ነገ አርብ በአንዋር መስጅድ ከፍተኛ የዝምታ ተቃውሞ ይካሄዳል

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንዳለው በነገው ተቃውሞ ሙስሊሞች  አፋቸውን በመሸፈንና  የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ  ተቃውሞአቸውን ይገልጣሉ። “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም! የህዝብ ድምጽ ይከበር! ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄድ! ” የሚሉት መፈክሮች እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሎአል። ትናንሽ የኢትዮጵያን ባንድራ ገዝተው  በማውለብልብ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚያሳዩት ፍጹም ሰለማዊ የሆነ ተቃውሞ ብዙዎችን እያስደመመ ነው። የመለስ መንግስት ተቃውሞውን በሀይል ለመጨፍለቅ እያዘተ ነው። በውጭ አገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ክርስቲያኑም መብቱን ለማስከበር እንዲነሳ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide