የሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የ40ኛ ቀን መታሰቢያ ሥነሥርዓት ነገ ይከናወናል፡፡

 

ግንቦት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሚያዝያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ያተለዩት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የ40ኛ ቀን መታሰቢያ ሥነሥርዓት ዘመድ ፣ወዳጆቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በነገው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤ/ክ ከንጋቱ 1፡00

በሚካሄድ የጸሎት ሥነሥርዓት እንደሚከናወን ሀብትና ንብረታቸውን የወረሰው መንግስታዊው  የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በነገው ዕለት በቤተክርሰቲያን ከሚካሄደው የጸሎት ሥነሥርዓት በተጨማሪ በአልፋ ቪላ የመኖሪያ ቤታቸው ተመሳሳይ ፕሮግራም እንደሚኖር ታውቋል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 1925 ዓ.ም አንኮበር በምትባል የገጠር መንደር የተወለዱት የሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዝያ 2 ቀ 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን የቀብር ሥነሥርዓታቸውም ሚያዝያ 6 ቀን 2004 ዓ.ም በከፍተኛ መንግሥታዊ ሥነሥርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ቤ/ክ መፈጸሙ የሚታወስ ነው፡፡

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide