መድረክ የአሰራር ችግር የለበትም ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እና የመድረክ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን የተናገሩት ኢሳት የግንባሩን ማንፌስቶ መጽደቅን አስመልክቶ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው።

ዶ/ር ነጋሶ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ ግንባሩ ያካሄደው ጉባኤ የተሳካ ነበር። በቅርቡ አቶ ቡልቻ ሚዴቅሳና ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መድረክን አስመልክቶ የተናገሩት ችግር በአሁኑ ጉበኤ ተነስቶ ተነጋግራችሁበታልን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ዶ/ር ነጋሶ ችግሩ ተነስቶ እንዳልተወያዩበት ግለሰቦቹ በግላቸው የሰጡት አስተያየት ትክክል እንዳልነበር ገልጸዋል።

ኢሳት ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የነበረው የመድረክ ህገደንብ ጸደቀ በሚል የሰራው ዘገባ ትክክል እንዳልነበር የገለጡት ዶ/ር ነጋሶ፣ ህገ ደንቡ ከስድስት ወራት በፊት የጸደቀና አሁን ማሻሻያ እንደተደረገበት ተናግረዋል።