አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መቀጠሉን ገለጠ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የ2012 አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በዝርዝር አቅርቧል። በአረቡ አለም የታየውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የመለስ መንግስት አምና በመጋቢት እና በሚያዚያ ወራት 250 የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ እና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላት መታሰራቸውን፣ በሰኔ ወር ደግሞ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙመ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄርና ደጄኔ ተፈራ መታሰራቸውን ገልጧል።

በሀምሌ ወር የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብየና ጆሀን ፔርሰን ፣ በነሀሴና መስከረም ደግሞ በቀለ ገርባና ኦልባና ሊሌሳ ፣ አንዱአለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋና ሌሎችም መታሰራቸውን ገልጠዋል።  በህዳር ወር 107 የተቃዋሚ ደርጅቶች መሪዎችና ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት መከሰሳቸውን እንዲሁም አልጀዚራ፣ የአሜሪካ ድምጽ፣ ኢሳት ቴሌቪዥን፣ አዲስ ነገርና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዌብሳይት መታፈናቸውን ድርጅቱ ገልጧል።

በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድብደባ እና እንግልት በዝርዝር አብራርቷል። በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሶማሊያ፣ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ያለፍላጎታቸው መፈናቀላቸውን አትቷል።

አምነስቲ በዚህ አመት ሪፖርቱ የምእራባዊያን መንግስታትን ክፉኛ ወቅሷል፡፡ የምእራባዊያን መንግስታት   በተለያዩ አገራት ሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ አይተው እንዳላዩ ሆነው ማለፋቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲጨምር እንዳደረገው ጠቅሷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide