ፕሬዚዳንት ኦባማ ኬንያውያን ወደ ግጭት እንዳይገቡ አስጠነቀቁ

ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ፕሬዚዳንቱ በመጪው ወር በኬንያ የሚካሄደው ምርጫ ከግጭት ነጻ እንዲሆን በዩቲዩብ ባስታለፉት መልክት ገልጸዋል። ምርጫው ኬንያውያን ከጎሳና ከብሄር ይልቅ ወደ አንድነት የሚመጡበትን እድል እንደሚፈጥርላቸው ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

” ኬንያውያን የሀይልን አማራጭ አስወግደው፣ ነጻና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ መፍቀድ አለባቸው። ልዩነቶች ካሉዋቸው በፍርድ ቤቶች መፍታት አለባቸው” በማለት የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ከሁሉም በላይ የኬንያ ህዝብ ከምርጫው በሁዋላ ወደ አንድነት በመምጣት አገራቸውን መገንባት አለባቸው ሲሉ አክለዋል። ፕሬዚዳንት ኦባማ በአባታቸው ኬንያዊ መሆናቸው ይታወቃል።