የሰሜን ጎንደር የመኢኣድ ምክር ቤት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ታሰሩ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታድሎ ተፈራ የታሰሩት ትናንት ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ ፖሊሶች ወደ ቤታቸው በመሄድ እና ከፍተኛ ፍተሻ በማካሄድ አፍነው ወስደውታል። የበለሳ ተወላጅ የሆነው አቶ ታደሎ ተፈራ  ጎንደር ከተማ ውስጥ ከአክስቱ ጋር ይኖር ነበር። አክስቱ  ወ/ሮ ዘርጊባቸው ሀይሉ ለኢሳት እንደገለጡት ግለሰቡን በርካታ ፖሊሶች ስራ ይሰራበት ከነበረው ደልጊ ከተማ ...

Read More »

በአፋር ክልል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፋር ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት በክልሉ ያለው ችግር መባባስ ህዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን እንዳይገፋ አድርጎታል።  በዞን አንድ እና ዞን 3 በተባሉት አካባቢዎች መንግስት ነዋሪዎችን በጉልበት እያፈናቀለ መቀጠሉን  በዞን ሁለት ደግሞ የማእድን ዘረፋው የችግሩ ምንጭ መሆኑን  የአፋር ህዝብ ጋድሌ ሰራዊት ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት ገልጠዋል:: ኮሎኔል ሙሀመድ እንዳሉት ለስኳር ፋብሪካ በሚል አካባቢው ...

Read More »

የመሬት ቅርምት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ጋዜጣ ዘገበ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስዊዘርላንድ የሚታተም ታገስ አንዛይገር የተባለ ጋዜጣ  ፣ በመሬት እና ባካባቢው ከሚኖሩ ዜጎች ፍላጎት እና ስምምነት ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ኢንቨስትመንት  በባለሃብቶች እና ባካባቢው በሚኖሩ ዜጎች መካከል በሚፈጠር  አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያመራ እና   በሃገሪቷ ውስጥም አለመረጋጋት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቋል። ጋዜጣው የአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የእርሻ መሬት 10% ወይም 3.6 ሚሊዮን ...

Read More »

ኢትዮጵያዊቷ በኩዌት ጎዳናዎች ራቁቷን ደም በደም ሆና ታየች

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደሟን እያዘራች ራቁቷን በኩዌት ጎዳናዎች ላይ ስትሮጥ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት በፖሊስ ተይዛ -በሳይካትሪስት ምርመራና ህክምና እንዲደረግላት ወደ ሆስፒታል መግባቷን አረብ ታይምስ ዘገበ። አረብ ታይምስ ፦ “አል ራይ” የተባለውን የአገሪቱን ሳምንታዊ ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በጎዳና ላይ ሲጓዙ የነበሩ እግረኞች  አፍሪካዊ መልክ ያላት ሴት ራቁቷን ሆና ደም እየፈሰሳት በጎዳና ላይ ስትሮጥ ማየታቸውን ለኩዌት የአገር ...

Read More »

ሆስኒ ሙባረክ በዕድሜ ልክ እሥራት እንዲቀጡ ተወሰነ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ 84 ዓመቱ ሙባረክ  ለፍርድ ቤቱ በከፍተኛ የጤና ችግር ላይ እንደሆኑ በማመልከት አስተያዬት ይደረግላቸው ዘንድ ጠይቀው እንደነበር የግብጽ መንግስታዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ሆስኒ ሙባርክን ለዕድሜ ልክ እሥራት ያበቃቸው፤ ባለፈው ዓመት የተካሄደውንና እርሳቸውን ከመንበራቸው የፈነቀላቸውን የግብጽ አብዮት  ለማክሸፍ በማሰብ  ባስወሰዱት የሀይል እርምጃ በርካታ ተቃዋሚዎች በመገደላቸው ነው። ሙባረክ፤በዓረቡ ዓለም አብዮት ከተወገዱት መካከል ፦ ለፍርድ የቀረቡ  ...

