በደቡብ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተነሳ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ የሰው ህይወት እያጠፋ መሆኑ ተገለጠ

በደቡብ  ክልል በተለያዩ ከተሞች የተነሳ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ የሰው ህይወት እያጠፋ መሆኑ ተገለጠ::

ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች ከሀገር ቤት እንዳስታወቁት ከሆነ በአርባ ምንጭ ብቻ 6 ሰዎች በማጅራት ገትር ወረርሽኙ ሞተዋል::

በዚህ መረጃ መሰረት በጨፌና በላሉ አካባቢዎችም ወረርሽኙ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን መግደሉን አመልክቶል::

በአዋሳ ከተማም በማጅራት ገትር ወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በሀደሌ ጤና ጣቢያ በጊዜያዊ የድንኮን መኝታ ተዘጋጅቶ ሰዎች በህክምና እየተረዱ ይገኛል ተብሎል::

በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል የህክምና ርብርብና መድሀኒት ግን እንደሌለ ምንጮች አስታውቀዋል::