ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ አንድ የወረዳው ፖሊስ የአስቴርዮ ማርያም ክበረ በአል በሚከበርበት እለት በህዝቡ ላይ በተኮሰው ጥይት አንድ ሰው ወዲያውኑ ሲሞት ፣ በርካቶች በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ታወቀ የኢሳት የጋሞጎፋ ዞን ወኪል እንደዘገበው በጨንጫ ወረዳ የአስቴርዮ ማርያም በአል ከፍተኛ ህዝብ ተገኝቶ የሚያከብረው ሀይማኖታዊ ክብረ በአል ነው። በእለቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ከአርባምንጭ እና ከሌሎች ከተሞች ...
Read More »አዲሱ የሊዝ አዋጅ በክፍለ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት ፈጥሯል
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንደዘገቡት፣ የኑሮ ውድነቱ የፈጠረው ውጥረት ሳይበርድ አሁን ደግሞ የሊዝ አዋጁ መጨመሩ ህዝቡ አለመረጋጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በኦሮሚያ የሚኖሩ ሰው ሲናገሩ በእርሳቸው አካባቢ አዲሱ የመሬት ፖሊሲ የህዝብ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው። ነገሮች ሊፈነዱ ተቃርበዋል የሚሉት እኝሁ ግለሰብ መድረክ የሊዝ አዋጁን በመቃወም ሊጠራ ያሰበው ስብሰባ ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ ...
Read More »የመንግስት ጋዜጠኞችና መድረክ መወዛገባቸው ተሰማ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውዝግቡ መንስኤ መድረክ ባለፈው ዓርብ አዲሱን የሊጅ አዋጅ በመቃወም በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የመንግስትና የ ኢህአዴግ ድርጅት ልሳናት ጋዜጠኞች ከ ዋናው አጀንዳ በመውጣት ፦”ሰሞኑን አፋር ውስጥ በአሸባሪዎች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ -መንግስት የያዘውን አቋም ትደግፋላችሁ?ወይስ ትቃወማላችሁ?” የሚል ጥያቄ አከታትለው በመጠየቃቸው ነው። ጋዜጣዊ መግለጫውን እየሰጡ የነበሩት የመድረክ አመራሮችም በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች የየመጡበትን የሚዲያ ተቋማት ይገልጹላቸው ዘንድ ...
Read More »አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የዓፄ ሀይለሥላሴ ሐውልት ቅሬታና ተቃውሞ አስነሳ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቻይና መንግስት በ200 ሚሊዮን ዶላር በተገነባው አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤትና አዳራሽ ቅጥር ግቢ ውስጥ የዓፄ ሀይለሥላሴ ሐውልት አለመቆሙ፤ በኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ዘንድ ቅሬታና ተቃውሞ አስነሳ። ቻይና- ለአፍሪካ ህብረት እንደ ገጸ-በረከት በነፃ ገንብታ ባስረከበችውና ባለፈው ሳምንት የመሪዎቹ ጉባኤ ሲካሄድ ተመርቆ በተከፈተው ታላቅ ህንፃ ውስጥ፤ከፓን አፍሪካኒዝም ሀሳብ አራማጆቹና ከአፍሪካ አንድነት መስራቾቹ ቀደምት የአፍሪካ መሪዎች መካከል ...
Read More »ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በደረሰበት የከፋ ድብዳባ ጆሮው ሲደማ በዓይኑ ማየቱን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ተናገረ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውራምባ ታይምሱ ማኔጂንግ ኤዲተር የነበረውና በቅርቡ በደረሰበት ጫና ለስደት የተዳረገው ጋዜጠኛ ዳዊት ይህን የተናገረው፤ ሰሞኑን የአቶ መለስ ፍርድ ቤት በነ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ላይ ፍርድ መስጠቱን ተከትሎ -ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ነው። በ አንድ ችሎት ላይ ውብሸት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ጆሮው ሲደማ መመልከቱንና ይህ የሆነውም በደረሰበት ድብደባ መሆኑን እንደተረዳ የገለጸው ጋዜጠኛ ዳዊት፤ ከዚያ ...
