሳ ወደ ኦሮሚያ ክልል መሰደዳቸውን የገለጡ 80 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ በቂ የሆነ የምግብ እርዳታ ስላልቀረበላቸው በቀን አራትና አምስት ሰዎች እየሞቱባቸው እንደሆነ ተናገሩ። ቁጥራቸው ከ300 ሺሕ በላይ የሆነውና በሶማሌ ክልል ይኖሩ የነበሩት የፊቅ ዑመር ወይም የሸካሽ ጎሳ ማኅበረሰብ አባላት በቂ እህልና ውሀ እንዲቀርብላቸው በተደጋጋሚ መንግስትን ሲጠይቁ ቆይተዋል። ...
Read More »በኦሮሚያና በሶማሊ ክልሎች በመጪዎቹ ስድስት ወራት ከፍተኛ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ
ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ብሎአል። የአለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው መንግስት አሁንም የተረጂዎችን ቁጥር ቀንሶ አቅርቧል ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው ቅድመ ማስጠንቀቂያ አሀዝ እንደሚያሳየው በመጪዎቹ ስድስት ወራት ከ365 ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ አብዛኛው በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልሎች የሚከፋፋል ነው ብሎአል። ከተረጅዎች ውስጥ ...
Read More »በአለፈው አመት ከመንግስት አልባዋ ሶማሊያ ይልቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ተሰደዋል
ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት አልባዋ ሶማሊያ ለአለፉት 10 አመታት ስደተኞችን በማምረት በኩል የሚስተካካላት አልነበረም፡ አሁን ግን ይህን ሪኮርድ ኢትዮጵያ ውስዳለች። ረዩተር ባወጣው ዘገባ በአሳለፍነው የፈረንጆች አመት በሪከርድነት የተመዘገበ 103 ሺ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን በሰላም እጦት አደጋ ውስጥ ወዳለችው የመን አቀንተዋል። ከእነዚህ ስደተኞች መካከል ከአራቱ እጅ ሶስቱ ወይም ከ77 ሺ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊ ቀሪዎቹ 25 ሺ ደግሞ ሶማሊያውያን ...
Read More »ኦብነግ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የሚያደርሱት ወቅታዊ ጥቃት ተከላከልኩ ሲል አስታወቀ
ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ወታደራዊ መግለጫ እንደማለከተው የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በየወቅቱ የሚያደርጉትን ህዝቡን የማስፈራራትና ማዋከብ ዘመቻ ጀምረዋል። በዋርዴር ቀብሪ ደሀርና ደገሀቡር አካባቢዎች የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የአካባቢውን እያመሰነ ነው ሲል ገልጧል። ግንባሩ ሂጋን በተባለው አካባቢ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ባደረገው የተኩስ ልውጥጥ 50 ገድሎ 70 ማቁሰሉን ገልጧል። 5 ቢኬኤም ከባድ ጠመንጃዎችን፣ 40 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ከወታደሮች ...
Read More »በ35 አትሌቶች ላይ የወሰደው የእግድ እርምጃ ለአመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮች ለማስተንፈስ ተብሎ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ተናገረ
ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ35 አትሌቶች ላይ የወሰደው የእግድ እርምጃ ለአመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮች ለማስተንፈስ ተብሎ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል አንድ ታዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛና ተንታኝ ተናገረ በስፖርት ተንታኝነቱ የሚታወቀው ኤርምያስ አማረ ለኢሳት እንደገለጠው በኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚታዩት ችግሮች ለረጅም ጊዜ የዘለቁና ሲሸፋፈኑ የቆዩ ናቸው። ኤርምያስ ወና ዋና ችግሮች የሚላቸው ፌደሬሽኑን፣ አትሌቶችንና አሰልጣኞችን የሚመለከቱ ናቸው የአትሌቲክስ ...
Read More »ESAT News analysis 20 January 2012-Ethiopia
በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየአመቱ ከጥር 10 እስከ ጥር 11 በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። ታቦታቱ በአዲስ አበባ በ16 ቦታዎች ያደሩ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ከቅዱስ ሚካኤል ታቦት በስተቀር ሁሉም ወደ መጡበት ተመልሰዋል። በጎንደር በአሉ የካርኒባል በአል የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለአንድ ሳምንት እንደሚከበር ታወቋል።
Read More »በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መጅሊሱ እንዲፈርስ ምርጫ እንዲደረግ በድጋሜ ጠየቁ
ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወልያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም በተባለው በዛሬው የስግደት ቀን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተዋል። ሙስሊሞቹ መጅሊስ ይፍረስ፣ ሙስሊሙ የራሱን አመራር ይምረጥ፣ አወልያ ኮሌጅ ይከፈት፣ አህባሽ ከአገራችን ይውጣ፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር፣ እስልምና የሰላም ሀይማኖት ነው፣ እስልምና አሸባሪ አይደለም እና የመሳሰሉትን መፈክሮች አሰምተዋል። የአወልያ መስጊድ ግቢ በመጥበቡ ህዝቡ ከግቢው ውጭ ሲሰግድ መዋሉን በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። በሙስሊሙ ...
Read More »በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸዉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ጥፋተኛ መባላቸውን የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች እያወገዙት ነው
ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ተጠርጥረው በታሰሩት 3 ጋዜጠኞች ፣ ሁለት የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባልና ደጋፊ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት የጥፋነተኝነት ብይን መስጠቱ ይታወሳል ። በሌለበት ብይኑ የተላለፈበትን የEthiopian Review ድረ ገፅ ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌን ጨምሮ፤ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ፤ በቅርቡ ከህትመት የወጣዉ የሳምንታዊው አውራምባ ታይምስ ...
Read More »በሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደሮች ተሽከርካሪ ላይ የቦምብ ፍንዳታ ደረሰ
ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማእከላዊ ሶማሊያ ባላዲወይኒ ሂራን የኢትዮጵያ ወታደሮችን ባሳፈረ ተሽከርካሪ ላይ በቅርብ ርቀት መቆጣጠሪያ / ሪሞት ኮንትሮል/ የተቀሰቀሰ የቦንብ ፍንዳታ መድረሱን ሸበሌ ሚዲያ ኔት ወርክ የዜና ወኪል ገለጸ። በተሽከርካሪዉ ላይ በተጫኑት የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ የተገለፀ ሲሆን ፍንዳታዉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአካባቢዉ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎችን ሲገድሉ አምስት ሰዎችን ማቁሰላቸዉን ...
Read More »