በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በንቃት ተሳታፊ የነበሩት ሼህ ወርቁ ኑሩ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አረፉ

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በንቃት ተሳታፊ የነበሩት ሼህ ወርቁ ኑሩ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አረፉ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪነታቸው በደቡብ አፍሪካ ጆበርግ ከተማ ውስጥ የበረው አንጋፋው አገር ወዳድ ሼህ ወርቁ ኑሩ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት ተሳታፊ የነበሩት ሼህ ወርቁ ኑሩ በደቡብ አፍሪካ ስደተኞች ተወዳጅና አሰባሳቢ አባት ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላን የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011)ከድሬደዋ ወደ ቢሾፍቱ ከአንድ ወር በፊት ሲበር የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላን የምርመራ ውጤት ይፋ ተደረገ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት አውሮፕላን ምንም የቴክኒክ ችግር እንዳልገጠመው በምርመራ ተረጋግጧል። ነሐሴ 24/2010 ከረፋዱ 3 ሰአት ከ40 ደቂቃ ከድሬደዋ መነሳቱ የተገለጸው የበረራ ቁጥር 808 ዳሽ 6 አውሮፕላን፣ኤጀሬ በተባለ ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ይታወሳል። አብራሪዎቹንና የቴክኒክ ባለሙያዎቹን ...

Read More »

ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ማለቱ ተገቢ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011)የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመነበር አቶ ሌንጮ ለታ ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ማለቱ ተገቢ አይደለም አሉ። ወጣቱ በባዶ እጁ ታንክ ፊት በሚጋፈጥበት ጊዜ የኦነግ ሰራዊት የት ነበር ሲሉ አቶ ሌንጮ ለታ በሀገር ውስጥ ከሚሰራጨው አሀዱ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል። ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ከፈለግን በሀገር ውስጥ መኖር ያለበት ሰራዊት የመንግስት ብቻ መሆን አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነጉ ሊቀመንበር አቶ ...

Read More »

መንግስት ከፍተኛ ሹም ሽር ሊያደርግ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011) መንግስት በቀጣይ ሳምንት ከፍተኛ ሹም ሽር እንደሚያደርግ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የሚወስነው ረቂቅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለፓርላማ መላኩም ይፋ ሆኗል። በሚቀጥለው ሳምንት በፓርላማ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ሕግ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን ቁጥር ከ28 ወደ 20 ዝቅ እንደሚያደርገው ተመልክቷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት የጸደቀውና በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማ ጸድቆ ስራ ላይ እንደሚውል በሚጠበቀው የአስፈጻሚ አካላትን ...

Read More »

ኦነግ በምዕራብ ወለጋ የመንግስት ታጣቂዎችን ትጥቅ እያስፈታ ከመሆኑም በላይ ያገታቸው ነጋዴዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ኦነግ በምዕራብ ወለጋ የመንግስት ታጣቂዎችን ትጥቅ እያስፈታ ከመሆኑም በላይ ያገታቸው ነጋዴዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት “በኡላ ኖሌ” ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች መንግስት ያስታጠቃቸውን የአካባቢ ሚሊሺያዎችን ትጥቅ በማስፈታት የጦር መሳሪያዎችን ወስደዋል። የኦነግ ታጣቂዎች በዚሁ ወረዳ ጌጡ ገበየሁ የሚባል ታዋቂ ነጋዴን አፍነው የወሰዱ ሲሆን፤ ነጋዴው እስካሁን የደረሰበት አልታወቀም። ከኖሌ ...

Read More »

የቅዱስ ላሊበላን ገዳማት እድሳት በተሟላ መልኩ ለማከናወን 3 መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪዎች እና የከተማው መስተዳደር አስታወቁ፡፡

የቅዱስ ላሊበላን ገዳማት እድሳት በተሟላ መልኩ ለማከናወን 3 መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪዎች እና የከተማው መስተዳደር አስታወቁ፡፡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከ 10 ዓመት በፊት በአውሮፓ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ እና የባህል ተቋም-ዩኔስኮ ድጋፍ የተሰራው ጊዚያዊ መጠለያ በተገቢው መንገድ በሚነሳበት እና የዘመኑ የቴክኖሎጂ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ጥገና የሚካሄድበት መንገድ ጥናቱ መደረጉን የላሊበላ ...

Read More »

የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ኢትዮጵያን ጎበኙ።

የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ኢትዮጵያን ጎበኙ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ዛሬ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። ሚስተር ኮንቴ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መሪዎቹ-በሁለቱ አገራት የልማት ትብብር ስምምነቶች እንዲሁም በኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ሥምምነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ነገ ወደ ኤርትራ በማቅናት ...

Read More »

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ የነበሩት አነጋፋው አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን “ሶከር ኢትዮጰያ” ዘገበ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ የነበሩት አነጋፋው አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን “ሶከር ኢትዮጰያ” ዘገበ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) አሰልጣኝ ሥዩም በተጫዋችነት ዘመናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ሲሆን ፣ካሰለጠኗቸው ክለቦች መካከል ኢትዮጵያ ቡና፣ መድን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ አሰልጣኘ ሰዩም ባደረባቸው ህመም ...

Read More »

ወጣቱ አፍሪካዊ ቢሊየነር ማስክ በለበሱ ታጣቂዎች ተጠለፈ።

ወጣቱ አፍሪካዊ ቢሊየነር ማስክ በለበሱ ታጣቂዎች ተጠለፈ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ቢቢሲ የታንዛኒያ ፖሊስን ጠቅሶ እንደዘገበው የ43 ዓመቱ ቢሊየነር መሀመድ ደዋይ በዳሬሰላም ካረፈበት ሆቴል ነው የታገተው። ቢሊየነር መሀመድ ደዋይ እንደወትሮው በዳሬሰላም ስዋነኪ ሆቴል ውጭ በሚገኝ ጅምናዚየም የማለዳ ስፖርት ሊሰራ ሲሄድ ነው ፊታቸውን የተሸፈኑ ታጣቂዎች ጠልፈው የወሰዱት። ከወንጀሉ ጋር በተገናኘ ሶስት ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ሁለቱ አጋቾች የውጭ ...

Read More »

መንግስት ኦነግን ትጥቅ ያስፈታል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011) መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲል ኦነግን ትጥቅ ለማስፈታት እንደሚገደድ የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ መንግስት የታጠቁ ሃይሎች በሃገር ውስጥ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ ሁለት መንግስት እንዲኖር አይፈቅድም ብለዋል። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማድረግ የወሰነ ሃይል በመሳሪያ ጭምር እንደማይንቀሳቀስ የገለጹት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኦነግ ትጥቅ ለመፍታት አልተስማማንም የሚለውን አቋሙን ...

Read More »