የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ፒተር ሀይን ላይን ተፈታ። ከኢትዮጵያ ሊባረር እንደሚችል ተጠቆመ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከፒተር ሀይንላይን መፈታት ቀደም ብሎ የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል፦”ጋዜጠኛውን ለመፍታት ወስነናል። በአስቸኳይ  ይፈታል”በማለት ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ  ተናግረው ነበር።

ፒተርሀይን ላይን የታሰረው፤ ትናንት በአወሊያ መስጊድ ተገኝቶ ተቃውሞ ሲያሰሙ የለነበሩትን ሙስሊሞች ቃለ ምልልስ በማድረግ ላይ እያለ ነበር።

አቶ ሽመልስ ለኤ. ኤፍ. ፒ ሲናገሩ፤ ፒተር ሀይን ላይን ሊታሰር የቻለው የመታወቂያ ካርዱን እንዲያሳይ ከፖሊስ ለቀረበለት ጥያቄ ትብብር ባለማሳየቱ ነው ብለዋል።

“ፖሊሶች በሚጠይቁት ጊዜ ስለማንነቱ ለመግለጽ ወይም ጋዜጠኛ መሆኑን ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም።በዚህም ምክንያት  ፖሊሶቹ ወደ ጣቢያ ይዘውት ሄደዋል” ብለዋል-አቶ ሽመልስ።

አቶ ሽመልስ ከዜና አውታሩ ጋር ይህን ምልልስ ባደረጉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፒተር ሀይንላይን  ከእስር ተፈቷል።

አቶ ሽመልስ በንግግራቸው መጀመሪያ ላይ  ሄይንላይን ከኢትዮጵያ ሊባረር ይችላል ብለው መናገራቸውን ያመለከተው ኤ.አፍ.ፒ፤ ወደ ሁዋላ ላይ ግን   በኢትዮጵያ እንዲቆይ ተፈቅዶለታል ሲሉ ተደምጠዋል ብሏል።

“ጋዜጠኛው ከአገር ሊባረር ይችላል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ይህ ከመታሰሩ ጋር ግንኙነት የለውም” ነው፡ያሉት አቶ ሽመልስ። ከጋዜጠኛው ጋር አብራ የታሰረችው አስተርጓሚ ትፈታ አትፈታ የታወቀ ነገር የለም።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞችን ጨምሮ አምስት ጋዜጠኞች የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።

በጋዜጠኛ ፒተር ሀይንላይን ላይ በትናንትናው ዕለት የተፈፀመውን እስር  ያወገዘው ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት(ሲ.ፒ.ጄ)፤ኢትዮጵያ   ጥብቅ የሚዲያ ህግ ከሚተገብሩ የዓለም አገሮች በግንባር ቀደምነት የምትጠቀስ መሆኗን አመልክቷል።

የመለስ መንግስት በ1997 ምርጫ ማግስት የከሰሰሳቸውን የአሜሪካ ደምጽ የአማራኛው ክፍል አዘጋጆች ክሳቸው እንዲቋረጥ ማድረጉ ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide