ትምህርት ሚኒስቴር ለሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ስብሳቢ ሾመ

ትምህርት ሚኒስቴር ለሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ስብሳቢ ሾመ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርስቲው ቦርድ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ማዕረግ የኦሮምያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ ሾሟቸዋል።
ቀደም ብለው በቦርድ ሰብሳቢነት ይሰሩ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው በቀረበባቸው የተለያዩ ወንጀሎች ምክንያት ከኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴነት ታግደው የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡ ጅማ በተደረገው የድርጅቱ ጉባኤም ላይ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሳይጠቆሙ ቀርተዋል።