ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብ የዕርዳታ ድርጅቶ ች ጥሪ አቀረቡ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብና በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በልግ ዝናብ ተስተጓጉሎ በሰብሎች ላይ ጉዳት በማስከተሉ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብ የዕርዳታ ድርጅቶ ች ጥሪ አቀረቡ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች አስተባባሪ ማይክ ማግዶናግ በልግ አብቃይ የሆኑት አካባቢዎች በተለይም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጠቃቱን ለኢሪን ገልጸዋል።

የሰሜን ምሥራቅ አማራ፣ የኦሮሚያ እና የ ትግራይ ክልሎችም ሌሎቹ በምግብ ሰብል እጥረት የተጠቁ አካባቢዎች መሆናቸውን ማግዶናግ አመልክተዋል።

የበልግ ዝናግ ዘግይቶ በመጀመሩ ብቻ ሳይሆን አጣጣሉም ከመደበኛው በታች ሆኖ በመመዝገቡ ጭምር በ አናዳንድ አካባቢዎች ከ ዓመታዊ ምርት 40 በመቶውን ያህል  ሲሸፍን የቆየው የበልግ ምርት በተያዘው ዓመት ክፉኛ በጣም እንደሚያሽቆለቁል የተመዱ አስተባባሪ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ቃል አቀባይ ጁዲት ስሹለር በበኩላቸው ሁኔታው አሣሳቢና የቅርብ ክትትልን የሚሻ ነው ብለዋል።.

በአሁኑ ጊዜ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን  በምግብ እጥረት  ተጠቅተው የቅርብ እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የኢሪን ዘገባ ያመለክታል።

ይህ አሀዝ በሴፍቲኔት ወይም በምግብ ለሥራ ፕሮግራም ታቅፈው እየተረዱ ያሉትን 8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አያካትትም።

የ ዓለም ምግብ ፕሮግራም፤ ከ 3 ነጥብ 2 ሚሊየኑ  ተረጀረዎች ውስጥ ፈጣን እና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ተረጅዎች ምግብ ማቅረቢያ የሚሆን 183 ሚሊዮን የ አሜሪካ ዶላር በተያዘው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ ይለቀቅለት ዘንድ ጥያቄ አቅርቧል።

በተለይ በኬንያ እና በደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የደቡብ ክልል ነዋሪዎች የተለየ ድጋፍና ክትትል ሊደረግላቸው እንደሚገባ  ተመልክቷል።

በ አሁኑ ጊዜ በ ኢትዮጵያ በሴፍቲኔት የታቀፉ 8 ሚሊዮን፣ አስቸኳይ ድጋፍ የሚሹ 3 ነጥብ 2 በ አጠቃላይ 11 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህዝብ በ እርዳታ እህል ህይወቱን እየገፋ ይገኛል።

አቶ መለስ ዜናዊ  ከሳምንት በፊት በካምፕ ዴቪድ በተካሄደው የጅ 8 አገሮች ስብሰባ  ላይ የተጋበዙት፤ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ አበረታች ውጤት በማስመዝገባቸ ነው መባሉ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide