በ35 አትሌቶች ላይ የወሰደው የእግድ እርምጃ ለአመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮች ለማስተንፈስ ተብሎ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ተናገረ

ጥር 12 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ35 አትሌቶች ላይ የወሰደው የእግድ እርምጃ ለአመታት ሲንከባለሉ የቆዩትን ችግሮች ለማስተንፈስ ተብሎ  የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል አንድ ታዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛና ተንታኝ ተናገረ

በስፖርት ተንታኝነቱ የሚታወቀው ኤርምያስ አማረ ለኢሳት እንደገለጠው በኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚታዩት ችግሮች ለረጅም ጊዜ የዘለቁና ሲሸፋፈኑ የቆዩ ናቸው።

ኤርምያስ ወና ዋና ችግሮች የሚላቸው ፌደሬሽኑን፣ አትሌቶችንና አሰልጣኞችን የሚመለከቱ ናቸው

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ በአትሌቶቹ ላይ የወደው እርምጃ የፈጠነ ቢሆንም፣ አትሌቶቹን ለረጅም ጊዜ አግዶ ለማቆየት የሚቻል አይመስለኝም ሲል ኤርምያስ አክሏል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወሰደው እርምጃ የተበሳጨው ቀነኒሳ በቀለ፣ እኔ መመሪያ ጥሼ አላውቅም ካልፈለጉኝ በሌላ አገር ስም እሮጣሉ ብሎ መናገሩን ማኔጀሩን ጆስ ሄርመንስን ጠቅሶ ኢንሳይድ ዘ ጌምስ ለተባለው የማህበራዊ መረብ ገልጠዋል፤፡ ኢሳት ይህን አስተያየት ለማረጋገጥ አልቻለም።