Read More »

በከምሴ የሚገኙ ሙስሊሞች ዛሬም ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ተፋጠው ሶላትን አሳለፉ

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሙስሊሞቹ በከተማው የገቢዎች ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በደዌይ መስመር አካባቢ በሚገኘው መስጊድ እንደተሰባሰቡ የፌደራል ፖሊስ አባላትም አብረው በመግባት ሙስሊሞቹ ሶላታቸውን እንደጨረሱ እንዲበተኑ አድርገዋል።  ፖሊሶች ከሶላት በፊት ሌላ ነገር ማድረግ አትችሉም ተብለው እንዲበተኑ ቢደረገም፣ ፍጥጫው እንዳለ መሆኑን ምንጮች ገልጠዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ሙስሊሞችን ለማግባባት ጥረት ሲያደርጉ፣ የተወሰኑ ወጣቶችንም ለማስፈራራት ሙከራ ...

Read More »

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሁለት የተቃዋሚ ፓርተዎች አባላትን አፍነው ወሰዱ

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደባርቅ ወኪል ባስተላለፈው መረጃ መሰረት በትናንትናው እለት ቀድሞ የመኢአድ አባል የነበረውና በምርጫ 97 ቅንጅትን፣ በምርጫ 2002 ደግሞ አንድነት ፓርቲን በመወከል ሲንቀሳቀስ የነበረውን አቶ ስለሺ ጥጋቤን አፍነው ወስደውታል። ግለሰቡ ከተያዘ በሁዋላ ቤቱ ለ2 ሰአታት ሲበረበር እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።  የአቶ ስለሺ ጥጋቤ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጡት፣ ፖሊሶች እና የደህንነት ሰዎች ግለሰቡን አፍነው ወደ አዲስ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ሙስና የኮንዶሚኒየም ቤቶችንም እየጎበኘ ነው

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል የሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሸን በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) ለባለዕድለኞች የማሰተላለፍ ሒደት ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡ ኮሚሸኑ ያካሄደውና በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በከተማዋ ዲዛይንና አስተዳደር ልማት ቢሮ ካሉበት ለሙስና የተጋለጡ ችግሮች መካከል ቤቱን ትክክለኛነቱን አረጋግጦ በመፈራረም አያሰረክብም የሚለው ይገኝበታል፡፡ ኮሚሸኑ በጥናቱ እንደአብነት ካነሳው ውስጥ ...

Read More »

ኢትዮጵያዊው የረዥም ርቀት ሯጭ በድራግ ምክንያት ታገደ

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሌላ በኩል በሮም በተካሄደው የ 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፋንቱ ማንጌሶ በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ በተመልካቾችና በኮሜንታሮች ዘንድ ልዩ አድናቆትን  ጭራለች። እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ  አትሌት ህዝቅያስ ሢሳይ ለሁለት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች የታገደው ባለፈው ዓመት በተካሄደው እና ዘጠነኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት የኒውዮርክ ማራቶን ላይ   ኤሪትሮፖቲን ወይም በምህፃረ-ቃሉ ኢፒኦ ተብሎ የሚጠራቀውን ሀይል ሰጪ ድራግ ...

Read More »

በከምሴ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድዋ እንዳያደርጉ ተከለከሉ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በከምሴ ልዩ  ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ባለፈው አርብ ሶላት ሊያደርጉ በከተማዋ መሀል አደባባይ በሚገኘው መስጊድ ውስጥ  ለመሰባሰብ ጉዞ ሲጀምሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት አካባቢውን ተቆጣጥረዋል። ነዋሪዎቹ ከመስጊዱ ግቢ አልፈው  በአስፓልቱ ላይ በመቆማቸው የከተማው ትራፊኮች  ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱትን መኪኖች  ጉዞአቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ተገደዋል። በፌደራል ከባድ ...

Read More »