ፒተር ሀይንላይን ወገቡ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተዘገበ

ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው አርብ ከፒተር ሀይንላይን ጋር  ለአንድ ቀን ከታሰረች በሁዋላ የተለቀቀችውና የቪኦኤው ዘጋቢ አስተርጓሚ የሆነችው ጋዜጠኛ  ስመኝሽ የቆዬ እንደገለጸችው፤ዓርብ ዕለት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ገደማ አወሊያ ትምህርት ቤት ቆይተው ሲመለሱ ሲቪል የለበሱ የደኅንነት ሰዎች በፖሊስ ካስቆሟቸው በኋላ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ እንዳለባቸው ይገልጹላቸዋል:: ጋዜጠኛ ሄይንላየንና ስመኝሽም፣ ‹‹ምን እንዳደረግን ሳናውቅ አንሄድም›› የሚል ምላሽ ይሰጣሉ:: ሪፖርተር ...

Read More »

በዩክሬን የፓርላማ አባላት ተደባደቡ

ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዩክሬን ምሥራቃዊ ግዛት በፍርድ ቤቶች፣ በሆስፒታሎች እና  በመንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሩሲያን ቋንቋ ለመጠቀም በወጣው ረቂቅ አዋጅ ሳቢያ የፓርላማ አባላት ተደባደቡ። እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ፤ ረቂቅ ሕጉን በሚደግፉትና በሚቃወሙት የዩክሬን ፓርላማ አባላት  መካከል  በተፈጠረው አምባጓሮ እና ድብድብ አንድ የፓርላማ አባል ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። ጠቡ የተቀሰቀሰው፣ የሩሲያን ቋንቋ መጠቀም አግባብ አይደለም የሚሉ የፓርላማ አባላት ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ግንቦት20 ሀዘን ይዞልን የመጣ በመሆኑ በሀዘን ነው የምናከብረው ይላሉ

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ወደ ስልጣን የመጣበትን 21ኛ አመት እያከበረ ባለበት ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አነጋገረናል። አንድ ስሟ እንዳይገለጥ የፈለገች በቤንሻንጉል አካባቢ የምትኖር ኢትዮጵያዊት ግንቦት20 ለኢትዮጵያ ሀዘንን ፣ ውድቀትና ጥፋትን ይዞ የመጣ በመሆኑ ቀኑን በሀዘን እንደምታከብረው ገልጻለች። ወጣቷ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ድል ይዞ መመምጣቱ ይነገራል ምን አስተያየት አለሽ ተብላ ለተጠየቀችው   ሰትመልስ በአገሪቱ  ረሀብ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ልዩ ሀይሎች 10 ሰዎችን ገደሉ ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ገለጠ

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የሰብአዊ መብቶች  ጠበቃ የሆነው ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ ባወጣው ዘገባ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ልዩ የፖሊስ ሀይል በምስራቅ የሶማሊ አካባቢ መጋቢት ወር ውስጥ 10 ሰዎችን መግደሉን ፣ የሂውማን ራይትስ ወች የእውነት አጣሪ ቡድን ወደ ሶማሊላንድ ተጉዞ ለማጣራት መቻሉን ገልጧል። እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር መጋቢት 16 የልዩ  ፖሊስ አባላት በጋሻሞ ወረዳ ራቅዳ በምትባል መንደር ውስጥ ...

Read More »

ኢህአዴግ የጥፋት ሀይሎችን በዝምታ እንደማያይ ተናገረ

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ገዢው ፓርቲ የግንቦት20 በአልን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ ተቃዋሚዎች እያሳደሩ ያለውን ተጽእኖ በዝርዝር አቅርቧል። ኢህአዴግ በመግለጫው ” አገሪቱ የተያያዘችው ፈጣን ልማትና የዳበረ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያስደነገጣቸው የጥፋት ሀይሎች ከውጭ ሆነው ለኢትዮጵያ ድጋፍ አታድርጉ፣ ብድር አትፍቀዱ ከማለት ጀምሮ ከሻዕብያ መንግስት ስልጠናና ምክር በመውሰድ በሽብር ስራ ላይ መሰማራታቸውን፣ በአገር ውስጥ ደግሞ የሀይማኖት፣ የኑሮ ውድነቱንና ሌሎች ...

Read More »

ሀይሌ ገ/ስላሴ በለንደን ኦሎምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችለውን እድል አጣ

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተደረገው የ10 ሺ ሜትር የሩቻ ውድድር ሀይሌ አንደኛ ወይም ሁለተኛ ወጥቶ ማሸነፍ ቢችል ኖሮ በለንደን ኦሎምፒክ መሳተፍ ይችል ነበር። ይሁን እንጅ ታዋቂው የ2 ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊው ሀይሌ፣ ውድድሩን 7ኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ሳይሳካለት ቀርቷል።” በለንደን ኦሎምፒክ እንደማልሳተፍ እርገጠኛ ሆኛለሁ፣ ይህ የህይወት አንድ አካል በመሆኑ ግን አላዝንም ” ሲል ሀይሌ ተናግሯል። ታሪኩ በቀለ ...

Read More »

የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ፒተር ሀይን ላይን ተፈታ። ከኢትዮጵያ ሊባረር እንደሚችል ተጠቆመ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፒተር ሀይንላይን መፈታት ቀደም ብሎ የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል፦”ጋዜጠኛውን ለመፍታት ወስነናል። በአስቸኳይ  ይፈታል”በማለት ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ  ተናግረው ነበር። ፒተርሀይን ላይን የታሰረው፤ ትናንት በአወሊያ መስጊድ ተገኝቶ ተቃውሞ ሲያሰሙ የለነበሩትን ሙስሊሞች ቃለ ምልልስ በማድረግ ላይ እያለ ነበር። አቶ ሽመልስ ለኤ. ኤፍ. ፒ ሲናገሩ፤ ፒተር ሀይን ላይን ሊታሰር የቻለው የመታወቂያ ካርዱን እንዲያሳይ ከፖሊስ ...

Read More »

ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደል ቅዱስ ሲኖዶስ በማውገዙ ሙስሊሞች ምስጋናቸውን ገለጹ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በስደት የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን በደል በማውገዙ አድናቆታቸውን እና ምስጋናቸውን ገለጹ። በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ 33 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህገ-መንግስቱ በፈቀደላቸው መሰረት እምነታቸውን በነፃነት እንዳይከተሉ መንግስት ጣልቃ በመግባት እየፈጠረባቸው  ካለው ጫና  በ ...

Read More »

ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የመዘጊያ ዕለታቸው አንድ ወር ከ 15 ቀደም ብለው እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላለፈ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መምህራን ለ ኢሳት እንደገለጹት፤በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ መንፈቅ ትምህርት ክፍለ ጊዜን ከያዙት መርሃ- ግብር ቀደም ብለው እንዲያጠናቅቁና ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ ኢህአዴግ መመሪያ አውርዷል። የኢህአዴግን ድንገተኛ ውሳኔ በመቃወም ከወረዳ እና ከዞን ትምህርት ቢሮዎች ጋር ለመነጋገር የሞከሩ ትምህርት ቤቶች ተቀባይነት አላገኙም ያሉን አንድ ...

Read More »

አይኤም ኤፍ የኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ግሽበቱን እንዲቀነስ ጫና እንደሚያደርግ ተዘገበ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ እንደጠቆመው፤ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄደው የአይኤም ኤፍ የልኡካን ቡድን፣ መንግስት አሁን የሚታየውን ኸፍተኛ የገንዘብ ግሽበት ለመቆጣጠር ይችል ዘንድ ግፊት ያደርጋል። የገንዘብ ተቋሙ እንዳለው ባንኮች የተቀማጭ ወለድን እንዲያሳድጉ ማድረግ አንዱ አማራጭ፣ በመሆኑ ይህንን ለማስፈጸም  ልኡካኑ ከመንግስት ጋር ይነጋገራሉ። ኢትዮጵያ ላለፉት አመታት ያገኘችው እድገት በገንዘብ ግሽበት የተነሳ ወደ ሁዋላ የመመለስ ...

Read More »