ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሊሾሙ ነው

ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሊሾሙ ነው ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) የብአዴን ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አምባቸው በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚሾሙ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ዶ/ር አምባቸው ፕሬዚዳንት ሆነው ለማገልገል ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውንና ፓርቲያቸው ጥያቄያቸውን ላለመቀበል ተቸግሮ እንደነበር የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

Read More »

ትምህርት ሚኒስቴር ለሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ስብሳቢ ሾመ

ትምህርት ሚኒስቴር ለሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ስብሳቢ ሾመ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርስቲው ቦርድ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ማዕረግ የኦሮምያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ ሾሟቸዋል። ቀደም ብለው በቦርድ ሰብሳቢነት ይሰሩ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው በቀረበባቸው የተለያዩ ወንጀሎች ምክንያት ከኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴነት ታግደው የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡ ጅማ በተደረገው የድርጅቱ ጉባኤም ላይ ...

Read More »

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከእስር ቤት ለማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸውን ፖሊስ ገለፀ። አቶ አብዲ መሀመድ በእስር ቤት የሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ተናገሩ።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከእስር ቤት ለማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸውን ፖሊስ ገለፀ። አቶ አብዲ መሀመድ በእስር ቤት የሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ተናገሩ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) በጅግጅጋና አካባቢው ለተቀሰቀሰው የእርስበርስ ግጭቶች፣ የጅምላ መፈናቀል፣ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል፣ ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ በመስጠት የዜጎችንና የአገር ሰላምን አውከዋል ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ...

Read More »

የአውሮፓ ኅብረት ያቀረበውን የስደተኞች ዕቅድ የሊቢያ መንግስት ውድቅ አደረገ

የአውሮፓ ኅብረት ያቀረበውን የስደተኞች ዕቅድ የሊቢያ መንግስት ውድቅ አደረገ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአውሮፓ ኅብረት ከኅብረቱ ግዛት ውጪ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያን ለማቋቋም ያቀረበውን ዕቅድ እንደማይቀበሉት የሊቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስት አስታወቁ። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የጣሊያን መንግስት የስደተኞች ፍልሰት ቁጥጥር እንዲደረግበት ላቀረበው ሃሳብ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ቁጥጥሩን ለማጥበቅ የወሰኑትን ውሳኔ ተከትሎ የተወሰደ ነበር። ነገር ግን የሊቢያው ...

Read More »

ህወሃት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱን ቁጥር ከ11 ወደ 9 ዝቅ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 9/2011) የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ከ11 ወደ 9 ዝቅ እንዲል ማድረጉን አስታወቀ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ቁጥሩን ዝቅ እንዲል ያደረገው ከዚህ በፊት ያልደርጅቱ ጉባኤ ፈቃድ ቁጥሩን ከፍ በማደረጉ ነው ተብሏል። በዚሁ መሰረት በቅርቡ የስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ በየነ መክሩ እና ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል እንዲቀነሱ ተደረገዋል። ሕወሃት የስራ አስፈጻሚውን ቁጥር ሕገ ደንቡን በመጣስ ከዘጠኝ ወደ ...

Read More »

አብዲ ኢሌ ከእስር ቤት ሊያመልጡ ነበር ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከእስር ቤት ሊያመልጡ ሙከራ ማድረጋቸውን  ፓሊስ ለፍርድ ቤት ተናገረ። ፓሊስ በአቶ አብዲ ኢሌ ላይ ባደረገው ምርመራም በሶማሌ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ መሆናቸውን ማመናቸውንና ለዚህም ይቅርታ መጠየቃቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል። የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ኢሌ መሃመድ ክልሉን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ክልሉን እንደፈለጋቸው ሲያሽከረክሩና ተቆጣጣሪ የሌላቸው በሚመስል መልኩ ዜጎችን በመግደል፣በማሰርና ክልሉን ለቀው እንዲሰደዱ በማድረግ ...

Read More »

አቶ ታዬ ደንደአ ወደ ኦዴፓ ጽሕፈት ቤት ተዛወሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 9/2011) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ ወደ ኦዴፓ ጽሕፈት ቤት ተዛወሩ። ለሶስት ወራት ከቆዩበት የፌደራል የሃላፊነት ቦታ ተነስተው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት  የሕዝብ ግንኙነት ክፍል በምክትል ሃላፊነት እንዲሰሩ መውሰኑን ለማወቅ ተችሏል። አቶ ታዬ ደንደአ ከፌደራል መስሪያ ቤት ወደ ክልላዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዲዛወሩ የተደረገበት ምክንያት ባይታወቅም በአዲሱ የኦዴፓ መዋቅራዊ አደረጃጀት ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) አቶ ሔኖክ አክሊሉና ሚካኤል መላከ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ። የአዲስ አበባ ከተማ እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ ሙሉ መብት እንዲሰጣት በመንቀሳቀሳቸው መታሰራቸውን የገለጸው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከፍልስጤም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ስልጠና ወስደዋል የሚል ክስም እንደቀረበባቸው አመልክቷል። ከትላንት በስቲያ አዲስ አበባ ላይ ተይዘው ትላንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና አቶ ሚካኤል መላከ በአስቸኳይና ...

Read More »

በውስጥም በውጭም ብዙ ችግሮች እያጋጠሙዋቸው እንደሆነ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ

በውስጥም በውጭም ብዙ ችግሮች እያጋጠሙዋቸው እንደሆነ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ፣ እርሳቸውን በግል እንዲሁም የለውጡ ሂደት እያጋጠመው ያለውን ፈተና ዘርዝረው አቅርበዋል። ስራቸውን የሚሰሩት ህይወታቸውን አስይዘው እንደሆነ የገለጹት ጠ/ሚኒስትር አብይ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችም ሆኑ በቅርቡ ወታደሮች ወደ ቤተመንግስት የሄዱበት አካሄድ የግል ህይወታቸውን አደጋ ውስጥ ...

Read More »

የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ- ከድርጅቱ ሊቀመንበር ከአቶ ኦርዲን በድሪ ጋር እየተጋጩ መሆኑ ተነገረ።

የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ- ከድርጅቱ ሊቀመንበር ከአቶ ኦርዲን በድሪ ጋር እየተጋጩ መሆኑ ተነገረ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) ፕሬዚዳንቱ አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ከድርጅታቸው ሊቀመንበርነት መነሳታቸውን ተከትሎ የክልሉ ምክር ቤት ኃላፊነታቸውን ባለማንሳቱ ምክንያት- አዲስ ከተሾሙት የሐብሊ ሊቀመንበር ከአቶ ኦርዲ በድሪ ጋር በተደጋጋሚ ግዜያት እንደሚጣሉ የድርጅቱ የቅርብ ምንጮች ተናግረዋል። አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ የክልሉን ካቢኔ አባላት ለአንድ ...

Read More »