ከአዲስ አበባ ታፍሰው ጦላይ ታስረው ከነበሩት ወጣቶች መካከል 1 ሺህ 174ቱ ተለቀቁ

ከአዲስ አበባ ታፍሰው ጦላይ ታስረው ከነበሩት ወጣቶች መካከል 1 ሺህ 174ቱ ተለቀቁ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) በቡራዩ ከተማ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ እና እሱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች በጅምላ ተይዘው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ከአንድ ወር በላይ ታስረው መቆየታቸው ይታወቃል። ፖሊስ ወጣቶቹ በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ መቆየታቸውን የገለጸ ሲሆን፤ ወጣቶቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ይህን ...

Read More »

አሜሪካና እንግሊዝ ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጋር በተያያዘ በሳኡዲ አረቢያ የተዘጋጀውን የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ረግጠው ወጡ።

አሜሪካና እንግሊዝ ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጋር በተያያዘ በሳኡዲ አረቢያ የተዘጋጀውን የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ረግጠው ወጡ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሳኡዲ አረቢያ ንጉሳውያን ቤተሰቦችን የሚተች ጽሁፎችን በዋሽንግተን ፖስት እና በተለያዩ ታላላቅ ሚዲያዎች ላይ በማውጣት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ካሾጊ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ነበር ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ለማስፈጸም በቱርክ ኢስታምቡል በሚገኘው የሳኡዲ ኤምባሲ እንደገባ በዚያው የቀረው። ያን ተከትሎ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) ባለፈው ወር መጀመሪያ በጅምላ ታፍሰው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ተወስደው የነበሩ ከ1ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ መለቀቃቸው ተገለጸ። ለወጣቶቹ ስልጠና ተሰጥቶ መለቀቃቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማጓጓዝ ስራ መጀመሩን አስታውቋል። ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳውና ህገመንግስታዊ መብቶችን የጣሰ ነው የተባለው የአዲስ አበባ ወጣቶች እስርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያለአግባብ የታሰሩ ከነበሩም ለለውጡ የከፈሉት መስዋዕትነት ...

Read More »

ሁለት የሰብዓዊ መብትና የህግ ባለሙያዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011)የአዲስ አበባ ወጣቶችን በማደራጀት ክስ የተመሰረተባቸው ሁለት የሰብዓዊ መብትና የህግ ባለሙያዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና ሚካዔል መላከ አዲስ አበባ ከሌላ አካባቢ በመጣ ሰው አትተዳደርም የሚል ቅስቀሳ በማድረግና የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሲያደራጁ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። የፖሊስ ክስ ላይ ለዚህ እንቅስቃሴ የሚረዳ ግንኙነት ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር መደረጉን የሚያመለክት ነው። የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማደራጀት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ሌሎች ...

Read More »

የስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊየን ተጠጋ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊየን መጠጋቱን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ። ከጥር እስከ ነሐሴ ብቻ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ከ36 ሺ በላይ መሆኑን የገለጸው ይህው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር መከፈቱን ተከትሎም የስደተኞቹ ቁጥር መጨመሩን አመልክቷል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ ነሐሴ 31/2018 በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር 905ሺ 831 መድረሱን የገለጸው የተባበሩት ...

Read More »

ለውጡን ለማደናቀፍ የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተመንግስት ተልከዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) የታጠቁ ወታደሮችን ወደ ቤተመንግስት የላኩት አካላት ለውጡን ለማደናቀፍ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። በወቅቱ ለድርጊቱ የጥንቃቄ ምላሽ ባይሰጥ ኖሮ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ የሚከታት ነበር ሲሉም ገልጸዋል። ሆኖም ሁሉም ወደ ቤተመንግስት የተንቀሳቀሱት ወታደሮች ይህንን ግንዛቤ ጨብጠው ነበር ለማለት እንደሚያስቸግርም አመልክተዋል። መስከረም 30 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ቁጥራቸው 250 የሚሆን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነትጥቃቸው ወደ ቤተመንግስት ያደረጉት ጉዞ ...

Read More »

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011)አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሌሎች ተጨማሪ ሶስት ግለሰቦችም ሹመት ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲወጡ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው የተሾሙት አቶ አባዱላ ገመዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ከተሰናበቱ ወዲህ ስፍራው ሰው ሳይሾምበት ቆይቷል። አሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ...

Read More »

በደቡብ ኢትዮጵያ በወረርሽኝ 20 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011) በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋና ወላይታ በወረርሽኝ 20 ሰዎች መሞታቸው ታወቀ። በጎፋ ዳራማሎ ወረዳ በትክትክ ወረርሽኝ 10 ሰዎች ሲሞቱ በወላይታ ኦፋ ወረዳ የቢጫ ወባ በሽታ ተከስቶ በተመሳሳይ 10 ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወረርሽኝ ደረጃ የተከሰቱትን እነዚህን በሽታዎች ለመቆጣጠር በመንግስት በኩል አፋጣኝ ርምጃ ካልተወሰደ የከፋ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ተብሏል። ትክትክ የተሰኘው በሽታ ከምድር ገጽ ላይ ጠፍቷል ከተባለ ዓመታት ተቆጥሯል። ...

Read More »

በአየሁ እርሻ ልማት የሰብአዊ መብት ረገጣ እየተፈጸመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011) በአየሁ እርሻ ልማት ሰራተኛና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛና የሰብአዊ መብት ረገጣ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ። በኢትዮ-አግሪ ሴፍት ኩባንያ ስር ያለው የአየሁ እርሻ ልማት በአካባቢው የተፈጥሮ ሃብትና ምርት እየተጠቀመ ሰራተኞቹ ግን ለከፍተኛ ድህነትና እንግልት መዳረጋቸውን ነው የሚናገሩት። የሼህ አላሙዲን ኩባንያ ነው የተባለው ኢትዮ-አግሪ ሴፍት በእርሻ ልማቱ ከ13 አመት በታች የሆኑ ሕጻናትን ጉልበትም እየበዘበዘ መሆኑም ታውቋል። የአየሁ እርሻ ልማት ...

Read More »

በአፋር ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011)ሰመራን ጨምሮ በአፋር ዘጠኝ ወረዳዎች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። የክልሉ አመራሮች ለውጡ ለአፋር ህዝብ እንዳይደርስ አድርገዋል፣ የአፋር ህዝብ በሃብቱ እንዳይጠቀም ተደርጓል፣የህወሃት ጣልቃ ገብነት በአፋር ክልል ይቁም የሚሉ መልዕክቶች የተላለፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በሌሎቹም የክልሉ ወረዳዎች እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል። በአፋር ክልል የህወሀት ባለሀብቶች የጨውና የማዕድን ስራዎችን መቆጣጠራቸው በአፋር ወጣቶች ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። በቅርቡ ከየወረዳው የተወከሉ ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ...

Read More »