አይኤም ኤፍ የኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ግሽበቱን እንዲቀነስ ጫና እንደሚያደርግ ተዘገበ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ እንደጠቆመው፤ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄደው የአይኤም ኤፍ የልኡካን ቡድን፣ መንግስት አሁን የሚታየውን ኸፍተኛ የገንዘብ ግሽበት ለመቆጣጠር ይችል ዘንድ ግፊት ያደርጋል።

የገንዘብ ተቋሙ እንዳለው ባንኮች የተቀማጭ ወለድን እንዲያሳድጉ ማድረግ አንዱ አማራጭ፣ በመሆኑ ይህንን ለማስፈጸም  ልኡካኑ ከመንግስት ጋር ይነጋገራሉ።

ኢትዮጵያ ላለፉት አመታት ያገኘችው እድገት በገንዘብ ግሽበት የተነሳ ወደ ሁዋላ የመመለስ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው አይኤም ኤፍ፣ መንግስት ግሽበቱን ከ10 በመቶ በታች ማድረግ እንዳለበት ጠቅሟል።

የ ኢሳት ዘጋቢ ያነጋገሯቸው የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች፤በያዝነው ወር በመላ አገሪቱ ከፍተኛ ሆነ የእህል ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጠዋል። የዘጋቢዎቻችን መረጃ እንደሚያሳየው ፤ህብረተሰቡ የኑሮ ውድነቱን ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ እንደሆነበት በእጅጉ ሲያማርር ይሰማል።  መንግስት የዋጋ ንረቱን እስከ መስከረም ወር ድረስ ወደ አንድ አሀዝ አስገባዋለሁ ቢልም፣ የሚሳካለት አይመስልም ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ኤኢ ኤም ኤፍ አሁን የሚታየው የዋጋ ንረት ባለበት ከቀጠለ፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መምራት ወደ ማይቻልበት ደረጃ ይደርሳል ብሎአል። በሌላ ዜና ደግሞ መንግስት ከ2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሆነ እጅግ ሰፊ መሬት ለውጭ ባለሀብቶች ቢሰጥም፣ እስካሁን ወደ ስራ የገቡት እጅግ ጥቂት በመሆናቸው ቅሬታ እንደተሰማው ገልጧል።

ይሁንና  ኩባንያዎቹ ወደ ስራ ለምን እንዳልገቡ መንግስት ያብራራው ነገር የለም።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide