በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መጅሊሱ እንዲፈርስ ምርጫ እንዲደረግ በድጋሜ ጠየቁ

ጥር 11 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-በአወልያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም በተባለው በዛሬው የስግደት ቀን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተዋል።

ሙስሊሞቹ መጅሊስ ይፍረስ፣ ሙስሊሙ የራሱን አመራር ይምረጥ፣ አወልያ ኮሌጅ ይከፈት፣ አህባሽ ከአገራችን ይውጣ፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር፣ እስልምና የሰላም ሀይማኖት ነው፣ እስልምና አሸባሪ አይደለም እና የመሳሰሉትን መፈክሮች አሰምተዋል።

የአወልያ መስጊድ ግቢ በመጥበቡ ህዝቡ ከግቢው ውጭ ሲሰግድ መዋሉን በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል።

በሙስሊሙ ውስጥ ከበሬታ ያላቸው በአፍሪካ ቴሌቪዥን እንግድነት ዝግጅት የሚያቀርቡት ታዋቂ ተንታኞቹ በድሩ ከማል፣ ያሲን ኑሩና  አቡበክር በአወልያ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

የፌደራል ፖሊስ አባላት አካባቢውን መክበባቸውን ወኪላችን አክሎ ዘግቧል። ሙስሊሞቹ ጥያቄዎቻችን መልስ የማያገኙ ከሆነ፣ በሚቀጥለው ሳምንትም ከዚህ የበለጠ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

መንግስት ቀደም ብሎ የአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች ያነሱትን ጥያቄ በከፊል በሚልስም ዋናውን መጅሊሱ ይፍረስ፣ የአህባሽ አስተምህሮ ይቁም፣ ሙስሊሙ በመረጠው የእስልምና መሪ ይተዳደር የሚለውን አልመለሰም።