በኢትዮጵያ ባንኮች እና በፍትህ አካላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ አካላት የደንበኞቻቸውን ምሥጢር እንዲያወጡ በሚያሳርፉባቸው ጫና ባንኮች በአሠራራቸው ላይ ከፍ ያለ ችግር ተጋርጦባቸዋል። እንደ ሪፖርተር ዘገባ፤አንዳንድ የፖሊስና የዓቃቤ ሕግ አባላት ለባንኮች የደንበኛ ምሥጢር እንዲገለጽላቸው በሚያቀርቡት ጥያቄና- ባንኮችም ጥያቄውን ለመመለስ የደንበኛው ፈቃድ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቀርብላቸው በሚያነሱት ጥያቄ የተነሳ፤ አለመባባት ከተፈጠረ ሰንበትበት ብሏል። በዚህም ሳቢያ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ባለፈው ረቡዕ ችግሩ ...

Read More »

ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ የፈለጉ ኢትዮጵያውያን ቪዛ እየተከለከሉ ነው

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ  ኢትዮጵያ ሄደው ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ የፈለጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን፦”የግንቦት 7 አባላት ናችሁ” እየተባሉ በየ አገራቱ ባሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እየተከለከሉ ነው። በቤልጂዬም የምትኖር እና ስሟን መግለጽ ያልፈለገች አንዲት ኢትዮጵያዊ ሰሞኑን ወደ አገሯ አቅንታ ዘመዶቿን ለመጠየቅ ብትፈልግም፤በብራሰልስ የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፦”የግንቦት ሰባት አባል  ስለሆንሽ ቪዛ አንሰጥሽም” በማለት ከልክሏታል። ኤምባሲው  ለአክቲቪስቷ የግንቦት ሰባት አባልነት የጠቀሰውና ...

Read More »

የሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የ40ኛ ቀን መታሰቢያ ሥነሥርዓት ነገ ይከናወናል፡፡

  ግንቦት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሚያዝያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ያተለዩት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የ40ኛ ቀን መታሰቢያ ሥነሥርዓት ዘመድ ፣ወዳጆቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በነገው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤ/ክ ከንጋቱ 1፡00 በሚካሄድ የጸሎት ሥነሥርዓት እንደሚከናወን ሀብትና ንብረታቸውን የወረሰው መንግስታዊው  የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ በነገው ዕለት በቤተክርሰቲያን ከሚካሄደው የጸሎት ...

Read More »

ነገ አርብ በአንዋር መስጅድ ከፍተኛ የዝምታ ተቃውሞ ይካሄዳል

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንዳለው በነገው ተቃውሞ ሙስሊሞች  አፋቸውን በመሸፈንና  የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ  ተቃውሞአቸውን ይገልጣሉ። “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም! የህዝብ ድምጽ ይከበር! ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄድ! ” የሚሉት መፈክሮች እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሎአል። ትናንሽ የኢትዮጵያን ባንድራ ገዝተው  በማውለብልብ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚያሳዩት ፍጹም ሰለማዊ የሆነ ተቃውሞ ብዙዎችን እያስደመመ ነው። የመለስ ...

Read More »

መንግስት ዳኞቹ የህዝብ አመኔታ እንደሌላቸው አመነ

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍትህ ሚንስትር ከሚያዚያ 10 ቀን እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2004 ዓ.ም “ለፍትህ ሥርዓቱ መጎልበት እንዘጋጅ” በሚል መርህ ሲያከብር ባከናወነው የዳሰሳ ጥናት ላይ የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዳኞችና ዐቃቤያን ሕጎች በተገልጋዮች፣ በታዛቢዎችና ችሎቱን በሚታደሙ ሦስተኛ ወገኖች እምነት እንደማይጣልባቸው ማረጋገጡን የሚ/ር መሥሪያ ቤቱ ምንጮች አስታወቁ፡፡ በአንፃሩ በሌሎች ችሎቶች በሚታዩ ተራ ...

Read More »

ሲፒጄ የኦባማ አስተዳደር በመለስ ዜናዊ ላይ ጫና እንዲያደርግ ጠየቀ

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ( ሲፒጄ) ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጻፈው ደብዳቤ፣ በአለማቀፉ የግብርና እና የምግብ ዋስትና መርሀግብር ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ የሚያቀኑት አቶ መለስ ዜናዊ የፕሬስ ነጻነትን እንዲያከብሩ ግፊት እንዲደረግባቸው ጠይቋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና እየተባባሰ መምጣቱን የገለጠው ሲፒጄ፣ የባራክ ኦባማ መንግስት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ፣ አቶ መለስ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያክብሩ ጫና ...

Read More »

ማህበረ ቅዱሳንን በመንግስት የማስመታቱ ሴራ ቀጥሏል

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ማህበረ ቅዱሳን በሚያሳትማቸው ልሳኖቹ በዋልድባ በሚገነባው የስኳር ፐወሮጀክት ዙሪያ መንግስትን የሚደግፍ ዘገባ ያላተመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ  በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ተጠየቀ። በቤተ- ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ለማህበሩ በፃፈው ክስ አዘል ደብዳቤ፦ “በዋልባ ገዳም አካባቢ የሚካሄደውን ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በተመለከተ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያወጣው መግለጫ በማኅበሩ ልሳናት ላይ ለምን እንዳልተዘገበ  ማህበሩ  በጽሁፍ መልስ ይሰጥበት ዘንድ ...

Read More »

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስጋት ላይ ናቸው

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሱዳን የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች የደህንነት ዋስትናቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ እየወደቀ መምጣቱን ተናገሩ። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ስደተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በወንጀለኝነት የሚጠረጥራቸውን በሱዳን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን፣ የአገሪቱ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጠው የሚያስችል ስምምነት ማድረጉ፣ በህልውናቸው ላይ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የሱዳን መንግስት የመለስን መንግስት ተቃውመው ወደ አገሩ የሚገቡ ኢትዮጵያውያንን እያሳለፈ እንደሚሰጥ ቢታወቁም፣ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በአውሮፓ ፓርላማ ፊት ለፊት ተደረገ

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት8፣ 2004 ዓም በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፊት ለፊት በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የተውጣጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት፣ የሉቅማን የኢትዮጵያውያንና ቤልጂየማውያን ሙስሊሞች ማህበር እንዲሁም በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በጋራ ባዘጋጁት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከጀርመን፣ ስዊድን፣ ሆላንድ፣ ሉክዘምበርግ፣ እንግሊዝና ከሌሎችም አገሮች የመጡ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን በብዛት ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ፈላጭ ...

Read More »

2 ሺህ 700 የ አዳማ (የናዝሬት) ከተማ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-2 ሺህ 700 የ አዳማ(የናዝሬት)ከተማ ነዋሪዎች  “ለሀዲድ ግንባታ “በሚል ያለ ምትክ ቦታ ከይዞታቸው በግዳጅ ተፈናቀሉ። ተፈናቃዮቹ፦”ንብረታችንና ቤታችን በማናውቃቸው ሰዎች ተዘርፏል”  ይላሉ። ሪፖርተር እንደዘገበው፤ለምድር ባቡር ሐዲድ ሥራ  ተብለው ከያዙት ሕጋዊ ቦታ ያለ ምትክ ቦታ በግዳጅ እንዲፈናቀሉ ከተወሰነባቸው    ከ2700 የአዳማ ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪዎች  መካከል ፤ግምት የተሰጠው ለ 719ኙ ብቻ ነው፡፡ ለ2,700 ሦቹ ተፈናቃዮች ምትክ ...

Read More »