አልሸባብ “አፍጎየ” የምትባለውን ስትራቴጂክ ከተማ ለቆ ወጣ

ግንቦት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አልሸባብ ፤ሰሞኑን ከሽግግር መንግስቱና ከአፍሪካ ህብረት በደረሰበት ጥቃት ከሞቃዲሹ በቅርብ ርቀት የምትገኘዋን አፍጎየ ከተማን ለቆ ለመውጣት መገደዱን ቢቢሲ ዘግቧል።

በአሁቡ ጊዜ በከተማ ይኖሩ የነበሩ ሶማሊያውያን አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ የአልሸባብ ሰራዊት ከተማውን ለቆ የወጣው ያለምንም ጦርነት ነው፣ ይሁን እንጅ የአፍሪካ ህብረት ጦር ወደ መሀል ከተማዋ ደፍሮ ለመዝለቅ አልቻለም።

የወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት የአልሸባብ አፍጎየን መልቀቅ፣ ለአፍሪካ ህብረት ድል፣ ለታጣቂው ሀይል ሽንፈት ነው። የኢትዮጵያ ጦር አሁንም በሶማሊያ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ባይደዋን የተቆጣጠረው ጦር ወደ ደቡብ ሶማሊያ ዘልቆ አልሸባብን ይወጋል ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከባይደዋ ውጭ ጥቃት ለመፈጸም አልፈለገም።

አቶ መለስ ጦሩ ግዴታውን ፈጽሞ በአጭር ጊዜ እንደሚመለስ ከሁለት ወራት በፊት መናገራቸው ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide