የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ አባላት እንቅስቃሴያቸውን በጎንደር ከተማ ለህዝብ ማሳወቃቸው ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) ዛሬ በጎንደር ከተማ 1ሺህ በላይ ነዋሪ በታደመበት ስብሰባ፣ የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ አባላት እንቅስቃሴያቸውን ለህዝብ ማሳወቃቸው ተገለጸ። በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መንግስት እየተዋከቡ የሚገኙትና በብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ድጋፍ ያጡት የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባለት በብአዴን የተከለከለ ስብሰባ ዛሬ በጎንደር ከተማ ከህዝቡ ጋር ማካሄዳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነት መኮንን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑዌር ወጣቶች ህብረት የደቡብ ሱዳን መልዕክተኛን ሹመት ተቃወመ

ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑዌር ወጣቶች ህብረት የደቡብ ሱዳን መልዕክተኛ አድርጎ የሾማቸውን አምባሳደር ተቃወመ። የሃገሪቱ መንግስትም የመልዕከተኛው ጀምስ ሞርጋንን ሹመት በአስቸኳይ እንዲሰርዝ ህብረቱ መጠየቁን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ሃሙስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። በልዩ መልዕክተኛው ላይ ተቃውሞ ያቀረበው የኑዌር ወጣቶች ህብረት አምባሳደር ጀምስ ሞርጋን የተባበሩት ኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ከተባለ አማጺ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ምክንያት ማቅረቡንም ጋዜጣው አስነብቧል። ...

Read More »

አቶ ሌንጮ ለታ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ አንድነት መንገድ የጠረገ መሆኑን ገለጹ

ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ የኦሮሞ አንድነት ያረጋገጠና ለእውነተኛ ኢትዮጵያ አንድነት መንገድ የጠረገ እንቅስቃሴ ነው ሲሉ አቶ ሌንጮ ለታ ገለጹ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባት መስራችና ምክትል ዋና ጸሃፊ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ይህንን የተናገሩን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ለስራ ጉዳይ ከአውሮፓ ወደ ዋሽንግተን ብቅ ያሉትና ...

Read More »

ኢትዮጵያ ለውጭ ንግድ የሚሆን ጥራጥሬ ማቅረብ አለመቻሏ የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ

ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋን ተከትሎ ሃገሪቱ ለወጪ ንግድ የሚሆን የጥርጣሬ ምርት ማቅረብ አለመቻሏን የንግድ ሚኒስቴር ሃሙስ አስታወቀ። ድርቁ ባስከተለው ጉዳትም ባለፉት ሰባት ወራት የወጪ ንግዱ የ126 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱን የሚንስቴሩ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል። ይኸው በስድስት ክልሎች ጉዳትን እያደረሰ ያለው አደጋ ሃገሪቱ ከግብርና ምርቶች በምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን ያሳደረ ሲሆን የተጠበቀውን ...

Read More »

በሰሜንና ደቡብ ወሎ የሚካሄደው የአሽከርካሪዎች አድማ ቀጥሎአል

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት ከሰዓት በሁዋላ በወልድያ የተጀመረው የታክሲ እና አውቶቡስ አሽከርካሪዎች አድማ በደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ውርጊሣ፣ ውጫሊ ቆቦ እና አላማጣ መስመሮችም እየተካሄደ ነው። በወልድያ ዛሬ የከተማው ባለስልጣናት ታርጋ ሲፈቱና ባለሀብቶችን ሰብስበው ሲያነጋግሩ አርፍደዋል። ባለሃብቶቹ ሾፌሮቻቸውን መክረው ስራ እንዲያስጀምሩ ፣ ስራ ካልቸጀመሩ ግን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ባለስልጣናቱ ለማስፈራራት ቢሞክሩም፣ ባለሀብቶቹ ግን ” የምትፍልጉትን አድርጉ፣ የወሰዳችሁትን ታርጋም ...