Read More »የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በአገሪቱ ውስጥ የሚሰሩትን ዋና ዋና ዘመናዊ ህንጻዎች መቆጣጠራቸውን ለማወቅ ታቸለ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የምርመራ ክፍል ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰሩ ህንጻዎችን ባለቤቶች ለማወቅ ባደረገው ጥረት የተወሰኑትን ህንጻዎች ባለቤቶችና የወጣባቸውን ወይም የሚወጣባቸውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ችሎአል። በተለምዶ ቦሌ መድሀኒአለም እየተባለ በሚጠራው ወይም ወረዳ አስራ ሰባት ውስጥ በምእረባዊያን የቤት ደረጃ የሚሰሩት ቤቶች 90 በመቶ የሚሆኑት በከፍተኛ ጄኔራሎች ባለቤትነት የሚሰሩ ወይም ተሰርተው የተጠናቀቁ ናቸው። በዚህ ስዕል የሚታየው በሶኮልላንድ ኩባንያ ...
Read More »በጋምቤላ ክልል ከመከላከያ ሰራዊት በተተኮሰ ጥይት 3 ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ደግሞ ቆሰሉ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ክልል ፉኝዶ ከተማ የመከላከያ ማዘዢያ ጣቢያ ውስጥ በድንገት በተተኮሰ ጥይት ሶስት ሰዎች ተገድለው ሁለት መቁሰላቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገልጧል። ጥር 19 ፣ 2004 ዓም ከሌሊቱ 8 ሰአት ሲሆን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ታይተዋል ተብሎ፣ ሰራዊቱ በየአቅጣጫው በከፈተው ተኩስ የግለሰቦቹ ህይወት አልፎአል በክልሉ የሚታየውን የመሬት ነጠቃ በመቃወም በርካታ ነዋሪዎች ነፍጥ እያነሱ ...
Read More »ኢትዮጵያ ለአለም ገበያ በቂ ቡና ማቅረብ እንዳልቻለች ተገለፀ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቡና ላኪዎች ባለባቸዉ የዉስጥ ችግር ምክንያት መንግሰት በዘንድሮዉ አመት ከያዘዉ 270ሺህ ቶን አመታዊ እቅድ ዉስጥ 25 በመቶ ያህሉን እንኳ እስካለፈዉ 2ኛዉ ሩብ አመት መጨረሻ ድረስ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ እንዳልቻለ አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘገበ። ይኸዉ ሁኔታ ያስደነገጣቸዉ የንግድ ሚኒስትሩ ከበደ ካሳና በሚኒስትር ማእረግ ያሉት ያእቆብ ያላ ባለፈዉ ሳምንት ዉስጥ ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር መሪዎች ጋር ...
Read More »ኢትዮጵያ በሶማሊያ በአልሸባብ ላይ አዲስ የዉጊያ ቀጠና መክፈቷ ታወቀ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግሰት ወታደሮች የአልሸባብ ተዋጊዎች ጠንካራ ምሽግ ወደ ሆነዉ ቁልፍ አካባቢ በመግባት አዲስ የዉጊያ ቀጣና በመክፈት ላይ እንዳሉ የአይን ምስክሮች ገልፀዋል። ዶሎዉ በተባለዉ የድንበር ከተማ በኩል ወደ ሶማሊያ የገባዉ የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ምእራብ ጌዶ ክልል ወደ ሚገኘዉ ለክ ከተማ እንዲሁም ባይ እና ባኩል ወደ ተባሉት በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ወደሚገኙት አካባቢዎች እንዳመራ ታዉቋል። በኢትዮጵያ ፤ ...
Read More »የአቶ መለስ ዜናዊ አያት የባሻ አስረስ ተሰማ ፎቶ ግራፍ በፌስ ቡክ እየተሰራጨ ነው
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህ በፌስ ቡክ፦”shocking photo ”(አስደንጋጭ ፎቶ” ) በሚል ርዕስ ስር የተለቀቀው የአቶ መለስ ዜናዊ አያት የባሻ አስረስ ፎቶ፤ ባሻ አስረስ ከጣሊያን ቅኝ ገዥዎች ሹመት በተቀበሉበት ቀን የተነሱት ነው ። በፎቶው ላይ የአቶ መለስ አያት ባሻ አስረስ ተሰማ፤ ሹመት በሰጧቸው የጣሊያን የጦር አዛዥ ጎን ቆመውና በተከታዮቻቸው ታጅበው ይታያሉ። አቶ ገብረመድህን አርአያን ጨምሮ የአቶ መለስ ዜናዊን ...
Read More »