በሀገረማርያም አካባቢ የሚኖሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከምርጫ በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አትችሉም መባላቸው ገለጡ

ጥር 20 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ለኢሳት እንደገለጡት የደህንነት ሀይሎች ከምርጫ በፊት ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል እንደነገሩዋቸው ገልጠዋል።

የደህንነት ሀይሎችም በተደጋጋሚ ሊያስፈራሩዋቸው እንደሚሞክሩ ተወካዩ ገልጠዋል።

በመደረክ አባላት ላይ የሚደርሰው ወከባ እየጨመረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።