ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደቡብ ሱዳንን ለመዉጋት ከሚያደርጉት ችኮላ እንዲቆጠቡና ሌሎችም ወታደራዊና ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን እንዲያደርጉ ለአልበሽርና ለመከላከያ ሚነስትራቸዉ ፣ ለአብዱል ረህማን መሃመድ ሁሴን ማስጠንቀቂያዉን የሰጡት ፣ ቁጥራቸዉ 700 የሚሆኑ የሱዳን የጦር ሃይል መኮንኖች እንደሆኑ ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘግቧል። ከደቡብ ሱዳን ጋር ባለ ችግር ምክንያት ወደ ጦርነት ሊገቡ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንቱና የመከላከያ ሚኒስትሩ ለጦር መኮንኖቹ ገለፃ ባደረጉበት ወቅት ፣ መኮንኖቹ ...
Read More »ሰሞኑን የምግብና ሌሎች የምግብ ነክ እቃዎች ዋጋ ማሻቀቡን ዘጋቢዎቻችን ገለጡ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደገለጡት በጥር ወር ጤፍ በተለምዶ የሚቀንስ ቢሆንም፣ በዚህ አመት ግን ይህ አልሆነም። ሰሞኑን በምግብ እህል ላይ ከ50 ብር ያላነሰ ጭማሪ ታይቷል። የጤፍ ዋጋ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተማዎችም ከ950 ጀምሮ በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ1 ሺ 100 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ነው። ወትሮውኑ በቆሎ እስከ 400 ብር በመሸጥ ላይ ...
Read More »የምርጫ ቦርድ፤ የአዋጁን መመዘኛ አሟልተው በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት ብቻ ናቸው አለ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ፤ የአዋጁን መመዘኛ አሟልተው በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት ብቻ ናቸው። እነሱም ኢህአዴግና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ብቻ ናቸው” ሲል ሌሎቹን ፓርቲዎች አስጠነቀቀ። የኢህአዴግ ታማኝ ተቃዋሚዎችን ብቻ ያካተተ የውይይት የክርክር መድረክ መዘጋጀቱ፤ተቃውሞ አስነሳ። “በምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ፣ የማደራጀት፣ የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመደገፍ ኃላፊነት አለኝ”ያለው ምርጫ ቦርድ፤ ብዙዎቹ ...
Read More »ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሶስተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ገለጠ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መግለጫ ፤ በኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በውጭ አገራት ውስጥ በአፍሪቃ፣ በአውስትራሊያ፣ በሩቅና መካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አባሎቹ ከጥር 12 ቀን እስከ 19 ድረስ ባደረጉት ሶስተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የንቅናቀያቸውን ሪፖርቶች አዳምጠው በጥንካሬዎችና ድክመቶች ላይ ግልጽና ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጧል። ግንቦት 7 ለኢትዮጵያዊያን ተስፋን የፈነጠቀ፤ በወያኔ ላይ ደግሞ ስጋትን ያሰፈነ ድርጅት መሆን ...
Read More »ኒኮላስ ዲ ክርስቶፍ መለስ ዜናዊ በወሰደው የጭካኔ እርምጃ የዓለምን የመገናኛ ብዙሀን ትኩረት የበለጠ ከመሳብ ውጭ ጸጥ ሊያሰኝ አይችልም አለ
ጥር 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የዘ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አምደኛ የሆነው ኒኮላስ ዲ ክርስቶፍ መለስ ዜናዊ በስዊድን፣ አሜሪካና ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ በወሰደው የጭካኔ እርምጃ የአለምን የመገናኛ ብዙሀን ትኩረት የበለጠ ከመሳብ ውጭ ጸጥ ሊያሰኝ አይችልም ብሎአል። ኒኮላስ ዲ ክርስቶፍ እንደጻፈው አስቀያሚ በሆነው የኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ ቅማል፣ ቁንጫና አይጥ በሞላበት እስር ቤት ውስጥ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብየ እና ጋዜጠኛ ጆን ...