Read More »

ኦህዴድ 3 ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ያለማእከላዊ ኮሚቴው እውቅና አሰናበተ

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ አቶ ዳባ ደበሌ ፣ አቶ ሰለሞን ኩቹንና አቶ ለሲሳ ሀዩን ለማእከላዊ ኮምቴው አቅርቦ ሳያስጸድቅ መሆኑ ተረጋግጧል። በኦሮሚያ ከተከሰተው ህዝባዊ አመጽ ጋር ተያይዞ ለዘብተኛ አቁዋም አሳይተዋል በሚል ከተገመገሙት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አቶ ዳባ ደበሌ የኦህዴድ/ኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባልና የኦህዴድ የጽ/ቤት ሀላፊ፣ አቶ ሰለሞን ኩቹ የጸጥታና አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ እንዲሁም አቶ ለሲሳ ...

Read More »

የወልቃይት የአማራ ማንነት ይከበርልን በማለት ጥያቄ ያነሱ ተወላጆች በጎንደር ስብሰባ አካሄዱ

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጥያቄ አቅራቢዎች ተወካይ ባደረጉት ንግግር፣ የወልቃይት ህዝብ ላለፉት 24 አመታት ሳይፈልግ ማንነቱን ተነጥቋል ብለዋል። ያለፈቃዳቸው ወደ ትግራይ ክልል መዛወራቸውን ሲቃወሙ የነበሩ ሰዎች፣ ሌሊት እየተወሰዱ በመገደላቸው፣ የወልቃይት ሴቶች ባል አልባ ሆነዋል ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ክልል መሬታችንን፣ ሃብታችንን ዘርፏል፣ ህዝባችንንም አዋርዷል ያሉት ተወካዩ፣ በትግራይ ክልል እስር ቤት የታሰሩት አብዛኞቹ የወልቃይት ሰዎች ናቸው ብለዋል። ...

Read More »

በረሃቡ ምክንያት ከሰሜን ወሎ ተሰደው ደብረብርሃን ከተማ የሰፈሩት ዜጎች በሃይል ወደ ቀያቸው ተወሰዱ

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደብርሃን ከተማ እና አካባቢዋ የነበሩትን ከሰሜን ወሎ ተሰደው በመምጣት በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር የእለት እንጀራቸውን ለማግኘት ሲጥሩ የነበሩ ስደተኞችን የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች‹‹ ማረፊያ አዘጋጅተናል››በማለት ከሰበሰቡና በአንድ ቦታ ካከማቹ በኋላ አርብ የካቲት18/2008 ዓም. ከ70 በላይ የሚሆኑ ተጎጂዎችን በአንድ አውቶብስ ከነልጆቻቸው በማሳፈር ወደ መጡበት መልሰዋቸዋል፡፡ ወደ አውቶቡስ በሚያስገቧቸው ሰዓት ‹‹የት ልትወስዱን ነው ?›› ብለው ...

Read More »

የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከ በጄኔቭ ውይይት ተካሄደ

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ አለማቀፍና አገር በቀል የሲቪክ ድርጅቶች የተውጣጡ በኢትዮጵያ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ድርጅቶች፣በአገሪቱ ስለሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ገለጻ አድርገዋል። በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ፣በኦሮምያ እና በአገሪቱ ስለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል።በውይይቱ ላይ ከተገኙት መካከል ዶ/ር አወልንና ዶ/ር ተድላ ደስታን አነጋግረናቸዋል። ...

Read More »

የውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተባባሰ ነው ተባለ

ኢሳት (የካቲት 23 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት አጋጥሞት ያለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተባባሰ ባለበት ወቅት ባለፉት ስድስት ወራት ከውጭ ንግድ የተገኘው ገቢ ማሽቆልቆሉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ረቡዕ አስታወቀ። ሃገሪቱ ከውጭ ንግድ የምታገኘው ገቢ እየቀነሰ መምጣቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችቱ ላይ ተፅዕኖ ከማሳደሩ በተጨማሪ በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ጫናን እንደሚፈጥር የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራቶች ከውጭ ንግድ ገቢ ...

Read More »