የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚሰው እርምጃ እንዲቆም አሳሰበ

ኢሳት (ጥር 13 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየወሰደ ያለውን የሃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አርብ አሳሰበ። በተቋሙ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ከፍተኛ ባለሙያዎች መንግስት እየወሰደ ያለውን ድርጊት በመቃወም የጋራ መግለጫን ያወጡ ሲሆን የጸጥታ ሃይሎች እርምጃም በአፋጣኝ እልባትን እንዲያገኝ ጠይቀዋል። በፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎች ድርጊትም ...

Read More »

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ ምልክት ማድረግ ሊጀመር ነው

ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወይም ኢንሳ አማካኝነት ሲካሄድ የከረመው የሁለቱን አጎራባች አገራት ድንበር የአየር ላይ ፎቶ ወይም erial photo acquisition የመስራቱ ስራ ለሁለት ሳምንት ከተቋረጠ በሁዋላ፣ ሰሞኑን እንደገና የተጀመረ ሲሆን፣ በድንበሩ ላይ ምልክት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የደህንት መስሪያ ቤት ምንጮች ገልጸዋል። በአሁኑ ሰአት በድንበሩ ዙሪያ መሬት ላይ ምልክት የማድረግ በእንግሊዝኛ pre ...

Read More »

ድንገተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ይነሳል የሚል ስጋት የገጠመው መንግስት ማረጋጊያ ያላቸውን እርምጃዎች ሊወስድ ነው

ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታህሳስ ወር መግቢያ ላይ በጦር ሃይሎች አካባቢ በሚገኝ አንድ የደህንነት ጽ/ቤት ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑ የደህንነት አባላት በተሳተፉበት ስብሰባ ላይ ከማስተር ፕላኑ፣ ከኑሮ ውድነቱና ከሌሎችም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ ህዝቡ በድንገት ወደ አደባባይ ሊወጣ ይችላል የሚል መልእክት ተላልፏል። በስብሰባው ላይ ለችግሩ መፍትሄ ያስገኛሉ የተባሉ በርካታ የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበዋል። የጦር መሳሪያዎች ...

Read More »

የአለማቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ከአቅም በላይ ነው ቢሉም መንግስት እያጣጣለው ነው

ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪዩተርስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ አስከፊ በተባለው ረሃብ 400 ሺ ህጻናት ከፍተኛ አደጋ አንዣቦባቸዋል። አንድ አስረኛ የሚሆነው ህዝብ ራሱን መመገብ በማይችልበት ደረጃ መደረሱን ዘጋባው አመልክቶ፣ የአለማቀፉ ማህበረሰብ የሚሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን ችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል። በአሜሪካ የህጻናት አድን ድርጅት ፕሬዚዳንት ካሮሊን ማይልስ አፋርና አማራ ክልሎችን መጎብኘታቸውን ለዜና ምንጩ ገልጸው፣ በምግብ ...

Read More »

በኦሮምያና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ

ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥር 13 ቀን 2008 ዓም በአውስትራልያ ብሪዝቤን ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በአይነቱ ልዩ የተባለለት ነው። ህብረ ብሄራዊነት በተንጸባረቀበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳታፊዎቹ በጋራ የኢትዮጵያን መንግስት ያወገዙ ሲሆን፣ በተለይም ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ ማፈናቀልና እስራት፤ በጎንደር ገበሬዎችን በማፈናቀል ለሱዳን መሬት ቆርሶ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ...

Read More »

የብሪታንያ መንግስት እንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥሪ እንዲያቀርብ ሪፕሪቭ የተሰኘ ተቋም ጠየቀ

ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) የብሪታኒያ መንግስት ከቀናት በኋላ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔን በመጠቀም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥሪዎን እንዲያቀርብ ሪፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሃሙስ አሳሰበ። በዚሁ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የብሪታኒያውን የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሚኒስትር የሆኑት ጀምስ ዱድሪጅ ወደ አዲስ አበበ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሃላፊው ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ ተከትሎም የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ...

Read More »

ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንደሚቆም ገለጹ

ኢሳት ዜና (ጥር 12 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በኢትዮጵያ መንግስትና በጸጥታ ሃይሎቹ በህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፅኑ ማውገዙን ተከትሎ የአውሮፓ  ህብረት ፓርላማ አባል ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት ምንጊዜም ከኢትዮጵያውያን ጎን እንደሚቆም ገለጹ። የህብረቱ ፓርላማ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ 140 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እንዲያይ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን  አመጽና ከግንቦት 2007 ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደከፋ የረሃብ ቀውስ ሊቀየር እንደሚችል ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 12 ፥2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ የሚገኘው የድርቅ አደጋ በተያዘው የፈረንጆች አዲስ አመት ወደከፋ የረሃብ ሰብዓዊ ቀውስ ሊለወጥ እንደሚችል ካሪታስ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የሰብዓዊ እርዳታ ተቋም ሃሙስ አሳሰበ። በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ጉዳትን እያደረሰ የሚገኘው ይኸው የድርቅ አደጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ አለም አቀፍ ርብርብ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ መድረሱንም ድርጅቱ ገልጿል። በሃገሪቱ ያለው የድርቅ አደጋ አስከፊ ገጽታን ከመያዙ በፊት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ

ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የመከረው የአውሮፓ ፓርላማ ባሰራጨው መግለጫ በኢትዮጵያ የመንግስት ሃይሎች በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን ግድያ አውግዟል። በዚሁ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ከተገደሉ ሰዎች በተጨማሪ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የአውሮፓ ፓርላማ ገልጿል። በተለያዩ አለም አቅፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በኢትዮጵያ የፓርቲ አካላት ይፋ የተደረገው የ 140 በላይ ...

Read More »

የአውሮፓ ፓርላማ በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ የእርምጃ ሃሳቦችን አጸደቀ

ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) የአውሮፓ ፓርላማ በወቅታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ለሰዓታት የፈጀ ክርክርን በማካሄድ ለውይይት የቀረቡ በርካታ የእርምጃ ሃሳቦችን ሃሙስ አጸደቀ። ይኸው የፓርላማ አባላቱ ያጸደቁት ሃሳብ የተለያዩ አንቀጾች ሲኖሩት የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ መወሰድ ስለሚገባው እርምጃዎችና ፖሊሲዎች ግብዓት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ተከትሎ የተካሄደው ይኸው ልዩ ...

Read More »