አልሸባብ “አፍጎየ” የምትባለውን ስትራቴጂክ ከተማ ለቆ ወጣ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አልሸባብ ፤ሰሞኑን ከሽግግር መንግስቱና ከአፍሪካ ህብረት በደረሰበት ጥቃት ከሞቃዲሹ በቅርብ ርቀት የምትገኘዋን አፍጎየ ከተማን ለቆ ለመውጣት መገደዱን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁቡ ጊዜ በከተማ ይኖሩ የነበሩ ሶማሊያውያን አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ የአልሸባብ ሰራዊት ከተማውን ለቆ የወጣው ያለምንም ጦርነት ነው፣ ይሁን እንጅ የአፍሪካ ህብረት ጦር ወደ መሀል ከተማዋ ደፍሮ ለመዝለቅ አልቻለም። የወታደራዊ ተንታኞች ...

Read More »

የአሜሪካ ደምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ፒተር ሀይንላይን ታሰረ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ፒተር ሀይንላይን የታሰረው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአወልያ ያደረጉትን ተቃውሞ ለመዘገብ በሄደበት ጊዜ ነው ። ፒተር ከአዲስ አበባ በሚያስተላልፋቸው ነጻ ዘገባዎቹ በመላው የአሜሪካ ድምጽ አድማጮች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት አለው። በያዝነው ሳምንት መግቢያ ላይ ጋዜጠኛ ፒተር የሙስሊሞችን ተቃውሞ በመዳሰስ የሰራው ዘገባ ለእስራቱ አፋጣኝ ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ...

Read More »

በአዲስ አበባ አትክልት ተራ ፤ፖሊሶች ከነጋዴዎች እና ከነዋሪዎች ጋር ተጋጩ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት ፣ መጋቢት 16፣ 2004ዓም በአትክልት ተራ ፖሊሶች አንድ አትክልት ሻጭን መደብደባቸውን ተከትሎ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ በማሰማቸው  ፖሊሶች ወደ ሀይል እርምጃ አምርተዋል። በተከራይ እና አከራይ  መካከል የተነሳን ውዝግብ ሳቢያ  በጉሊት ሽያጭ የሚተዳደር ሰኢድ ኡመካ የተባለ ወጣት በፖሊሶች በመደብደቡ፤ የአፍሪካ አንድነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን በጩኸት አሰምተዋል። ጩኸቱ ወደተካረረ ፍጥጫ አምርቶ ግጭት ማስከተሉን ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መቀጠሉን ገለጠ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የ2012 አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በዝርዝር አቅርቧል። በአረቡ አለም የታየውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የመለስ መንግስት አምና በመጋቢት እና በሚያዚያ ወራት 250 የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ እና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላት መታሰራቸውን፣ በሰኔ ወር ደግሞ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙመ ዘሪሁን ...

Read More »

ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብ የዕርዳታ ድርጅቶ ች ጥሪ አቀረቡ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብና በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በልግ ዝናብ ተስተጓጉሎ በሰብሎች ላይ ጉዳት በማስከተሉ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብ የዕርዳታ ድርጅቶ ች ጥሪ አቀረቡ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች አስተባባሪ ማይክ ማግዶናግ በልግ አብቃይ የሆኑት አካባቢዎች በተለይም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጠቃቱን ለኢሪን ገልጸዋል። የሰሜን ምሥራቅ አማራ፣ የኦሮሚያ እና ...

Read More »

ታዋቂው የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነት ያገለግሉ ነበሩ:: በደረሰባቸው ድንገተኛ ህመም ለጥቂት ጊዜ  በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ ባለትዳርና  የ4 ልጆ ች አባት እንዲሁም የሁለት ልጆች አያት ነበሩ:: በጋዜጠኛ ንጉሤ ጋማ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ ይዘን እንቀርባለን። ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ለአቶ መለስ ዜናዊ የተያዘው መርሀ ግብር እንዲሰረዝ ተደረገ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበር አባላት ባደረጉት ተጽእኖ ለአቶ መለስ ዜናዊ የተያዘው መርሀ ግብር እንዲሰረዝ ተደረገ አቶ መለስ ፣ ታቦ ምቤኪ አፍሪካን ሌደርሽፕ ኢንስቲቲዩት የተባለ ተቋም  ፣ በሚያዘጋጀው  ጉባኤ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች እና ምሁራን በሚገኙበት ዛሬ ሜይ 24፣ 2012 ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጾ ነበር። ዝግጅቱን ...

Read More »

የተለያዩ የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች የጋራ የትግል ሸንጎ መሰረቱ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተለያዩ የፖለቲካ እና ሲቪክ ማህበራትን በማካተት ከግንቦት10 እስከ 13 በካናዳዋ ዋና ከተማ ኦታዋ በተደረገው ጉባኤ ፣ በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኘውን የህወሀት/ ኢህአዴግን መንግስት ለመታገልና የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት ለማድረግ ላለፉት 2 አመታት በተደረገው ጥረት ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ” የተባለ ህብረት መመመስረቱን ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። ህብረቱን ከፖለቲካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኙ የጋዜጦችና የመጽሔቶች አሳታሚዎች ኢፕአማ የተሰኘ ማህበር ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚገኙ የጋዜጦችና የመጽሔቶች አሳታሚዎች የመንግሥትን ኢፍትሃዊ ጫና ለመቋቋም “የኢትዮጵያ ፕሬስ አሳታሚዎች ማህበር” (ኢፕአማ) የተሰኘ  ማህበር ለማቋቋም በመሠረታዊ ሃሳቡ ላይ ትናንት ከሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ትናንት ረቡዕ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም በአቶ አማረ አረጋዊ “ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕረስ ኢንስቲቲዩት” ቢሮ የተሰባሰቡት አሳታሚዎች በቅርቡ በብርሃንና ሰላም እና ቦሌ ማተሚያ ቤት የወጣውን ...

Read More »

የአንድ ለአምስት ፖለቲካዊ አደረጃጀት ወደ መንግስት መ/ቤቶች እየዘለቀ ነው

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞቹን አንድ ለአምስት በሚል አደረጃጀት በማዋቀር በሥራ ሰዓት ጭምር ስብሰባዎችን በማካሄድ ሠራተኛው እርስ በርስ እንዳይተማመን የማድረግ አሠራር ተግባራዊ በማድረጉ በሥራ ዋስትናቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡን አንዳንድ ሠራተኞች አስታውቀዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የልማት ሠራዊት ለመገንባት በሚል ሠራተኛው አንድ ለአምስት እንዲደራጅና በየዕለቱ ከ30 ደቂቃ ላላነሰ ግዜ በቀኑ ውስጥ ባጋጠሙ ...

Read More »