ህወሃት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱን ቁጥር ከ11 ወደ 9 ዝቅ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 9/2011) የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ከ11 ወደ 9 ዝቅ እንዲል ማድረጉን አስታወቀ።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ቁጥሩን ዝቅ እንዲል ያደረገው ከዚህ በፊት ያልደርጅቱ ጉባኤ ፈቃድ ቁጥሩን ከፍ በማደረጉ ነው ተብሏል።

በዚሁ መሰረት በቅርቡ የስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ በየነ መክሩ እና ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል እንዲቀነሱ ተደረገዋል።

ሕወሃት የስራ አስፈጻሚውን ቁጥር ሕገ ደንቡን በመጣስ ከዘጠኝ ወደ 11 ቁጥሩን ከፍ ሲያደርግ በድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔ አለመሆኑ ተነገሯል።

በድርጅቱ ህገደንብ መሰረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን የመጨመርም ሆነ የመቀነስ ስልጣን ያለው የድርጅቱ ጉባኤ ብቻ ነው። እናም ቁጥሩ ሲጨምር በድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔ ባለመሆኑ የማስተካከያ ውሳኔው መነሻ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

በዚሁ መሰረት በቅርቡ የስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ በየነ መክሩ እና ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል እንዲቀነሱ ተደረገዋል።

ድርጅቱ በቅርቡ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ሲመርጥ ለምን የድርጅቱን ጉባኤ እንደጣሰ የተገለጸ ነገር የለም።

ሁለቱ ስራ አስፈጻሚዎች በምን መስፍርት እንደጠቀነሱም የተባለ ነገር የለም።

ማስተካከያ ተደረገ ከተባለ በኋላ የቀሩት የስራአስፈጻሚ አባላት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፥ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር፥ አቶ ጌታቸው ረዳ፥ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፥ ዶክተር አብረሃም ተከስተ፥ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፥ አቶ ጌታቸው አሰፋ፥ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ፥ አቶ ዓለም ገብረዋህድ ናቸው።

ከ11 ወደ 9 ዝቅ እንዲል ከተደረጉ ስራአስፈጻሚ አባላት መካካል የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው የሚገኙትና በወንጀል የሚፈለጉት የቅድሞው የድህንነት አባል አቶ ጌታቸው አሰፋ ይገኙበታል።