ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትንበተመለከተ በዛሬው እለት ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራጨት ያስተዋወቀውየኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ ተመሳሳይፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ውስጥ አዋቂ ምንጮችን የጠቀሱዘገባዎች አመልክተዋል፤ቤተ ክህነት ለፊልሙ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጏ የተገለፀሲሆን ፤የሃይማኖት አባቶችም በሂደቱ ተዋናይ መሆናቸው ተመልክቶአል። ሐራ ተዋህዶ የተባለው የኦርቶዶክሳዊያን ድህረ ገፅ እንደዘገበው በኢትዮጵያቴሌቪዥን የተቀነባበረው ፊልም ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስን ጨምሮ በሶስትአባቶች ላይ አተኩሯል። ፓትሪያልክ አቡነ መርቆሪዮስን ከቀድሞው ስርአት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚልውንጀላ የጨመረው ፊልም ብፁእ አቡነ መልክአ ጻዲቅን ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ድጋፍ መስጠታቸውን በአሸባሪነት መፈረጁም ተመልክቶል:: በብጹ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያና በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ በብጹ አቡነ መልክአ ጻዲቅ እንዲሁም በብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ ላይ የተነጣጠረው ይህ ዶክመንተሪ ፊልም በቅርቡም ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው:: ብጹ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ነፍጥ ካነሱ ሀይሎች በተልይም ከግንቦት ...
Read More »በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው
ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ዋካ ውስጥ በአካባቢው ባለስልጣናትና በህዝቡመካከል የተፈጠረው ውዝግብ እየሰፋ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱንከስፍራው ለኢሳት የደረሰው ዜና አመለከተ። በዋካ ከተማ ሲካሄድ የነበረውእስራትና ፍተሻ በሳምንቱ መጀመሪያ በጦጫ ከተማ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ከክልልበመጡ ባለስልጣናት እሁድ እለት ለስብሰባ የተጠሩ የዋካ ከተማ ነዋሪዎችበስብሰባው ለመገኘት ባለመፍቀዳቸው ስብሰባው ተሰርዟል፤ በዐጎራባች በጦጫወረዳ የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለበርካታ ሰዎች መታሰር ምክንያትሆኗል፤የሃገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ሀያ ስድስት ሰዎች መታሰራቸውንከስፍራው የመጣው ዜና ያስረዳል። በበርካታ ሰዎች ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻኮምፒውተሮች የተወሰዱ ሲሆን፤በኮምፒውተሩ ውስጥ የዋካን ሕዝባዊእንቅንቅስቃሴ በተመለከተ በቪዲዮ የተቀነባበረ ዘገባ የተገኘባቸው ግለሰብ ወደእስር ቤት ተወስነዋል፤በኮምፒውተሮቹ ላይ በተደረገው ምርምራ ፋይሎችንከውስጥ ለማግኘት ለፖሊሶቹ አስቸጋር ሆኖ በመገኘቱ የአካባቢውባለስልጣናትን ለመገምገምና ውጥረቱን ለማርገብ የተላኩት የደቡብ ክልልከፍተኛ ባለስልጣናት አቶ አለማየሁ አሰፋ በኮምፒውተሮቹ ብርበራ ተሳታፊእንደነበሩ ተመልክቷል፤ኮምፒውተሩን አላስበረብርም ያሉ ኮምፒውተራቸውን አስረክበው ወደ እስር ቤት መላካቸውምታውቆአል፤እስረኞቹን ህዝቡ በነቂስ እየወጣ እንደሚጎበኝም የመጣው ዜናያብራራል።
Read More »በደቡብ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተነሳ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ የሰው ህይወት እያጠፋ መሆኑ ተገለጠ
በደቡብ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተነሳ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ የሰው ህይወት እያጠፋ መሆኑ ተገለጠ:: ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች ከሀገር ቤት እንዳስታወቁት ከሆነ በአርባ ምንጭ ብቻ 6 ሰዎች በማጅራት ገትር ወረርሽኙ ሞተዋል:: በዚህ መረጃ መሰረት በጨፌና በላሉ አካባቢዎችም ወረርሽኙ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን መግደሉን አመልክቶል:: በአዋሳ ከተማም በማጅራት ገትር ወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በሀደሌ ጤና ጣቢያ ...
Read More »የአለም ባንክ ባለሙያዎች በአለምአቀፍ ጨረታ ጉዳይ ላይ ምርመራ ማድረግ መጀመራቸው ተገለጠ
ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የጸረ ሙስና ኮሙሽን አቃቢህግ ሙስና ተፈጽሞበታል በማለት ክስ በመሰረተበትና ውሳኔ በተላለፈበት አለምአቀፍ ጨረታ ጉዳይ ላይ የአለም ባንክ ባለሙያዎች ምርመራ ማድረግ መጀመራቸው ተገለጠ:: ከሶስት ሳምንት በፊትም ሁለት የአለም ባንክ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ማነጋገራቸው ይታወቃል:: አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው የገጠር የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ዙሪያ በግዥና ሽያጭ ተፈጸመ የተባለው ሙስና በግዥና ...
Read More »ከፍተኛው ፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የሰጠበት የኢቲቪ ፊልም ቀረበ
ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ኢቲቪ ጂሀዳዊ ሀረካት በሚል ርእስ ሊያስተላለፍ የነበረውን ፊልም እንዳይተላለፍ ቢያግድም፣ እግዱ በሰአታት ውስጥ ታጥፎ ፊልሙ በኢቲቪ ተላልፎአል። ኢሳት ውሳኔው እንደተላለፈ የሙስሊም መሪዎች ጠበቃ የሆኑትን አቶ ተማም አባቡልጋን አነጋግሮ ፍርድ ቤቱ የእግድ ትእዛዝ ውሳኔ ማስተላለፉን ለማረጋጥ ችሎ ነበር ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢቲቪ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም ...
Read More »ዶላር ከገበያ መጥፋቱን ነጋዴዎች ይናገራሉ
ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ አምና የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ያገኘችው የውጭ ምንዛሬ አነስተኛ መሆን መንግስት ከሚከተለው ፖሊሲ ጋር ተደማምሮ የዶላር እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን ነጋዴዎች ይናገራሉ። በተለያዩ የአስመጪነት ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ዶላር በበቂ ሁኔታ ለማግኘት ባለመቻላቸው፣ የንግድ እንቅስቃሴያቸው ተዳክሟል። ዶላር ለማግኘት ኤልሲ ከፍተው ወረፋ መጠበቅ ከጀመሩ 5 ወራቸው መሆኑን ካፒታል ያነጋገራቸው የተለያዩ የኢንዱስትሪ ሃለፊዎች ...
Read More »ፕሬዚዳንት ኦባማ ኬንያውያን ወደ ግጭት እንዳይገቡ አስጠነቀቁ
ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፕሬዚዳንቱ በመጪው ወር በኬንያ የሚካሄደው ምርጫ ከግጭት ነጻ እንዲሆን በዩቲዩብ ባስታለፉት መልክት ገልጸዋል። ምርጫው ኬንያውያን ከጎሳና ከብሄር ይልቅ ወደ አንድነት የሚመጡበትን እድል እንደሚፈጥርላቸው ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። ” ኬንያውያን የሀይልን አማራጭ አስወግደው፣ ነጻና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ መፍቀድ አለባቸው። ልዩነቶች ካሉዋቸው በፍርድ ቤቶች መፍታት አለባቸው” በማለት የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ከሁሉም በላይ የኬንያ ህዝብ ከምርጫው በሁዋላ ወደ ...
Read More »በአክሱም ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት በርካታ ተማሪዎች ተጎዱ
ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዩኒቨርስቲው በተማሪዎች እና በአስተዳዳሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የተፈነከቱ ሲሆን የዩኒቨርስቲው መኪናዎች ተማሪዎች ባወረዱት የድንጋይ ናዳ ተሰባብረዋል። የመማሪያ ክፍሎች መስታውቶች እና አንዳንድ በግቢው ውስጥ የሚታዮ እቃዎችም ተሰባብረዋል። ተቃውሞው ባለፈው ቅዳሜ ጥር 25 የተነሳው ሁለተኛ ግጭት በምግብ መበከል ሲሆን ዩኒቨርስቲው ከትምህርት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ስራ ብዙ ጊዜ በማዋሉ እና የአስተዳደር ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት በታሰሩት የሙስሊም ኮሚቴዎች ላይ የሠራውን ፊልም ነገ ያስመርቃል።
ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ራሱን <<የጸረ-ሽብር ግብረ-ሀይል>>ብሎ የሚጠራው ገዥው ፓርቲ ያዋቀረው ወንጃይ ቡድን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር በታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ዚሪያ ያዘጋጀውን ዶክመንተሪ ነገ ማክሰኞ ምሽት እንደሚለቅ ኢቲቪ አስታወቀ። <<ጂሀዳዊ ሀረካት>>በሚል ርዕስ የተቀናበረው ይህ ፊልም <<ቦኮ ሀራም በ ኢትዮጵያ>> በሚል ንኡስ ርዕስ በሙስሊሞች የተጀመረው እንቅስቃሴ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ያለመ እንደሆነ በስፋት የሚተርክ ነው። የፊልሙ ማጠንጠኛ ...
Read More »መድረክ የአሰራር ችግር የለበትም ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ
ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እና የመድረክ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን የተናገሩት ኢሳት የግንባሩን ማንፌስቶ መጽደቅን አስመልክቶ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው። ዶ/ር ነጋሶ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ ግንባሩ ያካሄደው ጉባኤ የተሳካ ነበር። በቅርቡ አቶ ቡልቻ ሚዴቅሳና ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መድረክን አስመልክቶ የተናገሩት ችግር በአሁኑ ጉበኤ ተነስቶ ተነጋግራችሁበታልን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ዶ/ር ነጋሶ ...
Read More »