የቅዱስ ላሊበላን ገዳማት እድሳት በተሟላ መልኩ ለማከናወን 3 መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪዎች እና የከተማው መስተዳደር አስታወቁ፡፡

የቅዱስ ላሊበላን ገዳማት እድሳት በተሟላ መልኩ ለማከናወን 3 መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪዎች እና የከተማው መስተዳደር አስታወቁ፡፡
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከ 10 ዓመት በፊት በአውሮፓ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ እና የባህል ተቋም-ዩኔስኮ ድጋፍ የተሰራው ጊዚያዊ መጠለያ በተገቢው መንገድ በሚነሳበት እና የዘመኑ የቴክኖሎጂ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ጥገና የሚካሄድበት መንገድ ጥናቱ መደረጉን የላሊበላ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ለኢሳት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባሏት ቅርሶች ልክ የጥበቃ ፣የደህንነትም ሆነ የጥገና ባለሙያዎችን የሚያፈሩ ኮሌጆችንም ሆነ ዩኒቨርስቲዎችን- በቤተክርስቲያኗም ሆነ በመንግስት ደረጃ ማቋቋም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ምሁራን ያስገነዝባሉ።