በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ የነበሩት አነጋፋው አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን “ሶከር ኢትዮጰያ” ዘገበ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ የነበሩት አነጋፋው አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን “ሶከር ኢትዮጰያ” ዘገበ።
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) አሰልጣኝ ሥዩም በተጫዋችነት ዘመናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ሲሆን ፣ካሰለጠኗቸው ክለቦች መካከል ኢትዮጵያ ቡና፣ መድን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ አሰልጣኘ ሰዩም ባደረባቸው ህመም ሳቢያ ላለፉት ወራት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ሆስፒታሎች ከፍተኛ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል ። የኢሳት ባልደረቦች በአሰልጣኝ ሥዩም አባተ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።