Read More »የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራቸውን በገፍ መልቀቅ ያሳሰበው መንግስት ጥለው የሚጠፉ ፖሊሶችን ማሰር ጀመረ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከታማኝ የፌደራል ፖሊስ ምንጮች ባገኘነው መረጃ በመላ አገሪቱ የሚገኙ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራቸውን እየለቀቁ ነው። ባለፈው ወር ብቻ ከ100 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራ መልቀቃቸው ያስደነገጠው መንግስት፣ ያለፈቃድ ጥለው የሚጠፉትን እያደነ በማሰር ላይ ነው። ምንም እንኳ በትክክል የታሰሩ ፖሊሶችን ቁጥር ማግኘት ባይቻልም፣ በእየ ክፍለሀገሩና በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች ታስረው ...
Read More »የሶማሊንና የኦሮሚያን የክልል መንግስታት እያወዛገበ ያለው የሞያሌን ከተማ እና አካባቢውን አስተዳደር በፌደራል መንግስቱ ስር ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶማሊንና የኦሮሚያን የክልል መንግስታት እያወዛገበ ያለውና በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በርካታ ዜጎች ለሞትና ለስደት የሚዳረጉበትን የሞያሌን ከተማ እና አካባቢውን አስተዳደር በፌደራል መንግስቱ ስር ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ:: የኢሳት የሞያሌ ምንጮች እንደገለጡት ከወራት በፊት በሶማሊና በኦሮሚያ ብሄሮች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መጠን የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ተሰማርቷል። በአሁኑ ጊዜም በቦረና እና በገሪ ጎሳዎች መካከል ...
Read More »የኢህአዴግ አባልነታቸውን አነፈልግም ብለው ከለቀቁ በሁዋላ ወደ መኢአደ የገቡ 21 የቀደሞ የ ኢህአዴግ አባላት ታሰሩ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) እንዳለው፤ ካለፈው ጥር 8 ቀን እስከ ጥር 15 ቀን ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ብቻ፤ 38 የመኢአድ አባላት ታስረዋል። ከነዚህም መካከል 21ዱ፤ የኢህአዴግ አንድ ክንፍ ከሆነው ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር-ደኢህዴግ አባልነት ራሳቸውን በማግለል፤ ወደ መኢአድ የገቡ ናቸው። እንደ መኢአድ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ገለፃ፤ የኢህአዴግ አባላት የነበሩት 21 ሰዎች የታሰሩት፤ በመ ...
Read More »በሀገረማርያም አካባቢ የሚኖሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከምርጫ በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አትችሉም መባላቸው ገለጡ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ለኢሳት እንደገለጡት የደህንነት ሀይሎች ከምርጫ በፊት ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል እንደነገሩዋቸው ገልጠዋል። የደህንነት ሀይሎችም በተደጋጋሚ ሊያስፈራሩዋቸው እንደሚሞክሩ ተወካዩ ገልጠዋል። በመደረክ አባላት ላይ የሚደርሰው ወከባ እየጨመረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።
Read More »ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከ ጥር 12 ቀን ጀምሮ ሶስተኛ አመታዊ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄዱን ገለጠ
ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢሳት በላከው መግለጫ እንደገለጠው በጉባኤው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የክልል ተወካዮችን ጨምሮ የአውሮጳ፤ የአፍሪካ፤ የኦሲኒያ፤ የመካከለኛው ምስራቅ፤ የካናዳ፤ የሰሜን አሜሪካና የአውሮጳ ተወካዮች እየተሳተፉበት ነው። በዚህ ሶስተኛ ጉባኤ ላይ በዋንኛነት መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው ከወያኔ ጋር እየተካሄደ ያለው የጸረ ዘረኝነት ትግል ይበልጥ ተጠናክሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግቡን ሊመታ የሚችልበትን ድርጅታዊ አቅም በማጎልበት ላይ ...
Read More »