የአማራ ክልል የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎቸን አቀረቡ

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ክልሉ በሚያደርገው 5ኛ ዙር 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ዞኖች የተወከሉ የምክር ቤት አባላት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥያቄዎችን ጽፈው ለውይይት አቅርበዋል። ጥያቄዎቹ፣ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ጸጥታና አስተዳዳር የተመለከቱ ናቸው። የምክር ቤት አባላቱ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት መፈጠሩንና ችግሩ አለመቀረፉን፣ በእርዳታ የሚሰጠው በቆሎ በቂ አለመሆን፣የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በድርቅ ምክንያት ...

Read More »

አንድ ኢትዮጵያዊ በአውሮፕላን ኮንቴይነር ተደብቆ ስዊድን ገባ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ወደ ስዊድን ይጓዝ በነበረ አውሮፕላን ውስጥ በኮንቴይር ተደብቆ ውስጥ ተደብቆ ወደሃገሪቱ የገባ አንድ ኢትዮጵያዊ በስዊድን ጥገኝነት ጠየቀ። ከ10 ሰዓት አስቸጋሪ በረራ በኋላ በስዊድን የደረሰ እና ማንነቱ እስካሁን ድረስ ይፋ ያልተደረገው ኢትዮጵያዊ በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘቱን ስቶክሆልም ፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ካሪና ካገርለንድ ኤክስፕረስ ለተሰኘ ጋዜጣ ገልጸዋል። በሃገሪቱ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀው ኢትዮጵያዊ የተደበቀበት የእቃ ...

Read More »

13 ሰዎች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ፈጥራችኋል በሚል የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2008) በአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄን ለመሳተፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርጋችኋል የተባሉ 13 ሰዎች የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ከአራት ወር በፊት ከአርባ ምንጭ ከተማ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉት እነዚሁ ተከሳሾች የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ እንደሆነ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ክሱን ሰዎች ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው አቃቤ ህግ ...

Read More »

አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች የጋዜጠኝነት ስራቸውን በነጻነት እንዳያከናውኑ በኢትዮጵያ መንግስት ጫና እንደሚደረግባቸው ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2008) መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች የጋዜጠኝነት ስራቸውን በነጻነት እንዳያከናውኑ በመንግስት ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የውጭ ጋዜጠኞች ማህበር ሰኞ ገለጠ። ከቀናት በፊት ሁለት የማህበሩ ጋዜጠኞች ለ24 ሰዓት በጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወቀው ማህበሩ በመገናኛ ብዙሃን ላይ እይደረሰ ያለው ወከባ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንም አስታውቋል። ከአስተርጓሚያቸውንጋር በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ በቁጥጥር ስር ...

Read More »

በደቡብ ክልል በሱርማ ማህበረሰብ አባላት ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ግፍ በማህበራዊ ሚዲያው ቁጣን ፈጥረ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች የሱርማ ብሄረሰብ አባላትን አንገታቸውንና እግራቸውን በማሰር በፖሊስ መኪና ጭነው ሲወስዱዋቸው የሚያሳየው ፎቶግራፍ በማህበራዊ ሚዲያው ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ድርጊቱን የፈጸሙት የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊሶች ይሁኑ ወይም የክልሉን የፖሊስ መኪና የተጠቀሙ የመከላከያ ሰዎች ይሁኑ ባይታወቅም፣ ይህ በዚህ ዘመን ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ዘግናኝ ድርጊት፣ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ለመፈጸሙ ከተሽከርካሪው፣ ...

Read More »

አህዴድ አቶ ዘላለም ጀማነህን አባረረ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኦህዴድ ነባር አመራሮቹን ከሃላፊነት ማንሳቱን ቀጥሎአል። ቀድም ብለው ያለማእከላዊ ኮሚቴው እውቅና በስራ አስፈጻሚው ትእዛዝ ብቻ ተባረው ከነበሩት መካከል የአቶ ዳባ ደበሌ መባረር በማእከላዊ ኮሚቴው ሲጸድቅ፣ ” ከዚህ በሁዋላ ከኢህአዴግ ጋር አብሬ አልሰራም” ብለዋል ተብሎ ሲነገርላቸው የሰነበተው የኢህዴድ እና የኢህአዴግ የስራ ...

Read More »

ከይዞታቸው የተነሱ ነዋሪዎች ተገቢውን ካሳ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በላሊበላ አብያተ ክርስትያናት ዙሪያ ያሉት አካባቢዎች እንዲፀዱና የበለጠ መስህብነት እንዲኖራቸው በማሰብ ከመንግስት በቀረበላቸው ዕቅድ በመስማማት አካባቢውን የለቀቁት ነዋሪዎች በተነገራቸው መጠን የካሳውን ገንዘብ ካለማግኘታቸውም ሌላ ሊሰራላቸው የታሰበው መሰረተ ልማት ባለመገንባቱ በችግር ላይ መሆናቸውን ተነሺዎች ተናግረዋል፡፡ በዘላቂ ቱሪዝም መቋቋም አለባቸው በሚል ከዓለም ባንክ ለነዋሪዎች የተመደበው የ300 ሚሊዮን ብር በጀት ለታሰበለት አላማ ያለመዋሉ ሚስጥር ...

Read More »

አንድ ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ ተደብቆ ስዊድን ገባ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነቱ ያልተገለጠው ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ አውሮፐላን ውስት በመሆን ከ10 ሰአት ከ25 ደቂቃ በረራ በሁዋላ አርላንዳ አየር ማረፊያ ደርሷል። ግለሰቡ በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ስደተኝነት መጠየቁም ታውቋል። ነሃሴ ወር ውስጥ አንድ የአየር መንገድ ሰራተኛ በእቃ መጫኛ አውሮፐላን ውስጥ ሆኖ ስዊድን መግባቱ ይታወቃል። በሌላ ዜና ደግሞ በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተገድሏል። ...

Read More »

የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በአሸባሪነት ተከሰሱ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ 13 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል አቃቤ ሕግ የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው። በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች አቶ ሉሉ መሰለን ...

Read More »

ኦብነግ ቻይናንና ጅቡቲን አስጠነቀቀ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ የዓለማቀፉን የኢንርጂ ኃይል ሪፖርት ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ – ቻይና፣ ጁቢቱና ኢትዮጵያ ተባብረው የኦጋዴንን ጋዝ ለመበዝበዝ እየሰሩ እንደሆነ በመጥቀስ፣ ከኦጋዴን -እስከ ጅቡቲ ድረስ የተፈጥሮ ጋዝን በቧንቧ ለማስተላለፍ አዲስ የሜጋ ፕሮጀክት መነደፉን እና የጂቡቲው ፕሬዚዳንትም “ዳመርጆግ” በተባለችው የጅቡቲ ከተማ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን አትቷል። ቻይና፣ ጅᎅቲና ኢትዮጵያ ይህን ውልና ስምምነት ሲያደርጉ የተፈጥሮ ጋዙ ...

Read More »