ሀይሌ ገ/ስላሴ በለንደን ኦሎምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችለውን እድል አጣ

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተደረገው የ10 ሺ ሜትር የሩቻ ውድድር ሀይሌ አንደኛ ወይም ሁለተኛ ወጥቶ ማሸነፍ ቢችል ኖሮ በለንደን ኦሎምፒክ መሳተፍ ይችል ነበር። ይሁን እንጅ ታዋቂው የ2 ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊው ሀይሌ፣ ውድድሩን 7ኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ሳይሳካለት ቀርቷል።” በለንደን ኦሎምፒክ እንደማልሳተፍ እርገጠኛ ሆኛለሁ፣ ይህ የህይወት አንድ አካል በመሆኑ ግን አላዝንም ” ሲል ሀይሌ ተናግሯል። ታሪኩ በቀለ እና ሌሊሳ ደሲሳ ቤንቲ ውድድሩን አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው በመጨረሳቸው በ10 ሺ ሜትር የሚወዳደሩ ሲሆን፣ ቀነኒሳ በቀለ ቀደም ብሎ ማጣሪያውን ያለፈ በመሆኑ በውድድሩ ኢትዮጵያን ወክሎ ይቀርባል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide